መላእክት

አምላካችን እግዚአብሄር የቸርነቱን ብዛት ካሳየባቸው መንገዶች አንዱ ስነ-ፍጥረት ነው፡፡ አምላክ ከቸርነቱ ብቻ ተነስቶ እሱ ያለውን ፍቅር በመጋራት ይደሰቱ ዘንድ የራሳቸው ነፃ ፍቃድ ያላቸው ፍጥረታትን በሰባት ቀናት ፈጥሮ እንደጨረሰ በኦሪት ዘፍጥረት እናነባለን፡፡ ታዲያ ከፈጠራቸው ፍጥረታት መካከል በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ስለሁኔታቸው ጥቂት ብቻ ተጠቅሶ ከታለፉት ለየት ያለ አፈጣጠር ካላቸው ፍጥረታት ውስጥ አንዱ መላእክት ናቸው፡፡

*መላእክት ማለት ምን ማለት ነው? በስንት ይከፈላሉ?*

ከስም አሰያየሙ ብንነሳ “መላእክት” የግዕዝ ቃል ሲሆን ትርጉሙም መላእክተኞች ወይም ተላላኪዎች ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ እንደአገባቡ አለቆች ወይም አስተዳዳሪዎች የሚል ትርጉምም ሊኖረው ይችላል፡፡ አብዛኛው ጊዜ ሰዎች “መላእክት” የሚለውን ቃል ሲሰሙ ወዲያው ወደአእምሮአቸው የሚመጣው በብርሃን የተሸፈነ ባለ ትልቅ ክንፍ ፍጥረት ነው፡፡ በእርግጥ ትክክል ቢሆኑም “መላእክት” ሲባል የብርሃን ፍጥረታትን ብቻ የሚያመለክት ብቻ አድርጎም መውሰድ ትክክል አይደለም፡፡

መላእክት የሚለው ቃል መልእክተኞች ወይም ተላላኪዎች ማለት እንደሆነ አይተናል፡፡ ታዲያ ይህን በመመስረት “የሚላላኩት ማንን ነው” የሚለው ጥያቄ በመመለስ ለሁለት ስንከፍላቸው ፤ ለእግዚአብሄር አምላክ የሚላላኩትን ብርሃናዊ ፍጥረታት “ቅዱሳን መላእክት” ብለን ስንጠራቸው ለጠላታችን ዲያብሎስ የሚላላኩትን ጨለማ የተጎናፀፉ ፍጥረታትን ደግሞ “ርኩሳን መላእክት” በማለት እንጠራቸዋለን፡፡

*እግዚአብሄር አምላክ መላእክትን ለምን ፈጠረ?*

መላእክት የተፈጠሩበት ምክንያት ሰው ከተፈጠረበት ምክንያት የተለየ አይደለም፡፡ መላእክት የተፈጠሩት ልክ እንደ….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ቅዱሳን መላእክት (ክፍል 2) – ትምህርት በዲን ህብረት የሺጥላ

የቅዱሳን መላእክት አማላጅነት

 በዲያቆን ኅብረት የሺጥላ

ቅዱሳን መላእክት አማላጆቻችን ናቸው፡፡ ስለ ቅዱሳን መላእክት አማላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ በስፋት ተጽፏል፡፡ ይህንንም የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በመጥቀስና ትክክለኛ ትርጉማቸውን በምንረዳበት ጊዜ የምናገኘው ነው፡፡

የመላእክትን አማላጅነት በስድስት ዋና ዋና መንገዶች ከፍለን ለማየት እንችላለን፡፡

1ኛ. መቆም የሚለውን ቃል ትክክለኛ ትርጉም በመረዳት፡- መቆም የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በልዩ ልዩ ቦታዎች አገልግሎት ላይ ውሏል፡፡ እንደየአገባቡም ትርጉሙ የተለያየ ነው፡፡ መቆም የሚለው ቃል ከያዛቸው ትርጓሜዎች አንዱ ማማለድ የሚል ነው፡፡ መቆም ከተኙበት ወይም ከተቀመጡበት መነሣት፣ በእግር ቀጥ ማለት፣ መጽናት፣ በክብር መቀመጥ ወዘተ የሚሉ ሌሎች ትርጓሜያትም አሉት፡፡ ስለዚህ እንደየአገባቡ ታይቶ ይፈታል እንጂ ሁል ጊዜ ቃሉን በአንድ ዓይነት መንገድ ብቻ መመልከት ከስሕተት ላይ ይጥላል፡፡

ለዚህ ሁሉ አገባብ ማስረጃ ብትሻ እነዚህንና ሌሎችንም ጥቅሶች በሚገባ ፈትሽ፡፡ ‹‹የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ›.፣ ‹‹የደመናው ዓምድ ቆመ››፣ ‹‹በሃይማኖት ቁሙ›› (ሉቃ8.44፤ ዘዳ31.15፤ ዘኁ10.12፤ 1ቆሮ16.13) በእነዚህ ጥቅሶች ውስጥ መቆም የሚለው ቃል የተለያየ ሐሳብ ይዞ መገኘቱን ልብ ማለት ያሻል፡፡

አሁን ከዚህ ቦታ ከርእሳችን አንጻር እኛ የምንፈልገው ቆመ የሚለው ቃል ማማለድ የሚል ትርጉም ይዞ መገኘቱን መረዳት ነው፡፡ መቆም ሲባል ማማለድ የሚል ትርጓሜ እንዳለው ለመረዳት ስለ ሊቀ ነቢያት ሙሴ የተጻፈውን ልብ ማለት ያስፈልጋል፡፡ እስራኤላውያን ጣዖት በማምላክ ፈጣሪቸውን አስቆጡት፡፡ እርሱም ሊያጠፋቸው ጀመረ፡፡ ነገር ግን….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ቅዱሳን መላእክት (ክፍል 1) – ትምህርት በዲን ህብረት የሺጥላ

ቅዱሳን መላእክት

ቅዱሳን መላእክት ከተፈጠሩባት ከመጀመሪያዋ እለተ እሁድ አንስቶ እስከ ዛሬ ወደፊት ለዘለዓለም እግዚአብሔርን በቅድስና የሚያገለግሉ ተፈጥሯቸው የተቀደሰ ሕይወታቸውም በንጽሕና የተሞላ ነው፡፡

ቅዱሳን መላእክት በመንፈሳዊ ዓለም እየኖሩ በሰማይና በምድር በእግዚአብሔርና በሰው ፊት የቅድስናን መንፈሳዊ ሥራ የሚሰሩ ረቂቅ ፍጡራን ናቸው፡፡

#‹‹መላእክት›› የቃሉ ትርጉም

መላእክት የሚለው ቃል በ3 መንገድ ሊተረጐም ይችላል፡፡

  1. ‹‹መላእክት›› ማለት፡- መልእክተኞች፣ ተላላኪዎች ማለት ነው፡፡

ይህን ተግባር የሚፈፅሙት ቅዱሳን ሰማያውያን መላእክት ናቸው፡፡ የእርቅ፣የሰላም፣የበረከት መልእክተኞች ናቸውና፡፡

  1. ‹‹መላእክት›› ማለት አለቆች፣ ገዢዎች ማለት ነው፡፡

ይህ ደግሞ በሥልጣን መንበር ላይ ላሉ ሰዎችና ለቤተክርስቲያን አስተዳዳሪዎች አለቆች የሚሰጥ ስያሜ ነው፡፡ ራዕይ 1¸20 ‹‹በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምስጢር ይህ ነው፡፡ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፣ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው›› እንዲል፡፡

መልአከ አርያም፣መልአከ ሰላም፣መልአከ ገነት እንደሚባለው አጠራር ነው።

  1. ‹‹መላእክት›› ማለት ከክብር ይልቅ ኃሣርን መርጠው የተዋረዱትን ርኩሳን መናፍስት አጋንንትን መላእክት ይላቸዋል፡፡

ማቴ 25 41 ‹‹እናንተ ርጉማን ለሰይጣንና ለመላእክተኞቹ ወደተዘጋጀ ወደዘለዓለም እሳት ከእኔ ሄዱ›› እንዲል፡፡

#ቅዱሳን መላእክት ለምንና እንዴት ተፈጠሩ?

ቅዱሳን መላእክት በእለተ እሁድ በመጀመሪያው ሰዓት ተፈጥረዋል፡፡

እግዚአብሔር ቅዱሳን መላእክትን ሲፈጥር ‹‹እምኅበ አልቦ ኅበቦ›› ካለመኖር ወደመኖር አምጥቶ ፈጥሮአቸዋል፡፡

አፈጣጠራቸውም እንደሰው በነቢብ /በመናገር/ ሳይሆን በአርምሞ /በዝምታ/ ተፈጥረዋል፡፡ ሊፈጥራቸው አስቦ ፈጠራቸውም

የተፈጠሩበትም ዓላማ የሰውን ልመና፣ ንስሐ ወደእግዚአብሔር፣ የእግዚአብሔርን ምሕረት ወደ ሰው ለማድረስና መንፈሳዊ ሥራ ለመስራት እግዚአብሔርን ለማመስገን ተፈጥረዋል፡፡

#የቅዱሳን መላእክት የተፈጥሮ ሁኔታ /ኩነተ ተፈጥሮ/

ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ኢመዋትያን /የማይሞቱ/ ናቸው፡፡ ዝንተ ዓለም በቅድስና ቆመው እግዚአብሔርን ሲያገለግሉ ይኖራሉ፡፡

ቅዱሳን መላእክት ፈጻምያነ ፈቃድ ናቸው የእግዚአብሔርንና የሰውን ፈቃድ ሲፈጽሙ ይኖራሉ፡፡

ቅዱሳን መላእክት (አልቦ ፍፃሜ ለመዋዕሊሆሙ) ለዘመናቸው ፍፃሜ አይነገርላቸውም፡፡

ቅዱሳን መላእክት ተፈጥሮአቸው ከእሳትና ከነፋስ ነው፡፡

መዝ 103¸4 ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዩቹን የእሳት ነበልባል›› እንዲል፦

ነገር ግን ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ሲል ግብራቸውን ለመግለፅ እንጂ እንደምናየው እሳትና ነፋስ ቢሆኑ ኖሮ እንደእኛ ሰዎች ፈርሰው በስብሰው በቀሩ ነበር፡፡ ነገር ግን ከእውነተኛ አምላክ ብርሃን ተፈጥረዋልና እንደ እሳት ኃያላን፣ እንደእሳት ብሩሃን አእምሮ፣ እንደነፋስ ፈጣን፣ እንደነፋስ ረቂቅ መሆናቸውን ለመግለጽ ከእሳትና ከነፋስ ተፈጠሩ ይላቸዋል፡፡

  1. ኢዮር

ኢዮር ከሰባቱ ሰማያት ውስጥ በአምስተኛ ደረጃ ላይ ስትገኝ እግዚአብሔር በዚህች ከተማ ላይ ዐርባውን ነገደ መላእክት አስፍሯቸዋል፡፡ ሲያሰፍራቸው ለዐራት ከፍሎ ዐራት ዐለቆችን ሾሞላቸዋል፡፡ እነዚህንም ሲፈጥራቸው በ10ኛው ሰዓት ሌሊት ኢዮርን እንደፎቅ ላይ ቤት፣ ታች ቤት፣ ምድር ቤት አድርጐ ፈጥሯቸዋል፡፡

1.1 አጋእዝት

የመጀመሪያዎቹን በኢዮር ያሰፈራቸውን የመላእክት ነገዶች አጋእዝት ብሎ ጠራቸው፡፡ አለቃቸውን ሳጥናኤልን….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top