አምስቱ አዕማደ ሚስጥራት

አምስቱ አዕማደ ሚስጥራት

አምድ ማለት ምሰሶ ማለት ሲሆን አእማድ ማለት ምሰሶዎች ማለት ነው ። ቤት በአምድ (በኮለም) እንደሚፀና ፤ ሃይማኖትም በነዚህ ምሥጢራት ተጠቃሎ ይገለጻል ፤ ምዕመናንም እነዚህን ምሥጢራት በመማር ፀንተው ይኖራሉ ።

ምሥጢር ፤ ማለት ለተወሰነ ጊዜ በተወሰኑ ሰዎች ብቻ ተጠብቆ የሚቆይ ሲሆን ፤ በዚህ ትምህርታችን ግን በሚታዩ ምሳሌዎች የማይታየውን የሃይማኖት ምሥጢር መረዳት ፤ በሚታይ አገልግሎት የማይታይ ፀጋ ማግኘት ማለት ነው ።

አምስት ፤ ቁጥራቸው አምስት ብቻ ሆኖ የተወሰነው ፤ በ1 ሳሙ 17 40 ። እና በ 1ቆሮ 14 19 ። ባለው ቃል መሠረት ሲሆን ፤ አምስት መሆናቸውና የተደረጉባቸው ድንቅ ሥራዎች የአምስቱ አእማደ ምሥጢር ምሳሌነታቸውን ያስረዳል

✥ ምሥጢረ ሥላሴ  (የሥላሴን አንድነትና ሦስትነት)  Mystery of Holy Trinity
✥ ምሥጢረ ሥጋዌ  (የአምላክን ሰው መሆን)  Mystery of Incarnation
✥ ምሥጢረ ጥምቀት  (ስለ ዳግም መወለድ)  Mystery of Baptism
ምሥጢረ ቁርባን  (ስለ ክርስቶስ ሥጋና ደም)  Mystery of Holy Eucharist
✥ ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን  (ስለ ዳግም ምጽዓት)  Mystery of Resurrection of the dead
             

አምስቱ አዕማደ ምሥጢር በአፈጻጸማቸው በሦስት ይከፈላሉ ) ምሥጢረ ሥላሴና ምሥጢረ ሥጋዌ አምነን የምንቀበላቸው፤ ) ምሥጢረ ጥምቀትና ምሥጢረ ቁርባን አምነን የምንተገብረው፤ ) ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን አምነን በተስፋ የምንጠብቀው።

እነዚህን ምሥጢራት በቅደም ተከተል እንመለከታለን፤

ምሥጢረ ሥላሴ

ሠለሰ ሶስት አደረገ ፤ ካለው የግዕዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ፤ ሥላሴ ማለት ሶስትነት ማለት ነው ። በዚህ ትምህርት የአምላክን አንድነት ሶስትነት እንማራለን ።

የምሥጢረ ሥላሴን ትምህርት በምንማርበት ጊዜ ከሂሳብ ቀመር ህግ አስተሳሰብ ውጭ ሆነን ነው ። ምክንያቱም መንፈሳዊዉ ሥጋዊዉን ጥበብ (ፍልስፍና) ይመረምረዋል እንጅ መንፈሳዊ ጥበብና ምሥጢር በዓለማዊ ዕውቀት ምርምር ሊደረስበት አይቻልምና ። የሃይማኖት ነገር ቁሳዊ ሳይሆን መንፈሳዊና በሃይማኖት ሆኖ በመንፈሳዊነት የሚታወቅና የሚታመን ነው ።

የምሥጢረ ሥላሴ ትምህርት በብሉይ ኪዳን ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌያችን እንፍጠር አለ” ዘፍ 1 26 ። ። ከዚህ ቃል በፊት  እዚህ በመጫን ያንብቡ

ምሥጢረ ሥጋዌ

ሥጋዌ : ተሰገወ ሰው ሆነ ካለው የግዕዝ ቃል የተገኘ ሲሆን : ምሥጢረ ሥጋዌ ማለት ሰው የመሆን ምሥጢር ማለት ነው::

አምላክ ለምን ሰው ሆነ?

  1. አዳምን ከበደል ሊያነጻው አዳም የሰይጣንን ምክር በመስማት እግዚብአሔር አትብላ ያለውን ዕፀ በለስ በልቶ ትእዛዙን በማፍረሱ ከፈጣሪው በተጣላ ጊዜ የሞት ፍርድ (ሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ) ተፈረደበት ። ዘፍ 31 ። ለጥፋቱ ምክንያት የነበሩት ዕባብና ሄዋንም እንደ ጥፋታቸው መጠን ተረግመዋል ። ዘፍ 314 አዳምም ጥፋቱን አምኖ ንስሓ ስለገባ አምላክ ሰው ሆኖ እንደሚያድነው ቃል ገባለት ። ዘፍ 3 22 ። ቃል ኪዳኑም  እዚህ በመጫን ያንብቡ

ምሥጢረ ጥምቀት

ጠመቅ ማለት መነከር፣ መዘፈቅ፣ ውኃ ውስጥ ገብቶ መውጣት ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ጥምቀት የሥላሴ ልጅነት የሚሰጥበት እና የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት ምሥጢር ነው፡፡

የጥምቀት አመሠራረት

የምስጢረ ጥምቀት መሥራች ጌታችንና አምላካችን መድድኃኒታችን  እዚህ በመጫን ያንብቡ

ምሥጢረ ቁርባን

ቁርባን ፤ ማለት ፣ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ አምኃ ፣ መስዋዕት ፣ መንፈሳዊ ነገር ሁሉ ማለት ሲሆን ፤ በዚህ ትምሕርታችን ግን ፤ ስለ ሐዲስ ኪዳን መስዋዕት (የክርስቶስ ሥጋና ደም) እንማራለን ።

በብሉይ ኪዳን ለሐዲስ ኪዳን ቁርባን (መስዋዕት) ምሳሌዎች

  • የመልከ ጼዴቅ መስዋዕት ዘፍ 14 18 ። ዕብ 5 6 ። ዕብ 6 1 ። ህብስቱ የሥጋው ፤ ወይኑ የደሙ ምሳሌ ፤ መልከ ጼዴቅ የክርስቶስ ፤ አብርሐም የምዕመናን ።

  • የእስራኤል ፋሲካ ። ዘፀ 12 1 ። ሞት የዲያብሎስ ፤ እስራኤል የምዕመናን ፤ በጉ የክርስቶስ ምሳሌ ።

  • የእስራኤል መና ። ዘፀ 16 13 ። መና የጌታችን ቅዱስ ሥጋና ክቡር ደም ፤ እስራኤል የምዕመናን ፤ ደመና የእመቤታችን

በብሉይ ኪዳን መስዋዕት ቁርባን ያቀረቡና በረከት ያገኙ አባቶች አዳም አባታችን  እዚህ በመጫን ያንብቡ

ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን

1 የጌታችን ትንሣኤ

ስለ ጌታችን ሞትና ትንሣኤ የተነገረ ትንቢት ፤ የተመሰለ ምሳሌ

ትንቢት

  • እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁ ፤ እግዚአብሔር (እግዚአብሔርነቴ) ደግፎኛልና ነቃሁ ። መዝ 3 5

  • እግዚአብሔር ይነሣ ፤ ጠላቶቹም ይበተኑ ፤ የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ ። መዝ 27 1

  • እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሳ ። መዝ 77 65

ምሳሌ

  • ዮናስ ፤ ሶስት ቀንና ሶስት ሌሊት በዓሣ ነባሪ ሆድ ውስጥ ማደሩ ፤ ለጌታችን ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ ፤ እንደነበረ ጌታችን ተናግሯል ። ዮና 3 1 ። ማቴ 12 40

  • በዮርዳኖስ ባህር ውስጥ ገብቶ መጠመቁ የሞቱ ፤ ከባህር መውጣቱ የትንሣኤው ምሳሌ ነበር ።

ጌታችን ዓርብ ከቀኑ በዘጠኝ ሠዓት ቅድስት ነፍሱን ከቅዱስ ሥጋው በፈቃዱ ከለየ በኋላ  እዚህ በመጫን ያንብቡ

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top