የኢትዮጵያ ንግሥት ህንደኬ አዛዥና ጃንደረባ ባኮስ የኢየሩሳሌም የአምልኮ ጉዞና ክርስትናን ወደ ኢትዮጵያ ይዞ መጥቷል። (የሐዋርያት ስራ 8:26)
ይህ የክርስትና እምነት በኢትዮጵያ እንዲስፋፋ ጉልህ አስተዋጽዖ ካበረከቱ ቅዱሳን መካከል ደግሞ ተሰዓቱ ቅዱሳን ወይም ዘጠኙ ቅዱሳን ይገኙበታል ።
ዘጠኙ ቅዱሳን (ተሰዓቱ ቅዱሳን) የተገናኙበት ቦታ፦ በቃልኬዶን በ፬፻፶፩ ዓ.ም.በተደረገው የሃይማኖት አበው ጉባዔ ሲሆን፣ ወደ ኢትዮጵያ የገቡበት ዘመን ፭ኛው ምዕተ ዓመት በንጉሥ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት ነው።
ዘጠኙ ቅዱሳን በኬልቄዶን ጉባኤ ምክንያት በተዋሕዶዎች ላይ በአውሮፓ፣ በእስያና በመካከለኛው ምሥራቅ በተነሣው ፈተና የተነሳ ከሮም፣ ከእስያ፣ ከአንጾኪያ፣ ከቁስጥንጥንያ፣ ከቂሳርያና ከኪልቂያ በስደት የመጡ ናቸው።
ዘጠኙ ቅዱሳን ስማቸውም ፦
፩ኛ – አቡነ አረጋዊ ሮም
፪ኛ – አቡነ ጰንጤሌዎን
፫ኛ – አቡነ የማታ አቡነ
፬ኛ – አባ ገሪማ
፭ኛ – አባ ድሕማ
፮ኛ – አባ አፍፄ
፯ኛ – አባ ሊቃኖስ
፰ኛ – አባ አሌፍ
፱ኛ – አባ ጉባ
ስማቸው የመጡበት አገር የገደሙበት ቦታ የመታሰቢያቸው ቀን
፩- አቡነ አረጋዊ ሮም ደብረዳሞ ጥቅምት ፲፬
፪- አቡነ ጰንጤሌዎን ሮም አክሱም ጥቅምት ፮
፫- አቡነ የማታ ቆስይ ገርዓልታ ጥቅምት ፳፰
፬- አባ ገሪማ ሮም መደራ/ዓድዋ/ ሰኔ ፲፯
፭- አባ ጽሕማ አንጾኪያ እንደ አባ ድሕማ/ይዲያ ጥር ፲፮
፮- አባ አፍፄ ታናሽ እስያ የሓ ግንቦት ፳፱
፯- አባ ሊቃኖስ ቁስጥንጥንያ አክሱም ህዳር ፳፰
፰- አባ አሌፍ ቂሳርያ ደብረ ሃሌሉያ መጋቢት ፲፩
፱- አባ ጉባ ኪልቂያ አድዋ አጠገብ ግንቦት ፳፱