አላህ እና እግዚአብሔር አንድ ናቸው ወይ ?
፨ የእግዚአብሔር ስም በመጽሐፍ ቅዱስ
በእስልምና ሃይማኖት የአምላካቸው ስም አላህ ነው፡፡ ይህ ስም ምንጩ ከየት ነው? በእርግጥስ እነርሱ (እስላሞች) እንደሚሉት ይህ ስም በፊት በብሉይ ኪዳን ኋላም በሐዲስ ኪዳን የተገለጸው አምላክ ስም ነው? ክርስቲያኖችና እስላሞችስ አምላካቸው አንድ ነው? ልዩነት ካለስ የስም ልዩነት ብቻ ነው ወይስ መሠረታዊ የሆነ የ‹ምን›ነትና የ‹ማን›ነት ልዩነት አለ?
በብሉይ ኪዳን ያህዌ(YHWH) ይለዋል። ይህም ‹‹ዘሀሎ ወይሄሉ – ያለና የሚኖር›› ማለት ነው (ዘፍ ፫፥፲፬) ምንጩም ‹‹ሀዋህ – መኖር›› ከሚለው የዕበራይስጥ ቃል ነው።
በእስላሞች መጽሐፍ የአምላካቸው ስም “አላህ” እንደሆነ ሁሉ ፧ መጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተገለጸው የእግዚአብሔር ስም ደግሞ “ያሕዌ” ነው። ያህዌ የሚለው ስም ከሌላ ባህልም ሆነ እምነት ያልተወረሰ ወይም ያልተቀዳ፣ ሌላ አህዛባዊ ምንጭ የሌለው ነው የተገለጠው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው ።
፨ አላህ የሚለው ስም ከየት መጣ ?
እንደ ጥንተ ታሪክ ጥናት ማስረጃዎች ‹‹አላህ›› በመካ ይመለኩ ከነበሩት ብዙ ጣዖታት መካከል ዋናው ነው። አላህ የሚለው ስም አል እና ኢለህ (al” and “illah) ከሚሉት የዐረብኛ ቃላት የተገኘ ሲሆን (የታወቀ አምለክ ወይም ጣዖትን – “the god” or “the idol.”) የሚገልጽ ነው።
አላህ ሙሉ በሙሉ ዓረቦች ያመልኩት የነበረውን አምላክ(ጣዖት) የሚገልጽ እንጂ ፍፁም እግዚአብሔር ከሚለው የአምላካችን ስም ጋር ምንም ዝምድና የለውም።
‹‹ረቢ›› የሚለው ቃል “መምህር” የሚል ፍቺ አለው። አንዳንድ ሰዎች የእስላሞች ብቻ ይመስላቸዋል ትክክል አይደለም። ይሄ ቤተ ክርስቲያናች ትጠቀምበታለች ኃጢአትም አይደለም ምክንያቱም ዕብራይስጥ ስለሆነ እንጂ በአማርኛ መምህር ማለት ነው።
አላህ የመጽሐፍ ቅዱሳችን አምላክ እንደሆነና በቅዱሳት መጻሕፍትም እንደተጠቀሰ እስላሞች ይናገራሉ። ይህ ደረቅ ስህተት ነው። አላህ የሚለው ስም በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን ኣንዴም የተጠቀሰበት ቦታ የለም።
እስላሞች አላህ የሚለው ስም የትመጣ (ምንጭ) መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን ለማሳመን ለምን ይጨነቃሉ? ከዚህስ ምን ያገኛሉ?
አላህ የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ የተገኘ መሆኑን ማሳመን ከቻሉ ከአይሁዳዊነት ወደ ክርስትና ከዚያም ወደ እስልምና ሽግግር ተደርጓል ለሚሉት ዋናና መሠረታዊ የመከራከሪያ አሳብ አስረጅ ይሆነናል፣ አይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ወደ እስልምና ለመለወጥ መንገዱን ቁልቁለት ያደርግልናል ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡ አላህ የሚለው ስም አንዱ አምላክ በቅዱሳት መጻሕፍት አማካይነት ራሱን የገለጠበት ቀጣይ ሂደት ከሆነ እስልምና ከመጽሐፍ ቅዱስ ቀጥሎ የሚመጣ እምነት መሆኑ ነው፡፡ ይህም ማለት አይሁዳዊነት በክርስትና እንደተተካ፣ ክርስትናም በእስልምና ተተካ ማለት ነው፡፡ ነገር ግን አላህ የሚለው ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ ምንም ፍንጭ የሌለው እና ከእስልምና መምጣት በፊት በዐረብ ምድር የነበረ የጣዖት “አምላክ” ስም ከነበረ ደግሞ የእስልምና መሠረት ፉርሽ ሆነ ማለት ነው፡፡ ለዚህ ነው አላህ የሚለው ስም የጨረቃ አምላክ ስም የነበረ፣ ከጣዖት አምልኮ የተወረሰ መሆኑን ከላይ ሰፋ አድርገን ማየት ያስፈለገን፡፡
በዐረቢያ ምድር የተገኙ የተለያዩ የከርሰ ምድር ቁፋሮ ውጤቶች አላህ የተባለው አምላክ የጣዖት አምላኪዎች “አምላክ” የነበረ መሆኑን በግልጽ ያሳያሉ፡፡ ከፀሐይ አምላክ ጋር የተጋባና ሦስት ልጆችን ያስገኘ “አምላክ” ተብሎ ይታመን እንደነበር በብዙ ማስረጃዎች የተመሰከረ መሆኑን አይተናል፡፡ ከቱርክ ተራራዎች እስከ ግብጽ ድረስ ተስፋፍቶ የነበረው የጣዖት አምልኮ የጨረቃ አምልኮ ነበር፡፡ በሥነ ፍጥረት ተመራምሮ ወደ ፈጣሪው እስኪደርስና እግዚአብሔርም ተገልጦ አገሩንና ቤተሰቦቹን ሁሉ ትቶ ከከለዳውያን ዑር እንዲወጣና ወደ ከነዓን እንዲሄድ እስኪነግረው ድረስ የአብርሃምም እምነት ይኸው ነበር፡፡
ይህ እውነት መሐመድ “አላህ” የሚለውን ስም በቁርዓን ለምን እንዳልተረጎመው ያስረዳናል፡፡ መሐመድ ለዐረቦች ስለ አላህ ሲናገር ከዚያ በፊት ምንም ሰምተውት ለማያውቁ ሰዎች አዲስ አምላክ እንደሚናገርና እንደሚያስተዋውቅ ሳይሆን አላህ ማን እንደሆነ አስቀድሞ ለሚያውቅ ሰው እንደሚናገር ባለ ሰው አቀራረብና አነጋገር ነው የተናገራቸው፡፡ አላህን የማያውቁትና አዲስ አምላክ እያስተዋወቃቸው ቢሆን ኖሮ አላህ እንዲህ ነው በማለት ማንነቱን ማስተማር ከሁሉም በፊት ይቀድም ነበር፡፡ መሐመድ በአላህ አምልኮ ያደገ ነው፡፡ ነገር ግን ከሌሎቹ አሕዛብ-ፖጋን ዐረቦች አንድ እርምጃ አልፎ ሄደ፡፡ እነርሱ የጨረቃ አምላክ የሆነው አላህ ከሌሎቹ አማልክት የበለጠና ቀዳሚው ነው ብለው ሲያምኑ መሐመድ ግን አላህ ከሁሉም አማልክት የሚበልጠው ብቻ ሳይሆን ብቸኛውም አምላክ ነው አለ፡፡
መሐመድ በተግባር ያለው እንዲህ ነው፡- “የጨረቃ አምላክ አላህን ከሁሉም አማልክት በላይ መሆኑን ከበፊትም ጀምሮ ታምናላችሁ፡፡ አሁን እኔ ከእናንተ የምፈልገው ነገር ቢኖር እርሱ ከሁሉም የሚበልጥ ብቻ ሳይሆን ብቸኛ አምላክ መሆኑን ነው፡፡ ቀድሞም የምታመልኩትን አላህን አልወስድባችሁም፣ ሌላ የማታውቁት እንግዳ አምላክም አላመጣባችሁም፡፡ እኔ ያስወገድኩት ሚስቱን (የፀሐይን አምላክ)፣ ልጆቹን እና ሌሎቹን አማልክት በሙሉ ነው፡፡”
ይህ ከመጀመሪያው የእስልምና የሃይማኖት መግለጫ- አላህ ከሁሉ የበለጠ ነው- ከሚለው ግልፅ ሆኖ ይታያል፡፡ “አላህ ታላቅ ነው” (Allah is great) – ሳይሆን ንጽጽርን በሚያሣይ ሁኔታ “አላህ (ከሁሉም) የበለጠ ነው” (Allah is the greatest) ነው የሚለው፡፡ ይህም ማለት አላህ ከሌሎቹ አማልክት የበለጠ ነው ማለት ነው፡፡ ይህም በመሆኑ ፖጋን (ጣዖት አምላኪ) የነበሩት ዐረቦች አስቀድሞም ያውቁት ከነበረውና ከሚያመልኩት አምላክ ውጭ ሌላ አዲስ አምላክ እንዳመጣባቸው አድርገው አልተናገሩትም፣ አልተጣሉትምም፡፡ “አላህ ማነው?” ብለውም አልጠየቁትም፡፡ “ከዚህ በፊት የማናውቀውን አዲስ አምላክ ከየት አመጣኸው?” አላሉትም፡፡ አላህ የሚለው ስም ለእነርሱ እንግዳ አልነበረምና፡፡ ሲያመልኩት የነበረ፣ የሚያውቁት ነው፡፡
ስለዚህ መሐመድ በሁለቱም በኩል አትራፊ የሆነ ስልትን ለመጠቀም ሞከረ፡፡ ለጣዖት አምላኪ ፖጋኖች አሁንም በጨረቃ አምላክ በአላህ አምናለሁ አላቸው፡፡ ለአይሁድና ለክርስቲያኖች ደግሞ አላህ የእነርሱም አምላክ ነው ለማለት ሞከረ፡፡ ነገር ግን በባሕርይው ያለና የሚኖር- ያሕዌ- ዘላለማዊ አምላክን የሚያመልኩ ክርስቲያኖችና በኋላ ተስፋውን ባለመቀበላቸው ራሳቸውን ከድኅነት ውጭ ያደረጉ አይሁድም ሁለቱም የመሐመድ የጨረቃ አምላክ- ሐሰተኛ አምላክ- መሆኑን ስለሚያውቁ ውድቅ አድርገውበታል፡፡ የቀደሙ የክርስቲያንና የእስላም ክርክሮችን በጥልቀት ያጠናው ኒውማን (ዶ/ር) ጥናቱን “እስላም ከጣዖት አምልኮ የተወለደ፣ የተለየና በጥላቻ የታመቀ እምነት ነው” በማለተ ጥናቱን አጠቃሏል፡፡[20]
እስላሞች ከፍ ብለን የጠቀስነውን እውነታ ሁሉ የክርስቲያኖች የጥላቻ መግለጫ ነው ብለው ያስቡ ይሆን? ታዲያ የእስልምና ምልክት ጨረቃ መሆኗ በአጋጣሚ የመጣ ይሆን? የጨረቃ ምስል በመስጊዶቻቸውና በሚናሬቶቻቸው ጫፍ ላይ መቀመጡ እንዲሁ ያለምንም ታሪካዊ የት መጣ የተደረገ ይሆን? የጨረቃ ምልክት በብዙዎቹ እስላም አገሮች ባንዲራ ላይ መደረጉስ? ጨረቃ በሰማይ ላይ መታየት ስትጀምር በሚጀምረው ወር ጀምረው ይህቺው ጨረቃ ስትታይ በሚያልቀው ወር የሚጾሙትስ?
አላህ” የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል?
እስላሞች አላህ የሚለው ስም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ይገኛል ሲሉ ይሰማል፡፡ አላህ በቁርአን አንድ ጊዜም ያህዌ አልተባለም፣ ያህዌም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በጭራሽ አላህ አልተባለም፡፡ ኤሎሂም የሚለው ለያህዌ ተደጋግሞ የተነገረው በዕብራይስጥ ቃልም በቁርአን አንድ ቦታም ላይ አገልግሎት ላይ አልዋለም፤ አልተጠቀሰም፡፡
በመጽሐፍ ቅዱስ ራሱን “ያለና የሚኖር” በማለት የገለጸው አምላክ ራሱን የአብርሃም፣ የይስሐቅና የያዕቆብ አምላክ ነኝ በማለት ገለጸ፡፡ ይህ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን የዳዊት ከተማ በማለት ይጠራታል፡፡ መሲሑም ከዳዊት ዘር እንደሚወለድ ይናገራል፡፡ እንደተናገረም ተፈጽሟል፡፡ የአላህ ቅዱስ ሥፍራ የሚባሉትን መካንም ሆነ መዲናን አንድ ጊዜም አያነሣቸውም፡፡ ኢየሩሳሌምን ግን ስምንት መቶ ጊዜ ያህል ያነሣታል፡፡ ኢየሩሳሌም በቁርአን አልተጠቀሰችም፡፡ ሆኖም እስላሞች የእነርሱ እንደሆነች ይናገራሉ፡፡ መጽሐፋቸው ግን አንዴም አያነሣትም፡፡
በብሉይ ኪዳን ዘመን እግዚአብሔር የእስራኤላውያን አምላከ ነኝ አለ፡፡ እነርሱም የእርሱ ምርጦች ተባሉ፡፡ ይህም በሐዲስ ኪዳን ለክርስቲያኖች ሁሉ ነው፡፡ እነዚህ እስራኤላውያን የአላህ ምርጦች ግን አልተባሉም፡፡ ታድያ በብሉይ ዘመን አይሁድ፣ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ ክርስቲያኖች የእግዚአብሔር ምርጦችና የበኩር ልጆች እንጂ የአላህ አይደሉም፡፡ አላህማ አንድ እስላም ሌላውን አይሁዳዊም ሆነ ክርስቲያን ጓደኛው እንዳያደርግ ይከለክላል፡፡ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ፣ ይሁዶችንና ክርስቲያኖችን ረዳቶች አድርጋችሁ አትያዙ” ይላል (5፣51)፡፡
እስላሞች ከእስልምና ዘመን በፊት አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ ያህዌ (ዘሀሎ ወይሄሉ)- የአባቶች፣ የነቢያትና የሐዋርያት አምላክ እግዚብሔር ነው ይላሉ፡፡ የእስልምና እምነት ተከራካሪ የሆነው አሕመድ ዲዳት “ሃሌሉያ” (“Allelujah”) የሚለውን “አላህሉያ” (“Allahlujah”) ወደሚል የግድ መጠምዘዝ አላህ የመጽሐፍ ቅዱሱ የእግዚብሔር ስም ነው በማለት ይከራከራል፡፡[21]Yahweh) አጭር መግለጫ – ያህ YAH – ማመስገን (አመስግኑ) በሚለው የዕብራይስጥ ቃል ከመነሻው ሲቀደም የሚገኝ ነው፡፡ በጥሬ ቃሉ ሃሌሉያ ማለት ያህዌን አመስግኑ ማለት ነው፡፡ (alle – ማመስገን – praise,፣ ለ to, yah-ያህዌ- Yahweh) የቃሉ መጀመሪያ Hallel -ሀለል- ሲሆን ይህም ማመስገን ማለት ነው፡፡ ይህም ከአላህ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የለውም፡፡ የመጨረሻው ቃል ያህ- ደግሞ ያለና የሚኖር ሕያው የሆነውን አምላክ የሚያመለክት ነው፡፡ አሕመድ ዲዳት አራማይክንና ዐረብኛን በመደባለቅ ምናልባት ከእርሱ ያነሰ ዕውቀት ያለው ሰው ቢያገኝ አለማወቁን ተጠቅሞ ለማምታታት ሞክሯል፡፡ ከሌላ ቋንቋ የተገኘ ቃል አነባበቡ ከአንድ ሌላ ቋንቋ ጋር ቢመሳሰል እንኳን አጋጣሚ ሊሆን ይችላል እንጂ የንባብ መመሳሰል የትርጉም ወይም የአሳብ መመሳሰልን አያመለክትም፡፡ እንደ ዲዳት ያሉ እስላሞች ግን የሌላን ቋንቋና ባህል፣ ቃላትና ትርጉሞች የሚመሳሰሉ መስለው ከታዩዋቸው፣ የራሳቸውን መጽሐፍም ሆነ እምነት አስረጂዎች ለማስመሰል ይሞክራሉ፡፡ ይህ የሚያሳየው ዲዳት ዕብራይስጥና አራማይክ የማያውቅ ብቻ ሳይሆን ደፋር አላዋቂ መሆኑንም ነው፡፡ “ሃሌ ሉያ” የያህዌ (
እንዲሁም ይኸው ሰው አላህ የሚለው ቃል ከጣዖት አምልኮ ባህልና ታሪክ ፈጽሞ የጸዳና የጠራ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ “አላህ የብቸኛው አምላክ ልዩና ብቸኛ ስም ነው፡፡ …ማንም ለአላህ አንስታይ ፆታ ሊናገርለት አይችልም” ይላል ዲዳት፡፡ ከአላህ ልጆች አንዲቷ የአላህ አንስታይ ፆታ መግለጫ በሆነ ስያሜ አል-ላት ትባል የነበረ መሆኑን ግን ለአንባቢዎቹ አይነግራቸውም፡፡ ራሱም አያውቀው ይሆናል፡፡
ለስም አጠራሩ ክብርና ምስጋና ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የእነርሱን አምላክ ስም እንደጠራ ለማድረግ ሲሞክሩ የቃላት ጨዋታው የበለጠ አስቂኝ ይሆናል፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ” በማለት የጠራው የእነርሱን አምላክ እንደሆነ ያወራሉ፡፡ ሐዲስ ኪዳን የተጻፈው በግሪክ ቋንቋ ሲሆን ጌታችን በአራማይክ ቋንቋ የተናገረውን ነው የሚያሳየን፡፡ ጌታችን በመዝሙር 21፣1 ላይ የተነገረውን የሰውን ልጆች ጩኸት በሙሉ ነው እኛን ወክሎ የጮኸው፡፡ ይህም በአራማይክ ቋንቋ በድምፀ ንባብ ማጠጋጋት ዐረብኛ ቃል ለማግኘት የሚደረግ አስቂኝ ሙከራ ነው፡፡ ይህን መላ ምታቸውን የበለጠ ትርጉም የለሽ የሚያደረገው ደግሞ በመስቀል ላይ የተሰቀለው ኢየሱስ መሆኑን የማያምኑ መሆናቸው ነው፡፡ መጽሐፋቸው የተሰቀለው ኢየሱስ ሳይሆን በእርሱ ቦታ ሌላ ሰው ተተክቶ ነው ይላልና፡- “እኛ የአላህን መልክተኛ የመርየምን ልጅ አልመሲሕ ዒሳን ገደልን በማለታቸውም (ረገምናቸው)፣ አልገደሉትም፣ አልሰቀሉትም፤ ግን ለነሱ የተገደለው ሰው በዒሳ ተመሰለ…በእርግጥም አልገደሉትም” 4፣157፡፡ ታዲያ የእነርሱ “ዒሳ” በመስቀል ላይ ካልተሰቀለና ካልሞተ ኤሎሄ የሚለው የአራማይክ ቃል፣ አላህ ከሚለው የዐረብኛ ቃል ጋር በድምፀ ንባቡ ትንሽ ስለተቀራረበ ብቻ አሁን ለዚህ ሲሉ ሊሰቅሉት ነው?
ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና ? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው ? 2ኛ ቆሮ 6፥14 ወዳጆች፥ እናንተን ልናንጻችሁ ሁሉን እንናገራለን ፧ 2ኛ ቆሮ 12፥19