ገነት – መንግስተ ሰማይ – ሲኦል እና ገሀነም

የገነት: መንግስተ ሰማይ ሲኦል እና ገሀነም

ገነት :-በዚህ አለም ትሩፋት የሰሩ ቅዱሳን ፃድቃን እና ሰማዕታት የዚህ አለም ተጋድሏቸውን ከጨረሱ በኋላ ሲሞቱ ነፍሳቸው የምታርፍበት ቦታ ናት::

ስለገነት:- ሉቃ 23:43 “እየሱስም እውነት እውነት እልሀለሁ ዛሬ በገነት ከኔ ጋር ትሆናለህ አለው”

2ቆሮ 12:4 ” ወደ ገነት ተነጠቀ ሰውም ሊናገር የማይገባውን የማይነገረውን ቃል ሰማ”ራዕይ 2:7 “…ድል በነሳው በእግዚአብሄር ገነት ካለው ከህይወት ዛፍ እንዲበላ እሰጠዋለሁ”

መንግስተ ሰማያት :- ፅድቅ የሰሩ ሰዎች እና የቅዱሳን ሁሉ ዘላለማዊ ማረፊያቸው የእግዚአብሔር መንግስት ናት:: ይህም ማለት ዘመነ ምፅአት በደረሰ ጊዜ ጌታችን ለፍርድ ሲመጣ ከገነት ወደ መንግስተ ሰማያት ይሄዳሉ::

ስለመንግስተ ሰማይ:- ማር. 1፥14 – 15 “ዮሐንስም አልፎ ከተሰጠ በኋላ ኢየሱስ የእግዚአብሔርን መንግሥት ወንጌል እየሰበከና። ዘመኑ ተፈጸመ የእግዚአብሔርም መንግሥት ቀርባለች ንስሐ ግቡ በወንጌልም እመኑ እያለ ወደ ገሊላ መጣ። ማቴ 4 :17 “የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሆነ። ከዚያ ዘመን ጀምሮ ኢየሱስ፦ መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ እያለ ይሰብክ ጀመር።”

  • በገነት ውስጥ ያሉ አራቱ አፍላጋት እነማን ናቸው ?

የመጀመሪያው, ወርቅ በሚገኝበት በኤውላጥ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው ኤፊሶን ወንዝ ነው። ኤውላጥ ምርጥ የሆነ ወርቅ፣ መልካም መዐዛ ያለው ከርቤና የከበረ ድንጋይ የሚገኙበት ምድር ነው።( ዘፍ. 2:11-12)

ሁለተኛው, በኢትዮጵያ ምድር ዙሪያ ሁሉ የሚፈሰው የግዮን ወንዝ( አባይ) ነው። (ዘፍ 2:13)

ሦስተኛው,ከአሦር በስተምሥራቅ የሚፈሰው የጤግሮስ ወንዝ ፣ ( ዘፍ 2 :14)

አራተኛው, # የኤፍራጥስ ወንዝ ነው። (ዘፍ 2: 15)

አራቱ አፍላጋት በአራቱ ወንጌላትና ወንጌላውያን ይመሰላሉ:: ምክንያቱም አራቱ አፍላጋት ገነትን ሙሉ አጠጥተው እንደሚያረኩ አራቱ ወንጌላውያንም በስብከታቸው በትምህርታቸው ይኸን አለም ዙረው ምዕመናንን አርክተዋል::

በሌላ በኩል ደግሞ በአራቱ የእመቤታችን ንፅህና ይመሰላሉ::

  • የሲዖልና የገሃነም ልዩነት ምንድነው?

ሲኦል :-ጥሩ ያላደረጉ ኃጥአን ከዚህ አለም በሞቱ ጊዜ ነፍሳቸው እስከ ዘመነ ምፅአት ድረስ የሚቆይበት የስቃይ ቦታ ነው::

ገሀነም:- ደግሞ ከትንሳኤ ሙታን በኋላ መጥፎ ያደረጉ እና ሀጢአተኞች ለዘላለም የሚሰቃዪበት ቦታ ነው።

” ሕዝቤ እውቀት ከማጣቱ የተነሣ ጠፍቶአል፤ (ትንቢተ ሆሴዕ 4:6)

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top