የዘወትር ጸሎት

በአማርኛ

በስመ ሥላሴ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

 * በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ መስቀል ፊቴንና መላ ሰውነቴን ሦስት ጊዜ አማትባለሁ

፩. አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማጸንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለሁ፤ በዚህች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት። በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።
፪. አቤቱ እናመሰግንሃለን አቤቱ እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግንሃለን። ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበትም ሁሉ ለአንተ ይገዛል የአምላኮች አምላክ፣ የጌቶች ጌታ፣የንጉሦችም ንጉሥ አንተ ነህ የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።
፫. አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን  ዛሬ፤ በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል። አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት የአንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።
፬. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ። በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአቸናፊ  የእግዚአብሔር እናት ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባል ከሴቶቹ ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ  ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።
፭. ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ። የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም። ስለእኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ ደግሞም ስለእኛ ተሰቀለ በጰንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ፣ ሞተ፣ ተቀበረ፤ በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ፤ በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፤ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል፤ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው፤ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን  እናምናለን፤ ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን፤የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን፤የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።
፮. አቸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ። ምስጋናህም በሰማይና በምድር የመላ ነው። ክርስቶስ ለአንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ እንሰግድልሃለን ወደዚህ ዓለም መጥተህ አድነኸናልና።
፯. ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ (3 ጊዜ) አንድ ሲሆን ሦስት፤ሦስት ሲሆኑ አንድ፤ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለሁ። አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ፤ ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው፤ ኃይላችን መስቀል ነው፤ የሚያጸናን መስቀል ነው፤ መስቀል ቤዛችን ነው፤መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው። አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋል ያመነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም።
፰. ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል (3 ጊዜ) አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል፤ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ እንዳያሳፍረን ስሙን ለማመስገን ያነቃን ዘንድ። እርሱንም በማምለክ ያፀናን ዘንድ። እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጊልን ኃጢአታችንንም አስተሥርዪልን በጌታችን መንበር ፊት ጸሎታችንን አሳርጊልን ይህንን ኅብስት ላበላን፤ ይህንንም ጽዋ ላጠጣን ምግባችንንና ልብሳችንንም ላዘጋጀልን፤ ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሰልን፤ ክቡር ደሙን ቅዱስ ሥጋውን ለሰጠን፤እስከዚህችም ሰዓት ላደረሰን፤ ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም ምስጋና ይገባል ለወለደችው ለድንግልም ምስጋና ይገባል። ለክቡር መስቀሉም ምስጋና  ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱና በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።
፱. እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ለአንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን። ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል። ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።
፲. አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ጸሎት ማርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች መንፈሴም በመድኃኒቴ  በእግዚአብሔር ደስ ይላታል የባሪያዪቱን መዋረድ አይቷልና። እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና። ስሙም ቅዱስ ነው ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ነው ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ ትዕቢተኞችን በታተናቸው፤ ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤ የተራቡትንም በቸርነቱ አጠገባቸው፤ ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው። ምሕረቱን እንዲያስብ እስራኤል ባርያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩም እስከ ዘላለሙ ድረስ እንደተናገረ።

 

ግእዝ እና አማርኛ

* በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ መስቀል ፊቴንና መላ ሰውነቴን ሦስት ጊዜ አማትባለሁ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ

** አዐትብ ገጽየ ወኩለንታየ በትእምርተ መስቀል። በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ።

፩. አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማጸንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለሁ፤ በዚህች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት።በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን አምባ መጠጊያ አድርጌ እክድሃለሁ።

 *** በስመ ፡ አብ ፡ ወወልድ ፡ ወመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ አሐዱ ፡ አምላክ ፡ በቅድስት ሥላሴ ፡ እንዘ ፡ ኣአምን ፡ ወእትመኃፀን ፡ እክህደከ ፡ ሰይጣን ፡  በቅድመ ፡ ዛቲ ፡  እምየ ፡ ቅድስት ፡ ቤተክርስቲያን ፡  እንተ ፡ ይእቲ ፡  ስምዕየ ፡ ማርያም ፡ ጽዮን ፡ ለዓለመ  ፡ ዓለም።

 ፪. አቤቱ እናመሰግንሃለን አቤቱ እናከብርሃለን አቤቱ እንገዛልሃለን አቤቱ ቅዱስ ስምህን እናመሰግንሃለን። ጉልበት ሁሉ የሚሰግድልህ አቤቱ እንሰግድልሃለን አንደበትም ሁሉ ለአንተ ይገዛል የአምላኮች አምላክ፣የጌቶች ጌታ፣የንጉሦችም ንጉሥ አንተ ነህ የሥጋም የነፍስም ፈጣሪ አንተ ነህ። እናንተስ በምትጸልዩበት ጊዜ እንዲህ ብላችሁ ጸልዩ ብሎ ቅዱስ ልጅህ እንዳስተማረን እንጠራሃለን።

*** ነአኵተከ እግዚኦ ወንሴብሐከ ንባርከከ እግዚኦ ወንትአመነከ ንስእለከ እግዚኦ ወናስተበቍዓከ ንገኒ ለከ እግዚኦ ወንትቀነይ ለስምከ ቅዱስ ንሰግድ ለከ ኦ ዘለከ ይሰግድ ኵሉ ብርክ ወለከ ይትቀነይ ኵሉ ልሳን። አንተ ውእቱ ኣምላከ ኣማልክት፣ ወእግዚአ አጋእዝት፣ ወንጉሠ ንገሥት፣ አምላክ አንተ ለኵሉ ዘሥጋ ወለኵላ ዘነፍስ፣ ወንጼውዐከ ንሕነ በከመ መሀረነ ቅዱስ ወልድከ እንዘ ይብል አንትሙሰ ሶበ ትጼልዩ ከመዝ በሉ

፫. አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ መንግሥትህ ትምጣ ፈቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን የዕለት እንጀራችንን ስጠን ዛሬ፤በደላችንንም ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል።አቤቱ ወደ ፈተናም አታግባን ከክፉ ሁሉ አድነን እንጂ መንግሥት የአንተ ናትና ኃይል ክብር ምስጋና ለዘለዓለሙ አሜን።

 *** አቡነ ዘበሰማያት ይትቀደስ ስምከ ትምጻእመንግስትከ ወይኩን ፈቃድከ በከመመሰማይ ከማሁ በምድር ሲሳየነ ዘለለዕለትነ ሀበነ ዮም ኅድግ ለነ አበሳነ ወጌጋየነከመ ንሕነኒ ንኅድግ ለዘአበሰለነ ኢታብአነእግዚኦ ውስተ መንሱት አላ አድኅነነወባልሐነ እምኵሉ እኩይ እስመ ዚአከይእቲ መንግሥት ኃይል ወስብሐት ለዓለመዓለም

 ፬. እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ።በሀሳብሽ ድንግል ነሽ በሥጋሽም ድንግል ነሽ። የአቸናፊ የእግዚአብሔር እናት ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባል ከሴቶቹ ሁሉ ተለይተሽ አንቺ የተባረክሽ ነሽና የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው። ጸጋን የተመላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ነውና ከተወደደው ልጅሽ ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ይቅርታንና ምሕረትን ለምኝልን ኃጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ለዘለዓለሙ አሜን።

 **** በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ ኦእግዝእትየ ማርያም ሰላም ለኪ ድንግልበሕሊናኪ ወድንግል በስጋኪ እመእግዚኣብሔር ጸባዖት ስለም ለኪ ቡርክትአንቲ እምአንስት ወቡሩክ ፍሬ ከርሥኪተፈሥሒ ፍሥሕት ኦ ምልእተ ጸጋእግዚኦብሔር ምስሌኪ ሰአሊ ወጸልዪምሕረት በእንቲአነ ኀበ ፍቁር ወልድኪኢየሱስ ክርስቶስ ከመ ይሥረይለነ ኃጣውኢነ

 ፭. ሁሉን የፈጠረ አንድ አምላክ በሚሆን በእግዚአብሔር አብ እናምናለን። ሰማይንና ምድርን የፈጠረ የሚታየውንና የማይታየውን። ዓለም ሳይፈጠር ከእርሱ ጋር በነበረ አንድ የአብ ልጅ በሚሆን በአንድ ጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እናምናለን ከብርሃን የተገኘ ብርሃን ከእውነተኛ አምላክ የተገኘ አምላክ። የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ በባሕርዩ ከአብ ጋር የሚተካከል ሁሉ በእርሱ የሆነ በሰማይም ካለው በምድርም ካለው ያለ እርሱ ምንም ምን የሆነ የለም። ስለእኛ ስለ ሰዎች እኛን ለማዳን ከሰማይ ወረደ፤ በመንፈስ ቅዱስ ግብር ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም ሰው ሆነ ደግሞም ስለእኛ ተሰቀለ በጰንጤናዊ በጲላጦስ ዘመን እርሱ መከራን ተቀበለ፣ሞተ፣ተቀበረ፤በሦስተኛውም ቀን ከሙታን ተለይቶ ተነሳ፤በቅዱሳት መጻሕፍት እንደተጻፈ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ በአባቱም ቀኝ ተቀመጠ፤ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በምስጋና ይመጣል፤ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም። በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን እርሱም ጌታ ሕይወትን የሚሰጥ ከአብ የሠረፀ ከአብና ከወልድ ጋራ በአንድነት እንሰግድለታለን እናመሰግነዋለን እርሱም በነቢያት አድሮ የተናገረ ነው፤ከሁሉም በላይ በምትሆን ሐዋርያት በሠሯት በአንዲት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን፤ኃጢአት በሚሠረይባት በአንዲት ጥምቀትም እናምናለን፤የሙታንንም መነሣት ተስፋ እናደርጋለን፤የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን።

*** ጸሎት ሃይማኖት ነኣምን በኣሐዱ ኣምላክ እግዚኣብሔር ኣብ ኣኃዜ ኩሉ ሰማያት ወምድር ዘያስተርኢ ወዘኢያስተኢ። ወነኣምን በኣሐዱ እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ ኣብ ዋሕድ ዘህልው ምስሌሁ እምቅድመ ይፈጠር ዓለም። ብርሃን ዘእምብርሃን ኣምላክ ዘእምኣምላክ ዘበኣማን። ዘተወልደ ወኣኮ ዘተገብረ ዘዑሩይ ምስለ ኣብ በመለኮቱ። ዘቦቱ ኩሉ ኮነ ወዘእንበሌሁሰ ኣልቦ ዘኮነ ወኢምንትኒ ዘበሰማይኒ ወዘበምድርኒ። ዘበእንቲኣነ ለሰብእ ወበእንተ መድኃኒትነ ወረደ እምሰማያት። ተስብኣ ወተሠገወ ወእመንፈስ ቁዱስ ወእማርያም እምቅድስት ድንግል። ኮነ ብእሱ ወተሰቅለ በእንቲኣነ በመዋዕለ ጵላጦስ ጴንጤናዊ ሓመመ ወሞተ ወተቀብረ ወተንሥ እሙታን ኣመ ሣልስት ዕለት በከመ ጽሑፍ ዉስተ ቅዱሳት መጻሕፍት። ዐርገ በስብሓት ዉስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ ኣቡሁ፡ ዳግመ ይመጽእ በስብሓት ይኮንን ሕያዋነ ወሙታነ ወኣልቦ ማኅለቅት ለመንጉሥቱ። ወነኣምን በመንፈስ ቅዱስ እግዚእ ማሕየዊ ዘሰረፀ እም ንሰግድ ሎቱ ወንሰብሖ ምስለ ኣብ ወወልድ ዘነበበ በነቢያት። ወነኣምን በኣሐቲ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንተ ላዕለ ኩሉ ጉባኤ ዘሓዋሪያይ፡ ወነኣምን በኣሓቲ ጥምቀት ለሥርየተ ኃጢኣት። ወንሴፎ ትንሣኤ ሙታን ወሕይወት ዘይመጽእ ለዓለመ ዓለም።

 ፮. አቸናፊ እግዚአብሔር ሆይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ ትመሰገናለህ። ምስጋናህም በሰማይና በምድር የመላ ነው። ክርስቶስ ለአንተ እንሰግድልሃለን ከሰማያዊ ከቸር አባትህ ጋራ አዳኝ ከሆነ ከመንፈስ ቅዱስም ጋራ እንሰግድልሃለን ወደዚህ ዓለም መጥተህ አድነኸናልና።

*** ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚኣብሔር ጸባዖት ፍጹም ምሉእ ሰማያት ወምድር ቅድሳተ ስብሓቲከ። ንሰግስ ለከ ክርስቶስ ምስለ ኣቡከ ኄር ሰማያዊ ወመንፈስከ ቅዱስ ማሕየዊ እስመ መጻእከ ወኣኃንከነ።

 ፯. ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ አንዲት ስግደት እሰግዳለሁ (3 ጊዜ) አንድ ሲሆን ሦስት፤ሦስት ሲሆኑ አንድ፤ በአካል ሦስት ሲሆኑ በመለኮት አንድ ለሚሆኑ እሰግዳለሁ። አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም እሰግዳለሁ፤ዓለምን ሁሉ ለማዳን ሲል ኢየሱስ ክርስቶስ ለተሰቀለበት መስቀልም እሰግዳለሁ። መስቀል ኃይላችን ነው፤ ኃይላችን መስቀል ነው፤ የሚያጸናን መስቀል ነው፤ መስቀል ቤዛችን ነው፤መስቀል የነፍሳችን መዳኛ ነው። አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋል ያመነው እኛም በመስቀሉ እንድናለን ድነናልም።

*** እሰግድ ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓተ ስግደተ

እሰግድ ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓተ ስግደተ

እሰግድ ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓተ ስግደተ

እንዘ ኣሓዱ ሠለስቱ ወእንዘ ሠለስቱ ኣሓዱ ይሤለሱ በኣካላት ወይትወሓዱ በመለኮት

እሰግድ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ ኣምላክ

እሰግድ ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘተከደሰ በደሙ ክቡር

መስቀል ኃይልነ

መስቀል ጽንዕነ

መስቀል ቤዛነ

መስቀል መድሃኒተ ነፍስነ። ኣይሁድ ክሕዱ።

ንሕነሰ ኣመነ ወእለ ኣመነ ብኃይለ መስቀሉ ድኅነ።

 ፰. ለአብ ምስጋና ይገባል ለወልድም ምስጋና ይገባል ለመንፈስ ቅዱስም ምስጋና ይገባል (3 ጊዜ)

አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለድንግል ማርያም ምስጋና ይገባል፤ለኢየሱስ ክርስቶስ መስቀልም ምስጋና ይገባል። ክርስቶስ በቸርነቱ ያስበን ዘንድ ዳግመኛም በመጣ ጊዜ እንዳያሳፍረን ስሙን ለማመስገን ያነቃን ዘንድ። እርሱንም በማምለክ ያፀናን ዘንድ። እመቤታችን ጸሎታችንን አሳርጊልን ኃጢአታችንንም አስተሥርዪልን በጌታችን መንበር ፊት ጸሎታችንን አሳርጊልን ይህንን ኅብስት ላበላን፤ ይህንንም ጽዋ ላጠጣን ምግባችንንና ልብሳችንንም ላዘጋጀልን፤ ኃጢአታችንንም ሁሉ ለታገሰልን፤ ክቡር ደሙን ቅዱስ ሥጋውን ለሰጠን፤እስከዚህችም ሰዓት ላደረሰን፤ለእርሱ ለልዑል እግዚአብሔር ፍጹም ምስጋና ይገባል ለወለደችው ለድንግልም ምስጋና ይገባል። ለክቡር መስቀሉም ምስጋና ይገባል። የእግዚአብሔር ስሙ ፈጽሞ ይመሰገን ዘንድ ዘወትር በየጊዜያቱና በየሰዓቱ ምስጋና ይገባል።

*** ስብሓት ለኣብ ስብሓት ለወልድ ስብሓት ለመንፈስ ቅዱስ ፡ 

ይደልዎም ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፡   

ስብሓት ለኣብ ስብሓት ለወልድ ስብሓት ለመንፈስ ቅዱስ ፡ 

ይደልዎም ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፡ 

ስብሓት ለኣብ ስብሓት ለወልድ  ስብሓት ለመንፈስ ቅዱስ ፡ 

ይደልዎም ለኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፡  

 ስብሓት ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ ኣምላኽ 

ይደልዋ ለእግዝትነ ማርያም ወላዲተ ኣምላኽ 

ስብሓት ለመስቀለ እግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ 

ይደልዎ ለመስቀለ ኢየሱስ ክርስቶስ

ክርስቶስ በምሕረቱ ይዘክረነ

ኣሜን

ኣመ ዳግመ ምጽኣቱ ኢያስትኃፈረነ

ኣሜን

ለሰብሖተ ስሙ ያንቅሓነ

ኣሜን

ወበኣምልኮቱ ያጽነኣነ

ኣሜን

እግዝእትነ ማርያም ድንግል ውላዲተ ኣምላኽ ኣእርጊ ጸሎትነ

ኣሜን

ወኣስተስርዪ ኩሎ ኅጢኣተነ

ኣሜን

ቅድመ መንበሩ ለእግዚእነ

ኣሜን

ለዘኣብልኣነ ዘንተ ኅብስተ

 

እስመ ለኣለም ምሕረቱ

 

ወለኣዝተየነ ዘንተ ጽዋዐ

 

እስመ ለኣለም ምሕረቱ

 

ወለዘሠርዐ ለነ ሲሳየነ ወዐራዘነ

 

እስመ ለኣለም ምሕረቱ

 

ወለዘተዓገሰ ለነ ኩሎ ኃጢኣተነ

 

እስመ ለኣለም ምሕረቱ

 

ወለዘወሀበነ ሥጋሁ ቅዱሰ ወደሞ ክቡረ

 

እስመ ለኣለም ምሕረቱ

 

ወለዘኣብጽሓነ እስከ ዛቲ ሰዓት ነሀብ ሎቱ ስብሓተ ውኣኰቴተ ለእግዚኣብሔር ልኡል ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር ይትኣኰት ወይሰባሕ ስሙ ለእዚኣብሔር ኣምላክነ ወትረ በክሉ ጊዜ ወበኩሉ ሰዓት።

 ፱. እናታችን ማርያም ሆይ ሰላም ለአንቺ ይሁን እያልን እንሰግድልሻለን እንማልድሻለን። ከአዳኝ አውሬ ታድኝን ዘንድ ተማጽነንብሻል። ስለ እናትሽ ስለ ሐና ብለሽ ስለ አባትሽ ስለ ኢያቄም ብለሽ ድንግል ማኅበራችንን ዛሬ ባርኪልን።

*** ሰላም ለኪ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ ማርያም እምነ ናስተበቁዐኪ። እምኣርዌ ንኣዊ ተማኅጸነ ብኪ። በእንተ ሓና ኢምኪ ወኢያቄም ኣቡኪ ማኅበረነ ዮም ድንግል ባርኪ።

፲. አምላክን በድንግልና የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ጸሎት ማርያምም አለች ነፍሴ እግዚአብሔርን ታላቅ ታደርገዋለች መንፈሴም በመድኃኒቴ በእግዚአብሔር ደስ ይላታል የባሪያዪቱን መዋረድ አይቷልና። እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ያመሰግኑኛል እርሱ ብርቱ የሚሆን ታላቅ ሥራን ለእኔ አድርጓልና። ስሙም ቅዱስ ነው ለሚፈሩትም ምሕረቱ ለልጅ ልጅ ነው ኃይልን በክንዱ አደረገ። በልባቸው አሳብ የሚኮሩ ትዕቢተኞችን በታተናቸው፤ ብርቱዎችንም ከዙፋናቸው አዋረዳቸው የተዋረዱትንም ከፍ ከፍ አደረጋቸው፤የተራቡትንም በቸርነቱ አጠገባቸው፤ ባለጠጎችንም ባዶ እጃቸውን ሰደዳቸው። ምሕረቱን እንዲያስብ እስራኤል ባርያውን ተቀበለ። ለአባቶቻችን ለአብርሃምና ለዘሩም እስከ ዘላለሙ ድረስ እንደተናገረ።

*** ጸሎት እግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ ኣምላክ።ታዐብዮ ነብስየ ለእግዚኣብሔር። ወትትኃሠይ መንፈስየ በኣምላኪየ ወመድኃንየ፤ እስመርእየ ሕማማ ለኣመቱ። ናሁ እምይእዜሰ ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትዉልድ። እስመ ገብረ ሊተ ኃይለ ዐቢያተ ወቅዱስ ስሙ። ወሣህሉኒ ለትውልድ ትዉልድ ለእለ ይፈርህዎ። ወገብረ ኃይለ በመዝራዕቱ፡ ወዘረዎሙ ለእለ ያዐብዩ ሕሊና ልቦም፡ ወነሠቶሙ ለኃያላን እመ ናብርቲሆሙ። ኣዕበዩሙ ለትሑታን፡ ወኣጽገቦም እምበረከቱ ለርኁባን፡ ወፈነዎሙ ዕራቆሙ ለብዑላን ወተወክፎ ለእስራኤል ቍልዔሁ፡ ወተዘከረ ሣህሎ ዘይቤሎም ለኣበዊነ ለኣብርሃም ወለዘርኡ እስከ ለዓለም።ሉቃስ ፩፡፵፮-፶፭ (1.46:55) ።

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top