መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ ማነው? እዚህ በመጫን ያንብቡ

መንፈስ ቅዱስ

ይህ መንፈስ ቅዱስ የሚለው ስም ለዘላለም ከአብና ከወልድ ጋር የነበረ ፣ ያለና የሚኖር የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የህላዌ ( የአነዋወር ) ስሙ ነው ፤ ይህ ስም ከእርሱ በስተቀር ለማንም አይሰጥም ፤ ከእርሱ ውጭ ማንም በዚህ ስም አይጠራም ።
መንፈስ ቅዱስ በግሪክ ፓራክሊቶስ ተብሎ ይጠራል ትርጎሙም ፦
መንፅሂ [ የሚያነፃ ]
መፅንኢ [ የሚያፀና ]
ናዛዚ [ የሚያረጋጋ ]
ከሣቲ [ ሚስጢር የሚገልፅ ]
መስተፈስሂ [ የሚያስደስት ]
መስተሰርይ [ ኃጢአትን የሚያስተሰርይ ] ማለት ነው ።
የመንፈስ ቅዱስ ስሞች በመጽሐፍ ቅዱስ
መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ስሞች ይጠራል ፦
  1. መንፈስ ተብሎ ይጠራል ። ዮሐ 1 : 32
  2. የእግዚአብሔር መንፈስ ተብሎ ይጠራል ። ሮሜ 8 : 14
  3. ቅዱስ መንፈስ ተብሎ ይጠራል ።መዝ 50 : 11 , መዝ 142 : 10
  4. የጌታ የክርስቶስ መንፈስ ተብሎ ይጠራል ። ሮሜ 8 : 9 , 2ኛ ቆሮ 3 : 17
  5. የእውነት መንፈስ ተብሎ ይጠራል ። ዮሐ 15 : 26
  6. አፅናኝ ተብሎ ይጠራል ። ዮሐ 14 : 26
መንፈስ ቅዱስ በምን በምን ተመስሏል ?
መንፈስ ቅዱስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በተለያዩ ነገሮች ተመስላል ፦
  1. በርግብ ተመስሏል ። ማቲ 3 : 16
  2. በንፋስ ተመስሏል ። ዮሐ 3 : 8
  3. በእሳት ተመስሏል ። ሐዋ 2 : 3, ማቲ 3 :11
  4. በእግዚአብሔር ጣት ተመስሏል ። ማቲ 12 : 28 , ሉቃ 11 : 20
  5. በአምላክ እስትንፋስ ተመስሏል ። ኢዮ 4 : 9
መንፈስ ቅዱስ የባሕሪ አምላክ ነው
መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር በአንድነት በሦስትነት የሚሰለስ ፣ የሚቀደስ ፣ የሚመለክ የባሕሪ አምላክ ነው ።
ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ላይ ከቅድስት ሥላሴ ሦስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ሕጹጽ [ ፍጡር ] ነው ብሎ የተነሳው መቅዶንዮስ የተባለው መናፍቅ ነው ፤ በዚህም ምክንያት በ381 ዓ.ም ከዓለም አብያተ ክርስቲያናት የተሰበሰቡ 150 የሚያለህሉ ሊቃውንት በቁስጥንጥንያ ተሰብስበው በተደረገው ጉባኤ የመንፈስ ቅዱስን ፈጣሪነትና የባሐሪ አምላክነት ከመጽሐፍ ቅዱስ እየጠቀሱ አፉን ቢያሲዙትም በክህደቱ ጸንቶ አልመለስ ቢል አውግዘው ከቤተ ክርስቲያን ለይተውታል ።
መንፈስ ቅዱስ የሚታየውንና የማይታየውን ዓለማት ሁሉ የፈጠረ ፣ ሁሉን ቻይ ኤልሻዳይ አምላክ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ ይመሰክራል ።
ልበ አምላክ የተባለው ቅዱስ ዳዊት በመዝሙሩ ” ፊትህን ስትሰውር ይደነግጣሉ ፤ ነፍሳቸውን ታወጣለህ ይሞታሉም፥ ወደ አፈራቸውም ይመለሳሉ ፣ መንፈስህን ትልካለህ ይፈጠራሉም ” መዝ104 : 29 – 30 ሲል የመንፈስ ቅዱስን ፈጣሪ አምላክነት ይመሰክራል ።
ጻድቁ ኢዮብም ” የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ። ” ይላል ኢዮ 33 : 4 , ኢዮ 32 : 8
ወዳጄ እዚህ ላይ የመንፈስ ቅዱስን ፈጣሪነትና የባሕሪ አምላክነት የሚያረጋግጡልህን ሁለት ነጥቦችን ማስተዋል ትችላለህ ይኸውም ፦
1ኛ. ” የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ” የሚለው ቃል በማያሻማና በግልጽ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን ፈጣሪነት ይመሰክራል ፤ መፍጠር ማለት አንድን ነገር ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ ማስገኝት ማለት ነው ፤ ይሄ ስልጣን ያለው እግዚአብሔር ብቻ ነው ፤ እግዚአብሔር ለቅዱሳኑ የፀጋ አምላክነት ክብርን እስከ መስጠት ደርሶ ቢያልቃቸው ቢያገናቸውና ቢያከብራቸውም ፤ እነሱም ፈጣሪያቸው በሰጣቸው የአምላክነት ፀጋ እፁብ ድንቅ ተአምራትን መስራትና ማድረግ ቢችሉም ነገር ግን መፍጠር አይችሉም ምክንያቱም ከሱ ውጭ ፈጣሪ ( አስገኚ ) የለምና ፤ መፍጠር የእርሱ ብቻ የባሕሪ ገንዘቡ ነው ። ” ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም።” እንዳለ ዮሐ1 : 3
መንፈስ ቅዱስ ፈጣሪ ባይሆንና ፈጡር ቢሆን ኖሮ ፤ ” የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ ” ተብሎ ባልተጻፈም ነበር ? ይልቅስ ይሄ የሚያስረዳህ የመንፈስ ቅዱስን ፈጣሪ አምላክነት ነው ።
 
2ኛ. ” ሁሉን የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ” የሚለው ቃል የመንፈስ ቅዱስን ፈጣሪነት ያረጋግጣል እንዴት ? ካልክ እስቲ እነዚህን ስሞች ተመልከት ፦
ኤል [ ኃያል አምላክ ]
ኤሎሂም [ የአማልክት አምላክ ]
ያህዌ [ የነበረ ያለና የሚኖር ]
ኤልሻዳይ [ ሁሉን የሚችል ]
የሚባሉት እነዚህ ስሞች የእግዚአብሔር የባሕሪ ስሞች ናቸው ፤ አምላክነት የባሕሪው የሆነ ኃያል አምላክ እርሱ ብቻ ነውና ፤ የአማልክት አምላካቸው የሆነ እርሱ ብቻ ነውና ፤ ዓለም ሳይፈጠር የነበረ ፣ አሁንም ያለ በስልጣኑ ዓለምንም አሳልፎ የሚኖር እርሱ ብቻ ነውና ፤ ምንም የሚሳነው ነገር የሌለ ፣ የወደደውንና የፈቀደውን በስልጣኑ ማረግ የሚችል እርሱ ብቻ ነውና፤ እነዚህ ስሞች ከእርሱ
ውጭ ለማንም አይሰጡም ፤ ፍጡር በነዚህ ስሞች አይጠራም ፤ መንፈስ ቅዱስ ግን ሁሉን የሚችል ምንም የሚሳነው ነገር የሌለ ኤልሻዳይ አምላክ ነውና ” ሁሉን የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ” ተብሎ ሲጠራ ታያለህ ።
ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም የመንፈስ ቅዱስን የባሕሪ አምላክነት ሲመሰክር
” መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ….
ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር ለእግዚአብሔር ያለውን ማንም አያውቅም። ” በማለት ተናግሯል 1ኛ. ቆሮ 2 : 10 – 11
የእግዚአብሔር ባሕሪ ማን ሊመረምረው ይቻለዋል ? ማንስ ያውቀዋል ? የባሕሪ ሕይወቱ የሕይወት እስትንፋሱ ከሆነ ካንዱ ከመንፈስ ቅዱስ በቀር ? ፍጡር አንኳን የእግዚአብሔር ባሕሪ ሊመረምርና ሊያውቅ ቀርቶ መቼ የራሱን ባሕሪ ያውቅና ? እስኪ ልጠይቅህ አንተ ከተፈጠርክት ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ ውስጥ
” ንፋስን መስፈር ” ፤ ” እሳትን መዘዘን ” የሚቻለው ከእኛ ውስጥ ከቶ ማነው ? አንተ ሰነፍ የተፈጠርክበትን የንፋስና
የእሳትን ባሕሪ እንኳን በቅጡ መርምረህ የማታውቅ ደካማ ሆነህ ሳለ ፤ ከንፋስና ከእሳት ባሕሪ እጅግ የሚረቀውን የእግዚአብሔርን ባሕሪ እንደምን መመርመር ይቻልሃል ? ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለ የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር እና ሁሉን መመርመርና ማወቅ ከሚቻለው ካንዱ ከእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በቀር ? ይህም የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የባሕሪ አምላክነትና
አዋቂነት የሚያረጋግጥ ነው ።
 
ካንዱ ከእግዚአብሔር በቀር በሁሉ ቦታ መገኝት የሚችል [ ምልዑ በኩለሄ ] የሆነና እርሱ የማይደርስበት እርሱ የሌለበት ቦታ የሌለ ከቶ ማን አለ ? ቅዱሳን ሰዎች ብትል የሚጨበጥ የሚዳሰስና ውሱን የሆነ አካል አላቸው ፤ ቅዱሳን መላእክት ብትል የማይጨበጥና የማይዳሰስ ነገር ግን ውሱን የሆነ አካል አላቸው ፤ ፍጡራን በባሕሪያቸው ውሱንነት አለባቸው ፤ ዳሩ ግን ልትስተው የማይገባህ እውነት እግዚአብሔር ለቅዱሳን ሰዎችም ሆነ ለቅዱሳን መላእክት በቦታ የማይወሰኑበትንና በእውቀት የማይገደቡበትን ፀጋ ( በሁሉ ቦታ የሚደረገውን የሚያውቁበት ጥበብና ፀጋ ) መስጠቱን ነው ። ይህን እዚህ ጋር ብናየው ደስ ባለኝ ነበር ነገር ግን ከርእሳችን እንዳንወጣ ወደተነሳንበት እንመለስ ፤ መንፈስ ቅዱስ ግን የባሕሪ አምላክ ነውና በምልአት በስፋት በሁሉ ቦታ ይገኛል እርሱ የሌለበት ቦታ የለም ከእርሱ ፊት ተሸሽጎ መሰወረ አይቻልም መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት
” ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ አለህ። ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች። ” እንዳለ መዝ 139 : 7 – 10
ይሄ የእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የባሕሪ አምላክነት የሚያረጋግጥ ነው ።
 
ሐናንያ ከሚስቱ ከሰጲራ ጋር መሬታቸውን ሸጠው ፤ ግማሹን ደብቆ ግማሹን ይዞ ወደ ሐዋርያት በመጣ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ “መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?
….. እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው። ” ይላል ሐዋ 5 : 3 – 5 ታያለህ ቅዱስ ጴጥሮስ ሐናንያን በገሰጸው ጊዜ [ መንፈስ ቅዱስን ታታልላለህ ? ] ካለው በኃላ ያ ያታለለው መንፈስ ቅዱስ ደግሞ ማን እንደሆነ ሲገልጽለት [ እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም ] ሲለው ?
ሲጀምር መንፈስ ቅዱስን አታለልክ አለ ሲጨርስ እግዚአብሔርን ዋሸህ አለ ፤ ይሄም መንፈስ ቅዱስ ራሱ እግዚአብሔር እንደሆነና እግዚአብሔር በሚለው ስም እንደሚጠራ የምታረጋግጥበት የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ነው። እግዚአብሔር የሚለው ስም የአብም የወልድም የመንፈስ ቅዱስም የጋራ መጠሪያ ስማቸው መሆኑን አትዘንጋ ።
 
መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር የተካከ የባሕሪ አምላክና ፈጣሪ ባይሆን ኖሮ ? ጌታ ሐዋርያትን ” እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው ። ” ማቴ 28 :19 – 20 ብሎ ያዛቸው ነበር ? ሰው በፈጣሪ ስም እንጂ በፍጡር ስም አይጠመቅም ፤ መንፈስ ቅዱስ ፍጡር ቢሆን ኖሮ ጌታ ሐዋርያትን በመንፈስ ቅዱስ ስም እንዲያጠምቁ ፤ እኛም በእርሱ ስም እንድንጠመቅ ባላዘዘም ነበር ዳሩ ግን መንፈስ ቅዱስ የባሕሪ አምላክ ነውና ጌታ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ባንድነት ፤ ልጅነት የምናገኝባትን አንዲት ጥምቀት እንጠመቅ ዘንድ አዘዘ ።
 
ወዳጄ ብዙ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ ስታነብ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ ጋር ባንድነት አብሮ ሲገለጽ ማቲ 3 : 16 ፤
ስሙ ከአብና ከወልድ ጋር አብሮ በአንድነት ሲጠቀስ ታያለህ ፤ ቅዱስ ጳውሎስ ” የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ፣ የእግዚአብሔርም ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ፣ ከሁላችሁ ጋር ይሁን። ” እያለ ይጠቅስ ያስተምርና ይሰብክ እንደ ነበር ። 2ኛ ቆሮ 13 : 14 ይሄ በግልጽ መንፈስ ቅዱስ ከአብና ከወልድ የማይለይ የባሕሪ አምላክና ፈጣሪ መሆኑን ያስረዳል ።
አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ፤ ምንም እንኳን በስም በግብርና በአካል ሦስትነት ቢኖረውም ፤ በአምላክነትና በፈጣሪነት ግን አንድ ነውና አንድ አምላክ እንጂ ሦስት አምላክ አንድ ፈጣሪ እንጂ ሦስት ፈጣሪ አይባልም ።
 
መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረፀ ነው
 በሚስጢረ ሥላሴ ትምህርት እንደሚታወቀው አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ብለን ከምንጠራቸው ከሦስቱ አካላት ሦስተኛው አካል መንፈስ ቅዱስ ነው ፤ የሚታወቀውም በተለየ ግብሩ ሠራፂ በመባል ነው ፤ ሠራፂ የሚለው ቃል
ሠረፀ ከሚለው የግዕዝ ግሥ የወጣ ሲሆን ሠረፀ ማለት ወጣ ፣ ተገኝ ማለት ነው ፤ ሠራፂ ሲል ደግሞ የሚወጣ ፣ ወጪ ማለት ነው ።
የእግዚአብሔር ቃል መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳው መንፈስ ቅዱስ የሠረፀው ( የወጣው ) ከአብ ብቻ ነው ነገር ግን ካቶሊኮች መንፈስ ቅዱስ የሠረፀው ከአብና ከወልድ ነው ይላሉ ይህ ግን ፍፁም ስህተት ነው ። ጌታ ሐዋርያትን ” እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም [ ከአብ የሚወጣ] የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል ” ዮሐ 15 : 26 እንጂ ያላቸው ከእኔና ከአብ የሚወጣውን አላለም ፤ እነዚህ የተጻፈውን ትተው ያልተጻፈ የሚያነቡ ቃሉ የሚለውን ሳይሆን ምኞታቸውን በመሰለኝ የሚነግሩህ ደፋሮች ናቸውና አትስማቸው ጴጥሮስ እንዳለ ” ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።” ሐዋር 5 : 29
አንዳንድ ቦታ ላይ መንፈስ ቅዱስ
[ የልጁ መንፈስ ] [ የጌታ የክርስቶስ መንፈስ ] ስለተባለ ከወልድም የሠረፀ ነው ለማለት ይሞክራሉ ፤ ይሄ ግን መንፈስ ቅዱስ የወልድ ( የክርስቶስ )የባሕሪ ሕይወቱ ( እስትንፋሱ ) መሆኑን የሚገልጽ አንጂ ከወልድም የሠረፀ መሆኑን የሚገልጽ አይደለም ።
 
መንፈስ ቅዱስ የራሱ አካል አለው
አንዳንድ መናፍቃን መንፈስ ቅዱስ አካላዊ መንፈስ ሳይሆን እንደ እሳት ሙቀት ያለ የእግዚአብሔር ኃይል ነው ይላሉ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ እንደዚህ አይልም ።
መንፈስ ቅዱስ እንደ አብና እንደ ወልድ የራሱ የሆነ ፍፁም ገፅ ፣ ፍፁም መልክና ፍፁም አካል ያለው አካላዊ መንፈስ ነው ፤ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ አካል አለው ማለት እንደ ሰው የሚጨበጥና የሚዳሰስ አካል አለው ማለታችን አይደለም ፤ መንፈስ ሥጋና አጥንት የለውምና ዮሐ 4 : 24 , ሉቃ 24 : 36 – 43 ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ የማይጨበጥ የማይዳሰስና በሁሉ ቦታ የመላ ( ሙሉእ በኩለሄ ) የሆነ እረቂ አካል ነው ያለው ።
ጌታ ” አብ በስሜ [ የሚልከው ] ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ [ እርሱ ] ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።” ዮሐ14 : 26 ሲል መናገሩ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ መንፈስ መሆኑን ያስረዳል ፤ በተለይ ☞
[ የሚልከው ] እና ☞ [ እርሱ ] የሚሉት ሁለት ቃላት መንፈስ ቅዱስ አካላዊ መንፈስ መሆኑን ያረጋግጣሉ ምክንያቱም አካላዊ ያልሆነ ነገር እንዴት ሊላክ ይችላል ? እንዴትስ ከሌላው ተለይቶ ” እርሱ ” ሊባል ይችላል ? ይሄ የሚያረጋግጠው መንፈስ ቅዱስ አካላዊ መንፈስ መሆኑን ነው ።
ጌታ በተጠመቀ ጊዜ አብ በተለየ አካሉ ከሰማይ ሆኖ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው የምወልደው ልጄ ይህ ነው እረሱን ስሙት ማለቱ ፤ ወልድ በተለየ አካሉ በዮርዳኖስ መጠመቁና መንፈስ ቅዱስ ደግሞ በተለየ አካሉ በርግብ አምሳል ተገልጾ በእርሱ ላይ መውረዱ የምናመልከው አንዱ እግዚአብሔር በስም ሦስት ፤ በግብር ( በሥራ ) ሦስት ፤ በአካል ሦስት መሆኑን በዚህ መረጋገጥ ትችላለህ ። ማቲ 3 : 16
 
የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ
ወዳጄ ጸጋ ማለት ነፃ ስጦታ ማለት ነው ፤ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የማይሰፈር የማይቆጠር የማይለካ የጌትነት የቸርነት ሥራውን የሰራልንና ጸጋውን የሰጠን ፤ ዋጋ ከፍለነው ሳይሆን እንዲሁ በነፃ ነው፣ እንክፈልስ ብንል ምን አለንና ምን እንከፍለዋለን ? እኛ ” ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትንም ” አይደለንምን ? ራዕ 3 : 17
ቃሉ ” በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።” ማቴ10 : 8 እንደሚል ዋጋ ሳንከፍል በከንቱ ( በነፃ ) በተቀበልነው ፀጋ ከሰው ዋጋ ሳንጠብቅና ሳንቀበል በነፃ ልናገለግልበት አይገባንምን ?
መንፈስ ቅዱስ ከሦስቱ አካላት አንዱ ሲሆን ጸጋው ግን እጅግ ብዙ ነው።መንፈስ ቅዱስ በልዩ ጸጋ የተለያየ መንፈሳዊ ስጦታ ለተለያዩ አገልጋዮች እንደሚሰጥ የመንፈስ ቅዱስን ጸጋ ኢሳይያስ እንዲህ ሲል ይዘረዝረዋል ኢሳ.11:1 – 3 “የእግዚአብሔር መንፈስ፥የጥበብና የማስተዋልመንፈስ፥የምክርና የኃይል መንፈስ፥የእውቀትና እግዚአብሔርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል።”
 ብርሃነ ዓለም ጳውሎስ ደግሞ “የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው (አካሉ አንድ ሲሆን ስጦታው የበዛ ነው ማለቱ ነው) ለእያንዳንዱ በመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው ስጦታው ልዩ ልዩ ነውና ለሁሉም ጌታ እየረዳ እንደ ዕድሉ ይሰጠዋል ለእያንዳንዱ እንደሚገባውና እንደሚጠቅመው በግልጥ ይሰጠዋል የጥበብ ቃል የሚሰጠው አለው በመንፈስ ቅዱስም የዕውቀት ቃልን የሚሰጠው አለው በመንፈስ ቅዱስ ሃይማኖትን የሚሰጠው አለው ድውይን የመፈወስ ሥልጣንም የሚሰጠው አለው የእርዳታና የኃይል ሥራን የሚሰጠው አለው ትንቢት መናገርን የሚሰጠው አለው በመንፈስ ቅዱስ ትርጎሜ ማወቅን የሚሰጠው አለው የየአገሩን ቋንቋ እንዲያውቅ ትርጎሜውን የሚሰጠው አለው:: በዚህ ሁሉ ሁሉንም የሚረዳቸው መንፈስ ቅዱስ አንድ ነው ነገር ግን ለሁሉም እንደወደደ ያድላቸዋል”
 1ኛቆሮ12:4-11 “ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር (ማወቅ) ይሰጠዋል፥ለአንዱም ትንቢትን መናገር፥ለአንዱም መናፍስትን መለየት፥ለአንዱም በልዩ ዓይነት ልሳን(ቋንቋ) መናገር፥ለአንዱም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤ይህን ሁሉ ግን ያ አንዱ መንፈስ እንደ ሚፈቅድለ እያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።”
 
ቅዱሳን ሐዋርያትና አርደት መንፈስቅዱስ ስላደረባቸው ልዩ ልዩ ሕሙማንን የመፈወስ ኀይል : ርኩሳን መናፍስትን ከልዩ ልዩ በሽተኞች ላይ የማስወጣት ሥልጣን: ሙታንን ለማስነሣት የሚያስችል አሰደናቂ ኃይል ተሰጣቸው:: ቅዱሳን ሐዋርያትና ተከታዮቻቸው አርድእት የሰዎችን ኃጢአት ለማስተረይና ይቅር ለማለት የሚያስችል ሥልጣነ ክህነትያገኙት መንፈስ ቅዱሳን ስለተቀበሉ ነው(ዮሐ.20 : 21-23 ; የሐዋ.20:28)
 መንፈስ ቅዱስ መከፈል ሳይኖርበት:በአብና በወልድ በራሱም ፈቅድ ልዩ ልዩ ጸጋውን ለተለያዩ ሰዎች ሲያድል: እርሱ ራሱ እንደማይከፈልና ሀብቱም እንደማያልቅበት ቅዱስ ባሳልዩስ ዘቂሳርያ ሲመሰክር እንዲህ ብሎአል:: “እንደ ሚሰጣቸው እንደ ሀብቱ መጠን ከእርሱ ይቀበሉ ዘንድ ከእነርሱም አንዱ (እያንዳንዱን) የበቁ ያደርጋቸዋል:ሀብቱም ሁሉ ከእርሱ ከራሱ ይሰጣል: ከእርሱም ስለ ተሰጠው ለእርሱ ምንም ምን አይጎድለውም: እርሱ መቼም መች (ምንጊዜም) ሕፀፅ (ጉድለት) የለበትምና።ፀሐይ በሰው ሁሉ ላይ ሰለተስጠው ሙቀት ብርሃን ምንም ምን እንዳይጎድለው መንፈ ስቅዱስም እንዲሁ በፍጥረት ሁሉ ላይ ሀብቱን ያሳድራል:ነገር ግን አይጎድልበትም:አይከፈልም”(ሃይማኖተአበውግጽ 114-115 ቁ. 47-48)።
 
በተጨማሪም ይህ ቅዱስ አባት ስለ መንፈስ ቅዱስ ሥራ ከጻፈው መልእክት እጅግ ጠቃሚ የሆነውን ክፍል ከዚህ ቀጥለን ጠቅሰነዋል። “ሕያው እግዚአብሔር በማሳወቅ ሁሉን አዋቂ ያደርጋል።በነቢያት ቃል ትንቢትን ይናገራል: በሕግ ጸንተው ላሉ ጥበብን ይገልጣል: ካህናትን ጻድቃን ያደርጋቸዋል: ለነገስታት ኃይልን ይሰጣል: መከራውንም ለሚታገሱ ትእግስትን ይሰጣል:እውነተኛ ሀብትን: ልጅነትን ( የጸጋልጅነትን) ያድላል: ሙታንን ያስነሳል:እስረኞችን ይፈታቸዋል: ከኃጢአት ከጣዖት የተለዩትን በጥምቀት ዳግመኛ እንሲወለዱ (የእግዚአብሔር ልጆች እንዲሆኑ) ያደርጋቸዋል: በእኒህና በሚመስላቸውም ላይ ይህን ያደርጋል”(ሃይማኖተ አበው ገጽ 115 ቁ. 49-50)።
 መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸ ሰዎች : ታጋሾች: ሃይማኖቶች : ፍቅርን መጽዋትን የሚወዱ : ጸሎተኞች ርኅሩሆች ናቸው።ምክነያቱም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳለው። ገላ. 5:22-23 “የመንፈስ ቅዱስ ፍሬዎች ፍቅር ደስታ ሰላም ትዕግስት ቸርነት በጎነት እምነት የዋህነ ትራስን መግዛት ናቸውና።”
 ቅዱሳን ነቢያት ትንቢት ሊናገሩ የቻሉት መንፈስ ቅዱስስላደረባቸው ነው።ቅዱሳት መጻሕፍት የተጻፉት የእግዚአብሔር መልእክተኞች በሆኑ መንፈስ ቅዱስ ባደረባቸው ሰዎች ነው(1ኛጴጥ.1 : 20 – 21)።ምስጢራተ ቤተክርስቲያንን የሚቀድስ መንፈስ ቅዱስ ነው።ማንኝያውም ሰው ከውኃና ከመንፈስ ቅዱስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት ሊገባ አይችልም( ዩሐ. 3:5)።ዩሐንስ መጥምቁ ለንሰሐ በውኃ ያጠምቅ ነበር(ማቴ. 3:11)።ጌታችን ግን በመንፈስ ቅዱስና በእሳት ያጠምቃል(ማቴ. 3:11-12 : ዩሐ. 1: 32-34)።
መንፈስ ቅዱስ አካሉ አንድ ነው ጸጋው [ ሐብቱ ] ግን ብዙ ነው
” የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው ” እንዳለ 1ኛ ቆሮ 12 : 4
ወዳጄ አስተውል ለእኛ ለእያንዳንዳችን የሚሰጠንና የሚያድርብን የመንፈስ ቅዱስ ጸጋው አንጂ አካሉ አይደለም ፤ መንፈስ ቅዱስ በአካሉ ተከፍሎ ሳይኖርበት ጸጋው እስከ እለተ ምፅአት ድረስ ለሰው ልጆች ሲሰጥ ይኖራል ።
መንፈስቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ ነው
 
መንፈስ ቅዱስ ዝርው ኃይል አይደለም:: እንደ አብና እንደ ወልድ ፍጹም አካል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክዕ ያለው ነው:: እኔ ማለት የሚችል ነው:: መንፈስ ተብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለተጠራ አካል የለውም የሚለው አባባል ከደካማ አስተሳሰብ የመነጨ ነው::መጽሓፍ ቅዱስ “እግዚአብሔር መንፈስ ነው” ዮሃ 4:24:: ማለቱ አካል የለውም ማለቱ እንዳልሆነ ሁሉ መንፈስ ቅዱስንም መንፈስ ብሎ መጥራቱ አካል የሌለው ለማለት አይደለም:: እግዚአብሄር አካል ያለው ሲሆን ነገር ግን እንደ ፍጡራን ውሱን አይደለም:: እግዚአብሔር በዓለምና ከዓለም ውጭ ያለ የሌለበት ቦታ የሌለ ምሉዕ ስፍህ ነው::ለዚህም የልበ አምላክ የዳዊትን አባባል ብቻ መጥቀሱ በቂ ነው:: “ሰማየ ሰማያት ብወጣ አንተ በዚያ አለህ ወደ ባህር ብጠልቅ አንተ በዚያ አለህ የሌለህበት ቦታ የለም”እግዚአብሔር የሚከፋፈልና የሚበታተን አካል ያለው አይደለም ነገር ግን በፍጹም መለኮት እሱው ራሱ በኁሉም ቦታ ይገኛል::
 
በተጨማሪም “ከአብ በሠረጸ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ በሚሆን እንደ አብ እንደ ወልድ ፍጹም አካል ባለው በመንፈስ ቅዱስም እናምናለን::እንዲሁም በአካሉ በገጹ ጸንቶ ያለ ነው”14 በማለት ቅዱሳን አበው መጽሐፍ ቅዱስን ዋቢ አድርገው ያስረዳሉ:: መንፈስ ቅዱስ አካላዊ እስትንፋስ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚከተለው ያስረዳናል::ኦሪት ዘፍ18:1 :-በሰው አምሳል ከተገለጡት ከሦስቱ አካላት አንዱ መንፈስ ቅዱስ ነው ማቴ 3:16 :-…የእግዚአብሔር መንፈስ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ሲቀመጥ አየ” የእግዚአብሔር መንፈስ የተባለው መንፈስ ቅዱስ ለመሆኑ የሚያጠራጥር ነገር አይኖርም:: እንግዲህ በርግብ አምሳል መውረዱ ዝርው ኃይል ሳይሆን አካላዊ መሆኑን ሊያስገነዝበን ነው:: ብትን ሃይል ቢሆን ኖሮማ በርግብ አምሳል ወርዶ በራሱ ላይ ባልተቀመጠ ነበር::
ዮሃ 14:16 “እኔም አብን እለምነዋለሁ ጰራቅሊጦስንም ሌላውን አካል ይልክላችሁአል ለዘላለም ከእናንተ ጋር ይኖር ዘንድ” በአዳዲስ እትሞች ላይ ጰራቅሊጦስ የሚለው ሌላ አጽናኝ በሚለውተ ተክቶል ሌላውን አካል የሚለው እርሱም በሚለው ተተክቶል:: ይህም ቢሆን የመንፈስ ቅዱስን አካላዊነት የሚያስተባብል አይደለም::ሌላ አጽናኝ ሲል ፍጹም ገጽ ፍጹም መልክዕ ያለው ልዩ አካል መሆኑን የሚያስገነዝብ ሲሆን ሌላ ሲል ከአብና ከወልድ የተለየ ሦስተኛ አካል ማለቱ ነው::እርሱም የሚለው አባባልም ከአብና ከውልድ በተለየ አካል ያለ ልዩ በአካላት ሦስት ከሆኑት አንዱ እኔ ባይ አካል መኖሩን የሚገልጽ ነው::
“ነገር ግን አብ በስሜ የሚልክላችሁ የእውነት መንፈስ ጰራቅሊጦስ እርሱ ሁሉን ያስተምራችሁአል እኔ የነገርኩአችሁንም ሁሉ ያሳስባችሁአል” ከዚህ የምንረዳው መንፈስ ቅዱስ የእውነት አስተማሪና መሪ እንደሆነ ነው እንግዲህ ብትን ኃይል ሁሉን ማስተማር ይቻላል? ማሳሰብስ ይቻለዋል? መናገርስ ይቻለዋል? በእዚሁ በዮሃንስ ወንጌል 16:13 “…..ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኃል” ተብሎ እንደተገለጸው መንገድ ማሳየት መምራት ይቻለዋል? እርሱ ተብሎስ ብትን ለሆነ ኃይል ይነገራል? በፍጹም:: አካል የሌለው እስትንፋስ ወይም መንፈስ እርሱ ተብሎ አይጠራም:: ወደ እውነትም አይመራም መናገርም አይቻልም መንፈስ ቅዱስ ግን አካላዊ እስትንፋስ ስለሆነ ከላይ የተጠቀሰው ሁሉ ሊነገርለት ተችሎዋል::ኢሳ 48:16 “…… አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።”
በዚህ ላይ እግዚአብሔር ብሎ አብን መንፈስ ብሎ መንፈስ ቅዱስን ማመልከቱ ነው: እንግዲህ መንፈስ ቅዱስ በአብ ውስጥ የተከማቸ ብትን ኃይል ነው ከተባለ ወልድን እንዴት ሊልክ ቻለ? መላክስ ይቻለዋል? ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ ነው ያለው እንጂ መቼ መንፈስ ቅዱስ አለ እንዳይባል:: እግዚአብሔር ብሎ እና በሚለው ቃል በማያያዝ ሌላ አካል እንዳለም ገለጸ እንጂ የእግዚአብሔር መንፈስ ብሎ አንድ አካል ብቻ አድርጎ አላቀረበም:: ልከውኛል የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሁለትነትን እንጂ አንድነትን አይደለም:: ተጨማሪ የመጽሐፍ ቅዱስ ማስረጃ ዘፍ 6:3 “እግዚአብሔርም፦መንፈሴ በሰው ላይ ለዘላለም አይኖርም፥እርሱ ሥጋ ነውና ዘመኖቹም መቶ ሀያ ዓመት ይሆናሉ አለ።” ዘፍ 18:1 “በቀትርም ጊዜ እርሱ በድንኳኑ ደጃፍ ተቀምጦ ሳለ እግዚአብሔር በመምሬ የአድባር ዛፍ ተገለጠለት።ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ወደ ምድርም ሰገደ፥እንዲህም አለ፦አቤቱ፥በፊትህስ ሞገስ አግኝቼ እንደሆነ ባሪያህን አትለፈኝ ብዬ እለምናለሁ
 ኢሳ 48:16 “ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።”ዮሐ 15:26 “ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥እርሱስ ለእኔ ይመሰክራል፤ዮሐ 16:8 “እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል።እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤እኔ ብሄድ ግን እርሱን እልክላችኋለሁ።እርሱም መጥቶ ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል” ሐዋ 5:3-4 ” ጴጥሮስም፦ሐናንያ ሆይ፥መንፈስ ቅዱስን ታታልልና ከመሬቱ ሽያጭ ታስቀር ዘንድ ሰይጣን በልብህ ስለ ምን ሞላ?ትሸጠው የአንተ አልነበረምን? ከሸጥኸውስ በኋላ በሥልጣንህ አልነበረምን? ይህን ነገር ስለምን በልብህ አሰብህ? እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አልዋሸህም አለው። 1ኛቆሮ 12:11 “ይህን ሁሉ ግን ያአንዱ መንፈስ እንደ ሚፈቅድ ለእያንዳንዱ ለብቻው እያካፈለ ያደርጋል።” 2ኛጴጥ 1:21 “በክርስቶስም ከእናንተ ጋር የሚያጸናንና የቀባን እግዚአብሔር ነው፥ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው።
የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ [ ሐብቱ ] ብዙ ሲሆን ነገር ግን በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሱት ጥቂቶቹ የመንፈስ ቅዱስ ፀጋዎች ፦
፨ ትንቢት የመናገር ጸጋ
፨ በልሳን የመናገር ጸጋ
፨ የማስተማር ጸጋ
፨ ጥበብን የመናገር ጸጋ
፨ እውቀትን የመናገር ጸጋ
፨ የመግለጥ ጸጋ
፨ የመተርጎም ጸጋ
፨ የመምከር ጸጋ
፨ የመዘመር ጸጋ
፨ የአገልግሎት ጸጋ
፨ የመፈወስ ፀጋ
፨ ተአምራት የማድረግ ጸጋ
፨ መናፍስትን የመለየት ፀጋ
፨ የጸሎት ፀጋ
፨ የትህትና ፀጋ
፨ የአክብሮት ጸጋ
፨ በልግስና የመስጠት ጸጋ
፨ እንግዳ የመቀበል ጸጋ
፨ የመተባበር ጸጋ
፨ በሥራ የመትጋት ጸጋ
፨ የመግዛት [ የማስተዳደር ] ጸጋ
፨ መከራን የመታገስ ጸጋ
፨ የመማር [ የይቅር ባይነት ] ጸጋ
፨ የማግባት ጸጋ
፨ በድንግልና የመኖር ጸጋ ….
ሮሜ 12 : 3 – 18 , 1ኛ ቆሮ 12 : 1 – 31 ,1ኛ. ቆሮ 7 : 7
” እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን” ሮሜ12 : 6 እንደተባለ ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ ከማህጸነ ዮርዳኖስ በጥምቀት የተወለደ ክርስቲያን ሁሉ ከመንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው የራሱ ጸጋ አለው ፤ ከዚያች ቀን ጀምሮ እርሱ የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ይሆናል ቃሉ ” የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?” እንደሚል 1ኛ ወደ ቆሮ 3 : 16
አንዳንዱ አምስትና ሁለት መክሊት እንደተሰጠው ታማኝ ባሪያ ነግዶ ያተርፍበታል ማለትም በተሰጠው ጸጋ ምግባር ትሩፋት ሰርቶ ጸጋውን ያበዛል ለቅድስና ለክብር ይበቃበታል ፤ አንዳንዱ አንድ መክሊት እንደተሰጠው ሐኬተኛና አመጸኛ ባሪያ ሳይነግድና ሳያተርፍበት መክሊቱን ቆፍሮ ይቀብራል ፤ ማለትም ጸጋውን ሳያውቀው ፣ ቢያውቀውም ምግባር ትሩፋት ሳይሰራበትና ለቅድስናና ለክበር ሳይበቃ ፤ የተሰጠውን ጸጋ በኃጢአትና በበደል ውስጥ ቀብሮና አዳፍኖ ይኖራል ፣ በዚህም ሰጪውን መንፈስ ቅዱስን ያሳዝናል ። ምህረቱንና ቸርነቱን አቃለን ፤ የትዕግስቱንም ባለጠግነት እንዳላዋቂነትና እንደሞኝነት ቆጥረን ፤ በበደላይ በደል በኃጠአት ላይ ኃጢአት ለምንሰራው ለእኛ እግዚአብሔር እንዲህ ይለናል ” ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ።” ኤፌሶን 4 : 30
 የመንፈሰ ቅዱስ ጸጋ ለሐዋርያት ሲወርድ ለምን በእሳት አምሳል ተገለጸ ?
እሳት ከቡላዱ ( ከመነሻው ) ሲወጣ ትንሽ [ በመጠን ] ነው ኃላ ግን በእንጨት እያቀጣጠሉ ያሰፉታል ያበዙታል ፤ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ በጥምቀት ሲሰጠን በመጠን ነው ኃላ ግን በሥራ ማለትም በምግባር በትሩፋት ስንበረታ ፀጋው እየሰፋ እየበዛልን ይሄዳልና ነው ።
 
መንፈስ ቅዱስን ምንም ብንበድለው የባሕሪ አምላክነቱንና ፈጣሪነቱን እስካልካድነው ድረስ ፈጽሞ ከእኛ ተለይቶንና ጥሎን አይሄድምና ከምንሰራው በደልና ኃጢአት በንስሐ ወደሱ ተመልሰን ፤ የበለጠውን የጸጋ ስጦታ ለማግኝት በብርቱ እንትጋ ።
ሶምሶንን ያነቃቃ መንፈስ ቅዱሰ ፤ ሐዋርያትን ያጸና መንፈስ ቅዱስ ፤ በርናባስንና ሳውልን ለአገልግሎት ለዩልኝ ያለ መንፈስ ቅዱስ ፤ የተማርነውን የሚያሳስበን መንፈስ ቅዱስ ፤የምንናገረውንም የሚሰጠን እርሱ መንፈስ ቅዱስ አይለየን ፤ እሱን እያመለክን በምንኖርባት በተዋህዶ ሃይማኖታችን ያጽናን አሜን ።

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top