እንደቸርነትህBy zetewahedo / 08/31/2021 እንደቸርነትህ እንደቸርነትህ አቤቱ ማረኝ /2/እንደምሕረትህ ይቅርታን ስጠኝ /2/ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ /2/ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ /2/እኔም አበሳየን በደሌን ሳውቀው /2/ፍጹም የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው /2/አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ /2/አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ /2/ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን /2/መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሃን /2/አሁን ትባርክ ዘንድ ማህበራችንን ሀገራችንንጌታ ሆይ ላክልን መንፈሰ ቅዱስን ጰራቅሊጦስን