፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ 81 ወይስ 66 ?

መጽሐፍ ቅዱስን ማን ጻፈው?

– – – – – – –

መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ ስምንት በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20

– – – – – – –

-+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር?

– መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡

– – – – – – –

-+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ?

-ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419 እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት

ተጀመረ::

– – – – – – –

-+- ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡

ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያናችን መጽሐፍ ቅዱስን ያገኘችው ከመጽሐፉ ጸሐፍት ከነቢያት ከሐዋርያት እና ከተከታዮቻቸው ነው፡፡ ለቁጥሩም ብዛት መጠየቅ የሚገባት እስዋ ብቻ ናት 81 ብለው ሰፍረው ቆጥረው ቅዱሳን ሐዋርያት ለቅዱስ ጴጥሮስ ደቀመዝሙር ለቅዱስ ቀሌምንጦንስ ሰጡት። እሱም ለተከታዮቹ ከዚያም ለሠለስቱ ምዕት እነሱም ሰፍረው ቆጥረው አስረከቡን፡፡ ቁጥራቸው 81 ለመሆኑ በመኃ.መኃ6፤8 ስድሳ ንግስታት ሰማንያ ቁባቶች ቁጥር የሌላቸውም ቆነጃጅት አሉ ብሎ ስድሳ ብሎ አንዱን ሰማንያ ብሎ ሰማንያውን ቅዱሳት መጻህፍት መንፈስ ቅዱስ ሲያናግረው ነው ብለው አበው እንዲህ በትርጓሜ አስቀምጠውልናል፡፡ ከዚህም ሌላ በፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 2 የሐዋርያት መጻሕፍት አብጥሊስ እና ትእዛዝ ሲኖዶስን ጠቅሶ ይዘረዝራቸዋል፡፡ የፕቴስታንቱ ዓለም ለምን 66 እንደሚቀበሉ ምክንያታቸው፤ ሐዋርያት እናንተ የምትቀበሉትን አልጠቀሱትም ነው የሚሉት፤ ቅዱሳን ሐዋርያት ግን እነሱ የማይቀበሉትን ቤተክርስቲያናችን ከቅዱሳን ሐዋርያቱ የተቀበለችውን መጽሐፈ ሄኖክን ጠቅሰውታል ይሁ1፤14 ሄኖክ 9፤3 እንዲሁም ተረፈ ኤርምያስን ተጠቅሶ እናገኘዋለን፡፡ ማቴ 27፤9 ባሮክ1፤3 ከዚህም ሌላ የመጽሐፈ ጦቢት የምጽዋት ትምህርትም በማቴ፤6 ላይ ተጠቅሶ ይገኛል፡፡

እነርሱ የሚቀበሏቸው ነገር ግን ሐዋርያት ለትምህርት ያልጠቀሷቸው ብዙ የቅዱሳት መጻህፍት ዓይነቶችም አሉ፤ ስለዚህ ይህ አባባላቸው ስህተት ነው፡፡

– በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-

ሀ. ከ ብ ሉ ይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):-

1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል

2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ

3.መጽሐፈ ጦቢት

4.መጽሐፈ ዮዲት

5.መጽሐፈ አስቴር

6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ

7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ

8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ

  1. መጽሐፈ ሲራክ

10.ጸሎተ ምናሴ

  1. ተረፈ ኤርሚያስ

  2. ሶስና.

  3. መጽሐፈ ባሮክ

  4. መጽሐፈ ጥበብ

  5. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ

  6. ተረፈ ዳንኤል

  7. መጽሐፈ ኩፋሌ

  8. መጽሐፈ ሄኖክ

– – – – – – –

ለ. ከሐዲስ ኪዳን:-

  1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ

  2. ግስው ሲኖዶስ

  3. አብጥሎ ሲኖዶስ

  4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ

  5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ

  6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ

  7. ቀለሚንጦስ

  8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81 መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡

– – – – – – –

-+- እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣

-መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡

– – – – – – –

-+- መጽሐፍ ቅዱስ በኢትዮጵያ፡-

– ብሉይ ኪዳን በሐገራችን ቋንቋ በግዕዝ የተተረጎመው ከክርስቶስ ልደት በፊት አንድ ሺህ ዓመት ቀደም ብሎ ሲሆን ይኸውም በንግሥተ ሳባ ዘመነ መንግሥት ጊዜ ነው፡፡

– ኢትዮጵያ ከዚህን ጊዜ ጀምሮ መጻሕፍትን ጠብቃ አቆይታለች፡፡ አባቶች ምንም አይነት ጦርነት ቢነሳ ህይወታቸውን በማስቀደም መጻሕፍትን ጠብቀው አቆይተውልናል፡፡

– ከምዕራባውያን በፊት ክርስትናን ሆነ የአይሁድ እምነትን የተቀበለችው ሀገራችን በምዕራባውያን የሌሉ መጻሐፍት መገኛ ብቸኛ ሀገር ናት፡፡ ለዚህም ነው በአይሁድ ዘንድ ሆነ በሮማውያን ዘንድ በነበረው ጦርነት የጠፉ መጻህፍት ኢትዮጵያ ውስጥ ግን የሚገኙት፡፡ ለዚህም መጽሐፈ ሄኖክ እና መጽሐፈ ኩፋሌ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የመጽሐፈ ሄኖክ ጥቅልል አሁን በቅርቡ በቁምራን ዋሻ ተገኝቷል፡፡ የተገኘው ጥቅልልም ሀገራችን ጠብቃ ካቆየችው መጽሐፈ ሄኖክ ጋር አንድ አይነት ሆኖ በመገኘቱ ምዕራባውያን ተርጉመው መጠቀም ጀምረዋል፡፡

– – – – – – –

-+- የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት:-

– የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ሁለት አይነት የቀኖና ክፍሎችን ያካትታል እነሱም ፕሮቶካኒካል እና ዲዩትሮካኖኒካል ይባላሉ፡፡

– (የመጀመሪያ)፡- እነዚህ መጻሕፍት የተሰበሰቡት በካህኑ እዝራ ሲሆን መጀመሪያ በቀኖና መጻሕፍትነት የተመዘገቡ ናቸው፡፡ 1ኛ. መቃብያን 2፡10

“ነህምያም የነገስትን መጻሕፍት የያዘ ቤተ መጻሕፍት አቋቁሞ ነበር“ እነዚህም መጻሕፍት በ ሶስት ይከፈላሉ እነሱም ቶራህ (አምስቱ ብሔረ ኦሪት) ፣

ነበኢም (ቀደምት ነብያት እና ደኃርት ነብያት) እና ከተቢም (ታላላቅ የታሪክ መጽሐፍትና ታናናሽ የታሪክ መጽሐፍትን ያካትታል) ተብለው ይጠራሉ፡፡

እንዲሁም

– ዲዩትሮካኖኒካል የምንላቸው አይሁድ እንደ ቀኖና መጻሕፍት የማይቀበሉዋቸው ግን እንደ አዋልድ መጻህፍት የሚቀበሉዋቸው ናቸው፡፡ በነገራችን ላይ 

-> አይሁዶች 24 የብሉይ ኪዳን መጻህፍትን ብቻ ሲቀበሉ (የመጽሐፋቸው አቆጣጠር ከእኛ አቆጣጠር ይለያል)

-> ፕሮቴስታንቶች 39 የብሉይ ኪዳን እንዲሁም 27 የሐዲስ ኪዳን ይቀበላሉ፡፡

-> ካቶሊኮች 46 የብሉይ ኪዳን መጻህፍት እና 27 የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት ሲቀበሉ እኛ

-> ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች ግን 46 የብሉይ ኪዳን እና 35 የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እንቀበላለን፡፡ (ከካቶሊኮች ጋር በብሉይ ኪዳን የምንቀበላቸው

መጻሕፍት ላይ የአቆጣጠር እና የመጻሕፍት ልዩነት አለ፡፡)

– እዚህ ላይ ከላይ በግልጽ እንደምንረዳው 81 የነበረው የመጀመሪያው መጽሐፍ ቅዱስ ብዛት ቀስ በቀስ በሰዎች እየተቀነሰ እንዲሁም በነበሩት ጦርነቶች መጻሐፍቱ እየጠፉ በመምጣታቸው፣ መጀመሪያ 73 እንዲሆን በመቀጠልም ማርቲን ሉተር ሲያምንበት ከነበረው የካቶሊክ እምነት ፣ከካቶሊክ መነኮሳት ጋር በነበረው የግል ጸብ እና የፖለቲካ ጸብ (የጀርመን ዜጋ ስለነበር የአይሁዶች ጥላቻ ስለነበረው) በነበረው ቅራኔ ምክንያት 7 መጻህፍትን በገዛ ፈቃዱ ቀንሶ ዛሬ በምዕራብውያን ዘንድ በስፋት የተስፋፋውን እና የእኛን ሐገር ጨምሮ በኢኮኖሚ እና በፖለቲካ ሀይል የሌላቸውን ሀገራት የተቆጣጠረውን የ66 መጻሐፍት ሊያስፋፋ ችሏል፡፡

– – – – – – –

።–> መናፍቃን 81 /ሰማንያ አሃዱ/ መጽሐፍ ቅዱስን የማይቀበሉባቸው ምክንያቶች እና እንዲቀበሉ የሚያስገድዳቸው ምክንያቶች እንዲሁም ከስልሣ

ስድስቱ ውጭ ሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት የሉም እንዳይሉ ማስረጃዎች፡-

-> ተቃዋሚዎች ከ66 ውጭ መጽሐፍ የለም ቢሉም ሐዋርያት ሆኑ ጌታ ከ81 መጻሐፍት እየጠቀሱ አስተምረዋል፡፡ ይህን እስቲ በማስረጃ

እንመልከተው፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 1. – ኢየሱስም ሊያስተምር ሲጀምር ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ያህል ሆኖት ነበር ይለናል ወንጌላዊው ቅዱስ ሉቃስ (ሉቃ.3፡3) – እንግዲህ ጌታችን

አምላካችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከ30 ዓመቱ በፊት የት ነበረ? ምን እየሰራ ነበረ? ብልን ስንጠይቅ መልሱን በ66 መጻሕፍት ውስጥ ሳይሆን

በቤተክርስቲያናችን የትውፊት መጻህፍት ውስጥ እድገቱምን እንደሚመስል በዝርዝር ተጽፎ እናገኛለን፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 2. – በማቴዎስ ወንጌል 27፡3-10 (በዚያን ጊዜ አሳልፎ የሰጠው ይሁዳ እንደ ተፈረደበት አይቶ ተጸጸተ፥ ሠላሳውንም ብር ለካህናት አለቆችና ለሽማግሎች መልሶ፦ ንጹሕ ደም አሳልፌ በመስጠቴ በድያለሁ አለ። እነርሱ ግን። እኛስ ምን አግዶን? አንተው ተጠንቀቅ አሉ። ብሩንም በቤተ መቅደስ ጥሎ ሄደና ታንቆ ሞተ። የካህናት አለቆችም ብሩን አንሥተው። የደም ዋጋ ነውና ወደ መባ ልንጨምረው አልተፈቀደም አሉ። ተማክረውም የሸክላ ሠሪውን መሬት ለእንግዶች መቃብር ገዙበት። ስለዚህ ያ መሬት እስከ ዛሬ ድረስ የደም መሬት ተባለ። በዚያን ጊዜ በነቢዩ በኤርምያስ የተባለው። ከእስራኤል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን፥ የተገመተውን ዋጋ ሠላሳ ብር ያዙ፥ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሠሪ መሬት ሰጡት። የሚል ተፈጸመ።) በዚያን ጊዜ የነቢዩ የኤርሚያስ ቃል ተፈጸመ ይለናል ይሁዳ… እንዲህ ያለው ‹‹የእስራኤል ልጆች የተስማሙበትን የክቡርን ዋጋ ሠላሳውን ብር ወሰዱ›› ይህን ቃል የምናገኘው በስድሳ ስድስቱ ውስጥ ሳይሆን በተረፈ ኤርሚስ 7፡ 2-4 ባለው ላይ ነው፡፡ ቅዱስ ማቴዎስ ትንቢተ ኤርሚያስን ጠቅሶ ሲጽፍልን ‘በነብዩ ኤርሚያስ የተባለው ብሎን ነው፡፡’ ምን ተባለ ስንል ማቴዎስ ”የተባለውን” እና ”ተፈጸመ” ያለንን የምናገኘው መናፍቃኑ አንቀበለውም በሚሉት በ81

መጽሐፍት ውስጥ ነው፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 3. – ኦሪት ዘፍጥረት 1፡26 እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፡፡ ‹‹እንፍጠር›› ሲል ከአንድ በላይ ብዛትን ሲያመለክት 2 ወይም 4 ወይም 10 ሳይሆኑ ስላሴን /ሶስትነት/ ስስት መሆናቸውን የሚነግረን በሲራክ 2፤22 ሄኖክ 5፤38 ሄኖክ 6፤24 ሄኖክ 13፤14 እዝራ ስቱኤል 4፤56 እዝራ ስቱኤል 12፤48 ሲራክ 44፤10 በግልጽ ሥላሴ እያለ በማሳየት ነው፡፡ ክብር ለቅድስት ሥላሴ ይሁን!

_ _ _ _ _ _ _

ማስረጃ 4. በሉቃስ 14:13-14 “ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጕንድሾችን አንካሶችንም ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና

ብፁዕ ትሆናለህ” የሚለውን ኃይለ ቃል ከጦቢት 4፡7፡10 የተገኘ ነው ‹‹ከገንዘብህም ምጽዋት ስጥ ምጽዋትም በመጸወትህ ጊዜ በገንዘብህ አትዘን፣

ከድሃም ፊትህን አትመልስ፤ እግዚአብሔርም ገጸ በረከቱን ካንተ አይመልስም፡፡››

_ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 5. 1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4፡2 በጌታ በኢየሱስ የትኛውን ትእዛዝ እንደ ሰጠናችሁ ታውቃላችሁና። ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም

መቀደሳችሁ ነውና፤ ከዝሙት እንድትርቁ፥ የሚለውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ ከጦቢት 4፡12 ጠቅሶ ነው ያስተማረው የተገኘ ነው፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 6. በዮሐንስ ወንጌል 10፡22 በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤ … ‹‹የመቅደስ መታደስ በዓል›› በሌሎቹ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት አናገኘውም ግን ቅዱስ ዮሐንስ ከመጽሐፈ መቃብያን 4 ላይ ጠቅሶ ተናገረ፡፡

_ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 7. በ ሮሜ 13፡1 ከእግዚአብሔር ካልተገኘ በቀር ሥልጣን የለምና፤ ያሉትም ባለ ሥልጣኖች በእግዚአብሔር የተሾሙ ናቸው። የሚለው ኃይለ ቃል ከሲራክ 17፡14 የተወሰደ ነው፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 8. አዳምና ሔዋን አቤልና ቃየልን ወለዱ፡፡ ቃየል ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ይላል ዘፍጥረት 4፡17 በ66ቱ መጽሐፍት ላይ ስለ አቤልና ቃየል መወለድ እንጂ ሌላ የሰው ዘር በምድር ላይ ሰለመኖራቸው ምንም አያወራም፡፡ ታድያ ይህቺ የቃየል ሚስት ከየት መጣች? ስለስዋ ምንም አይናገርም በአለም ላይ የነበሩ ሰዎች አራት ብቻ እንደነበሩ ነበር የምናነበው፡፡ የዚህን መልስ የምናገኘው በኩፋሌ 5፡8-17 ላይ ነው፡፡

_ _ _ _ _ _ _

_ማስረጃ 9. – ይሁዳ በመልዕክቱ ‹‹የሄኖክን ትንቢት ከመጽሐፈ ሄኖክ ጠቅሶ›› ጽፎታል (ከአዳም ጀምሮ ሰባተኛ የሆነ ሄኖክ። እነሆ፥ ጌታ በሁሉ ላይ እንዲፈርድ፥ በኃጢአተኝነትም ስላደረጉት ስለ ኃጢአተኛ ሥራቸው ሁሉ ዓመፀኞችም ኃጢአተኞች በእርሱ ላይ ስለ ተናገሩ ስለ ጭከና ነገር ሁሉ ኃጢአተኞችን ሁሉ እንዲወቅስ ከአእላፋት ቅዱሳኑ ጋር መጥቶአል (ይሁዳ 1፡14-15) መጽሐፈ ሄኖክ ደግሞ በስልሣ ስድስቱ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፡፡ ሄኖክ ትንቢት ተናገረ ብሎ ከትንቢቱ ጠቅሱ ይሁዳ በመልዕክቱ ጽፎልናል ይህም ትንቢት በሄኖክ 1፡9 ላይ በግልጹ ተቀምጦ እናገኘዋለን፡፡

እንግዲህ ይሁዳ ሄኖክ ትንቢት መናገሩን እየነገረን ተቃዋሚዎች ሄኖክ ትንቢት አልተናገረም ይሉናል፡፡እኛስ በመንፈስ ቅዱስ ተመርቶ የጻፈወን ይሁዳን እናምናለን፡፡ እሱ የተቀበለውን እንቀበላለን ጥበብ አይኮረጅም (መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ የአምላክ ቃል)

– – – – – – –

-+- በመጀመሪያ እስኪ መጽሐፍ ቅዱስ ትውፊታዊ መረጃ መሆኑን እንተማመን፡፡ ትውፊት ማለት ቅብብል፣ ርክክብ ወይም ውርስ ማለት ነው፡፡ ይህ መንፈሳዊ ውርስ ከቀደሙት አበው ለእኛ በርክክብ ደርሶናል፡፡ አንዱ ከሌላው የተቀበለውን ለሌላው አሳልፎ በመስጠት እስከ ዘመናችን የደረሰ እውነታ ነው፡፡ ትውፊት መጽሐፍ ቅዱስ ከመጻፉ በፊት ያለ የነበረ ነው፡፡ እንደውም መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን አምነን የተቀበልነው የቀደሙት አባቶቻችን የእግዚሐብሔር ቃል መሆኑን በትውፊት ስላስረዱን ነው፡፡

-ለምሳሌ፡-

1-ዓለም ከተፈጠረ ሺህ 486 ዘምን መጽሐፈ ሄኖክ ተጻፈ

2- እስራሄል በግብጽ ሳሉ በፈርሆን ዘመን የኢዮብ መጽሐፍ ተጻፈ

3- 3643 ዓ.ዓ. እስራሄል ከግብጽ ወጡ በዚህ ጊዜ ኦሪት ተጻፈ፣ ወዘተ. . . . . እንግዲህ ከ1486 ዘመን በፊት የተጻፈ ህግ አልነበረም፤ በዚያ ጊዜ የነበሩ አበው ይመሩ የነበሩት ሙሉ በሙሉ በትውፊት ወይም በህገ ልቡና ነበር ማለት ነው፡፡ ከስልሳ ስድስቱ (66) መጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትየለም የምትሉ ወይም ትውፊታዊ መረጃ አንቀበልም ለምትሉ እስኪ የሚከተለውን ጥያቄ ላቅርብ

_ _ _ _ _ _ _

1- በኦሪት ዘፍጥረት አገላለጥ ቃየንም ሆነ አቤል ሁለቱም ለእግዚሐብሔር ከስራቸው ውጤት መስዋዕት አቅርዋል፡፡ ዳሩ ግን የተቀበለው የአቤልን መስዋዕት ብቻ ነው፡፡ የቃየንን መስዋዕት ያልተቀበለው ለምንድን ነው? መቼም ለአቤል አድልቶ ነው የሚል መልስ እንደማይሰጥ እርግጣኛ ነኝ ምክንያቱም እግዚሐብሔር ለሰው ፊት አያዳላም፡፡

2- አቤል ከበጎቹ በኩራትና ከሰቡ እግዚሐብሔር መስዋእት አቅርቧል፤ ከበጎቹ መካከል በኩራትና ስቡን ማቅረብ እንደሚገባ እንዴት አወቀ? ምክንያቱም የጽሁፍ ህግና ትዕዛዝ በዘመኑ አልነበረም 3- ‹ቃየንም ሚስቱን አወቀ ጸነሰችም ሄኖህንምም ወለደች› ይላል፡፡ እግዚሐብሔርወንድና ሴት አድርጎ የፈጠረው አዳምንና ሄዋንን ብቻ ነው፡፡ አዳምና ሄዋን ደግሞ የወለዱአቸው አቤልና ቃየንን እንደሆነ በምዕራፍ 4 ተገልጽዋል ፤ታዲያ የቃየን ሚስት ማንነች? ከየትስ መጣች? ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከ66 መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆኑትን ሌሎች ቅዱሳት መጻህፍትንና ትውፍታዊ መረጃ መሰረት ማድረግ ይገባል ያለበለዚያ ጥያቄዎቹ የማይፈቱ እንቆቅልሽ ሆነው መቅረታቸው ነው?

_ _ _ _ _ _ _

– እስኪ ደግሞ ወደ ሐዲስ ኪዳን እንሂድ፡፡ የመጀመሪያዎቹ ክርስቲያኖች ቢያንስ ቢያንስ ለ20 ዓመታት ያህል ስለ ጌታ ይማሩ የነበሩት በቃል ነበር ምክያቱም ሐዲስ ኪዳን ገና በጽሁፍ አልተቀረጸም ነበርና በቅብብል ወይም በሰሚ ያገኙትንም እነርሱ ራሳቸው ከጌታ እደተቀበሉት አድርገው ያስተምሩ ነበር ለዚህም ጥሩ ምሳሌ የሚሆነው ጳውሎስ ነው (1 ቆሮ. 11፥23-24)፡፡ ጳውሎስ ከሐዋርያት ቃል የተማረውን ለሌሎች ደግሞ አስተላለፈ፡፡ ስለዚህም ወንጌል የሚያሰኘው በጽሁፍ መስፈሩ ብቻ ሳይሆን የሕያው የእግዚሐብሔር ቃልና የህይወት መንገድ መሆኑነው፡፡ በጌታ ጊዜ ወንጌል ገና አልተጻፈም ነበር፣ “ለሐዋርያቱም ወደ ዓለም ሒዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ ”(ማር.16፥1) ይህም ሲል የሰሙት ተማሩት እንጂ በጽሁፍ ቀርጾ የሰጣቸው ወንጌል አልነበረም፡፡

_ በተጨማሪም በማርቆስ ወንጌል ም.1፥21-22 ‹ወደ ቅፍራንሆም ገቡ ወዲያውም በሰንበት ወደ ምኩራብ ገብቶ አስተማረ እንደ ባለስልጣን ያስተምራቸው ነበር እንጂ እንደ ጸፎች አይደለምና በትምህርቱ ተገረሙ›፡፡ ይህ የክርስቶስን ተቃዋሚዎች ራሱ ያስገረማቸው ትምህርት ምን አይነት ነበር ‹ከሙሴና ከነቢያት ሁሉ ጀምሮ ስለእርሱ በመጻህፍት ሁሉ የተጻፈውን ተረጎመላቸው› ሉቃ 24-27

_ ከትንሳሄው በኋላ ለሁለቱ ደቀ መዝሙር ተረጎመላቸው የመጻህፍት ትርጓሜ በየትኛው ሀዲስ ኪዳን ላይ ይገኛል? “በነቢያት ናዝራዊ ይባላል የተባለው ይፈጸም ዘንድ. . . ናዝሬት ወደምትባል ከተማ መጥቶ ኖረ” ማቴ 2፥23 ይህን የተናገረው ነቢይ ማነው? በየትኛው የትንቢት መጽሐፍ ይገኛል? ማቴ 27፥9 ‹በዚያን ጊዜ በነቢዩ ኤርምያስ የተባለው ከእስራሄል ልጆችም አንዳንዶቹ የገመቱትን የተገመተውን ዋጋ ሰላሳ ብር ያዙ ጌታም እንዳዘዘኝ ስለ ሸክላ ሰሪ መሬት ሰጡት የሚል ተፈጸመ› ይህስ ከየት ተገኘ? በተጨማሪም ሉቃ 2፥25-32፣ 2ኛ ጢሞ 2፥ 8፣ ዕብ 12፥ 21 ፣ ራዕይ 2 ፥14፣ ዮሐ 20፥ 30

፣ ዮሐ 21 ፥25፣ ይሁዳ 9 እንዲሁም ዮሐ 1 ፥48 ሌሎች ማሳያዎች ናቸው፡፡

_ በአጠቃላይ እነዚህ መረጃዎች ከ66ቱ መጻህፍት የማናገኛቸውና ነገር ግን ተዋህዶ እምነት በምትጠቀምበት ሰማንያ አህዱ ውስጥ ፍንትው ብለው የተጠቀሱ ናቸው፡፡ ታዲያ እነዚህን የመሳሰሉ ፍሬ ሃሳቦች ስለተቀመጡበት ነው ሰማንያ አሃዱን ከሌላው ጋር ይጋጫል የሚባለው?

_ ብርሃን ዓለም ጳውሎስ ‹እንግዲያስ ወንድሞች ሆይ ጸንታችሁ ቁሙ በቃላችንም ቢሆን ወይም በመልእክታችን የተማራችሁትን ወግ ያዙ› ያለው (2ተኛ

ተሰሎንቄ 2 15)፡፡ በቃላችንም በመልእክታችንም የተማራችሁትን ‹ወግ› ያዙ ሲል ትውፊትን ማለቱ ነው፡፡

_ ፊልጵ 4፥9 ‹ከህኔ የተማራችሁትና የተቀበላችሁትን የሰማችሁትንም እና ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሰላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል›፡፡

የቅዱስ ጳውሎሰ መልዕክት ግልጽ ነው፡፡ በፊልጵስዮስ የሚኖሩ ክርስቲያኖች ከእርሱ ከአንደበቱ የተማሩትንና በጽሁፍ የተቀበሉትንም የሰሙትንም ያዩትንም ሁሉ እንዲይዙ እንደያደርጉ እንጂ የተጻፈውን ብቻ እንዲይዙና እንዲጠብቅ አልነበረም፡፡ ዛሬም እኛ በትውፊት የደረሰንን ሁሉ ልንጠብቅ መንፈሳዊ ግዴታችን ነው ፡፡

_ 2ኛ ጢሞ ‹የእግዚሐብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ስራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለበትን መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሳጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ይጠቅማል›፡፡ ምክሩም ጠቃሚና አስፈላጊ መሆኑን ተዋህዶዋውያን እናምናለን፡፡ ስለዚህም በቤተክርስቲያናችን ያሉትን የእግዚሐብሔር መንፈስ ያለባቸውን ቅዱሳት መጻህፍት ሁሉ ለክርስቲያናዊ ህይወታችን እንገለገልባቸዋለን፡፡

–> በመጨረሻም ኦርቶዶክሳዊያን በቤታችን ያለን መጽሐፍ ቅዱስ:-

81: የኦርቶዶክስ

73: የካቶሊክ

66: የፕሮቴስታንት

24: የአይሁድ

በሆኑንና አለመሆኑን ለይተን ተረድተን የረሳችንን የሆነውን ትክክለኛውን 81 አሐዱ መጽሐፍ ቅዱስን እንጠቀም።

+ + + + + + +

ከዋክብት የሚያመሰግኑት በስማቸውም የሚጠራቸው: የፀጋው ብዛት የማይታወቅ ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋውን ያብዛልን በትክክለኛው መንገድ እንድንኖርና እንድናልፍ ይርዳን ። አሜን

፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ

መጽሐፍ ቅዱስ ማን ጻፈው?

መጽሐፍ ቅዱስ ባለቤቱ እግዚአብሔር ሲሆን ጸሐፊዎቹ ግን ከእርሱ የተላኩ ቅዱሳን ሰዎች ናቸው፡፡ ጸሐፊዎቹ ብዛታቸውም ከአርባ በላይ ሲሆን አንዳቸውም ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አልጻፉም፡፡ “በእግዚአብሔር ተልከው ቅዱሳን ሰዎች በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ተናገሩ” 2ጴጥ 1፡20

 

-+- መጽሐፍ ቅዱስ አሁን በእጃችን ላይ እንዳለው በአንድ የተጠረዘ መጽሐፍ ነበር?

– መጽሀፍ ቅዱስ በአንድ ወቅት በአንድ ጊዜ ተጠርዞ የተሰጠ ወይም ከሰማይ የወረደ ሳይሆን የተለያዩ ክፍሎች በተለያዩ ጸሐፍት እና ዘመናት የተጻፉ ናቸው፡፡ በጥንት ዘመን መጸሀፍት በጥቅል ተጠቅልልው ይቀመጡ እንደነበር ብዙ ማስረጃዎች አሉ፡- ጌታችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ናዝሬት በሚገኘው ምኩራብ ያነበበው የነቢዩ ኢሳያስን ጥቅልል መጽሐፍ ነበረ፡- “የነቢዩን የኢሳያስን መጽሀፍ ሰጡት መጽሐፉንም በተረተረ ጊዜ የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው …….. ተብሎ የተጻፈበትን ስፍራ አገኘ፡፡ መጽሐፉንም ጠቅልሎ ለአገልጋዩ ሰጠውና ተቀመጠ፡፡” ሉቃ 4፡17-20 ከዚህ ክፍል እንደምንረዳው ቅዱሳት መጻህፍት ለየብቻቸው በአንድነት ሳይጠረዙ እንደነበሩ ነው፡፡

 

-+- ቅዱሳት መጻህፍት አሰባሰብ?

-ቅዱሳት ሐዋርያት ስለ ስርዓተ ቤተክርስትያን የተለያዩ ቀኖናትን ደንግገዋል፡፡ ከነዚህም ውስጥ አንዱ ስለ ቅዱሳት መጻህፍት ነው፡፡ በ325 እ.ኤ.አ በኒቂያ በተካሄደው ጉባኤ ላይ እውነተኖቹን ቅዱሳት መጻህፍት ለመሰብሰብ በተወሰነው መሰረት ቅዱስ አትናቲዎስ በ367 ዓ.ም በ39ኛው የትንሳኤ ምልዕክቱ ላይ የቅዱሳትን መጽሐፍትን እና አይነት በአብዛኛው አስታውቋል፡፡ ከዚያም በሎዶቅያ በተካሄደ ጉባኤ እና በ393፣399 እና 419 እ.ኤ.አ በሰሜን አፍሪካ ትገኝ በነበረችው ቅርጣግና /ካርቲጅ/ በተካሄዱት ጉባኤዎች ቅዱሳት መጽሐፍትን ለይቶ ለማወቅ ጥረት ተደርጓል፡፡ የካርቴጁ ጉባኤ ከተካሄደ በኋላ ቅዱሳት መጻሕፍትን በአንድ ላይ መጠረዝ እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ የሁሉም ቅዱሳት መጻሕፍት መድብል/ጥራዝ/ ተብሎ መጠራት ተጀመረ::

 

-+- ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን የቅዱሳት መጻሕፍት ብዛት ሰማንያ አንድ መሆኑን ትናገራለች፡፡ ዳሩ ግን በዓለም ላይ በብዛት ተሰራጭቶ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ስልሣ ስድስት ነው፡፡

– በስልሣ ስድስቱ ውስጥ የሌሉት መጻሕፍት:-

ሀ. ከ ብ ሉ ይ (2ኛ የቀኖና መጻሕፍት):-

1.መጽሐፈ ዕዝራ ሱቱኤል

2.መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ

3.መጽሐፈ ጦቢት

4.መጽሐፈ ዮዲት

5.መጽሐፈ አስቴር

6.መጽሐፈ መቃብያን ቀዳማዊ

7.መጽሐፈ መቃብያን ካልዕ

8.መጽሐፈ መቃብያን ሣልስ

  1. መጽሐፈ ሲራክ

10.ጸሎተ ምናሴ

  1. ተረፈ ኤርሚያስ

  2. ሶስና.

  3. መጽሐፈ ባሮክ

  4. መጽሐፈ ጥበብ

  5. መዝሙረ ሰልስቱ ደቂቅ

  6. ተረፈ ዳንኤል

  7. መጽሐፈ ኩፋሌ

  8. መጽሐፈ ሄኖክ

– – – – – – –

ለ. ከሐዲስ ኪዳን:-

  1. ትዕዛዘ ሲኖዶስ

  2. ግስው ሲኖዶስ

  3. አብጥሎ ሲኖዶስ

  4. ሥርዓተ ጽዮን ሲኖዶስ

  5. መጽሐፈ ኪዳን ቀዳማዊ

  6. መጽሐፈ ኪዳን ካልዕ

  7. ቀለሚንጦስ

  8. ዲዲስቅሊያ (እነዚህ የሐዲስ ኪዳን መጻህፍት አሁን በእጃችን በሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አልተካተቱም፡፡ ይህም የሆነው እያንዳንዳቸው በጣም ትልቅ መጻሕፍት በመሆናቸው ለማካተት አስቸጋሪ በመሆኑ ነው፡፡ ግን ከ81 መጻሀፍት መድበን ነው የምንቆጥራቸው፡፡ ሁሉም መጻህፍት በቤተክርስትያኖች ቤተ-መጻሀፍት ውስጥ ይገኛሉ እንዲሁም ገዝቶ ማንበብ ይቻላል፡፡

– – – – – – –

-+- እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን መጽሕፍት ሳታጓድል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ትቀበላለች፡፡ ዘመናዊ ነን የሚሉ እምነቶች ግን ከስልሣ ስድስቱ ውጭ ሌላ የለም ሲሉ ይሰማሉ፣ ለዚህም የሚጠቀሱት ዩሐንስ ራዕይ መጨረሻው ላይ ያለውን ቃል ነው።

‹‹ማን በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር እግዚአብሔር በዚህ መጽሐፍ የተጻፉት ቃሎች አንዳች ቢያጎድል በዚህ መጽሐፍ ከተጻፉት ከሕይወት ዛፍና ከቅድስቲቱ ከተማ እግዚአብሔር ዕድሉን ያጎድልበታል››፡፡ ራእይ 22‹18

– ይህን አባባል በጥሞና ስናጤነው የዩሐንስ ራዕይን ብቻ የሚመለከት ሆኖ አናገኘዋለን፡፡ “በዚህ በትንቢት መጽሐፍ” አለ እንጂ ከዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ አላለም፡፡ ምክንያቱም መጽሐፍ ቅዱስ “የትንቢት መጽሐፍ” ብቻ ሳይሆን የ”ወንጌል” ፣የመዝሙር፣ የመልዕክታት እና የመሳሰሉት መጽሐፍ ነው፡፡

– በተጨማሪ የዮሐንስ ራዕይ መጽሐፍ ጠፍቶ ስለነበር እንደገና ለቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እግዚአብሔር ገልጾለት ስለጻፈው ” በዚህ ላይ አንዳች ቢጨምር” ብሎ የጻፈው ወጌላዊው ዮሐንስ ሳይሆን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ነው።

– ደግሞም መጽሐፍ ቅዱስ ከመነሻው እንደዚሁ አንድ ላይ እንደተጠረዘ ሆኖ የተገኘ አይደለም፡፡ ጻሕፍቱ በተለያየ ዘመን የነበሩ እንደሆነ ሁሉ ፣መጻሕፍቱም በተለያዩ ዘመናት የተጻፉና በአንድ ወቅት ሁሉም የመጽሐፍ ቅዱስ መጸሐፍ ተጽፈው አልቀው በጥራዝ መልክ እንደወጡ አድርጎ በመውሰድ የዩሐንስ ራዕይን ማጠቃለያ ለሁሉም መጻሕፍት አድርጎ መውሰድ አለማወቅ ወይንም ተንኮል ነው፡፡

– – – – – – –

 

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top