አማላጅነት

ምልጃ ማለት አንዱ ስለሌላው የሚያደርገው ልመናና ጸሎት ነው፡፡ አንድ ሰው ሌላውን ሰው ያስቀየመ በደለኛ፤ አንድም ጥፋቱን በመገንዘቡ ወይም ካስቀየመው ሰው በኩል የነበረውንና ሊኖረው የሚችለው ጥቅም ስለሚቀርበት ወይም ደግሞ ከዚያ ካስቀየመው ሰው ጋር በሰላም ካልኖረ ችግር ሊደርስበት ስለሚችል አስታርቁኝ ብሎ አማላጅ ይልካል፡፡ አማላጅ በመላክ ፈንታ ራሱ ሄዶ ይቅርታ የማይጠይቀው አንድም ያስቀየመውን ሰው ከማክበሩ የተነሣ በቀጥታ መሄድን እንደ እፍረት በመቁጠሩ ወይም ያን ሰው በጣም በማስቀየሙ እንዴትአድርጌዓይኑንለማየትእችላለሁ ብሎ በመፍራት ወይም ደግሞ ያ አማላጅ የሚላክበት ሰውበደረጃውከፍያለ ከመሆኑ የተነሣ በቀላሉ ሊያገኘው የማይችል በመሆኑ ነው፡፡ አማላጅ ሆኖ የሚላከው ሰው አግባብቶ እሺ ለማሰኘት ተሰሚነት ያለው ሰው መሆን ይኖርበታል፡፡
አማላጅነት ሦስት ነገሮችን (አካላትን) ይይዛል፡፡
ሀ) ተማላጅ (የሚለመን)፡- ተማላጅ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር አምላክ ነው፡፡
“ከአንዱከእግዚአብሔር በቀርኃጢአትሊያስተሰርይማንይችላል?” (ሉቃ 5፡፳1)
ለ) አማላጅ (የሚለምን)፡- አማጅነት የፍጡር ሥራ ነው፡፡ አማላጆች ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ሐዋርያት፣ ቅዱሳን ናቸው፡፡ ቅዱሳን በጸሎታቸው፣ በቃል ኪዳናቸው ከእግዚአብሔር ስለ በደለው ሰው ምሕረትን የሚያሰጡ ናቸው፡፡ (1ኛ ዜና ፳1፡07፣ ዘፍ 08፡፳3)
ሐ) የሚማለድለት (የሚለመንለት)፡- ኃጥኣን የቅዱሳን ምልጃና ቃል ኪዳን የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ናቸው፡፡ (ኤር 7፡06-09፣ ዘኊ ፳1፡6-9)
አማላጅነት ያስፈለገበት ምክንያት
1. አማላጅነት የእግዚአብሔር ፈቃድና ትዕዛዝ በመሆኑ ነው፡፡
ጻድቃን ለኃጥኣን ወገኖቻቸው የሚለምኑት ልመና በእግዚአብሔር ዘንድ ተወዳጅና ተሰሚነት አለው፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ምንም እንኳን ኃጥኣንን በክፉ ሥራቸው ቢያዝንባቸውም በቸርነቱ የሚምርበት ምክንያት….
ተጨማሪ ያንብቡ ︾

የቅዱሳን አማላጅነት በአፀደ ሥጋ እና በአጸደ ነፍስ

የአማላጅነት ትምህርት በዘመነ አበው በሕገ ልቡና፣ በዘመነ ኦሪት በመጻሕፍተ ብሉያት በዘመነ ሐዲስ በመጻሕፍተ ሐዲሳት የነበረና አሁንም ያለ ወደፊትም የሚቀጥል ትምህርት እንጂ ከጊዜ በኋላ ድንገት የመጣ አይደለም፡፡ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያናችንም የቅዱሳት መጻሕፍትን የሐዋርያትንና የሊቃውንትን ትምህርትና ትውፊት ታስተምራለች፡፡ አማላጅነት እግዚአብሔር የሚፈቅደውና የሚወደው እንጂ ሰው ሰራሽ ልማዳዊ ወግ አይደለም ከቤተ ክርስቲያን ታሪክ እንደምንረዳው ክርስትና ከተመሠረተበት ጊዜ አንስቶ የአማላጅነት ትምህርት ያለ እንጂ በኋላ ጊዜ ብቅ ያለ አይደለም፡፡

ዛሬ በተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በተለይ በሀገራችን ውስጥ በየአውቶቢስ ማቆሚያው በመናፈሻዎች፣ በሠረግ ቤት፣ በለቅሶ ቤት፣ በሆቴሎች፣ በመሥሪያ ቤቶች ፣ በትምህርት ቤቶች፣ በመኖሪያ አካባቢዎች በገጠር በከተማ እጅግ አከራካሪና አወዛጋቢ የሆነው አቢይ ጉዳይ በአማላጅነት ላይ የሚነሳው አቢይ ጥያቄ ነው፡፡ ሰዎች ስለአማላጅነት ያላቸው አቋም የሚከተሉትን እምነት የሚጠቁም በመሆኑ ያ ብዙ ውጣ ውረድ የሰዎችን እምነት አቋም መለያ ሆኗል ከዚህም የተነሣ ወላጆችና ልጆች ባል ከሚስት ጓደኛ ከጓደኛ ጎረቤት ከጎረቤት ወዘተ ተቆራርጧል ተለያይቷል፡፡

እኛ ኦርቶዶክሳውያን ፃድቃን ሰማዕታት ቅዱሳን መላእክት ይልቁንም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ያማልዱናል ከፈጣሪያችን ዘንድ ያስታርቁናል ብለን የምናምነው እምነት የምንቀበለው ትምህርት የቅዱሳንን አማላጅነት ለማይቀበሉት ወገኖች ጆሮን የሚያሳክክ የእግዚአብሔርን ክብር የሚነካ ትምህርት መስሎ ይታያል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ፣ የቅዱሳንን አማላጅነት የሚቃወሙት ወገኖች ክብር ምስጋና ይግባውና የባሕሪ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስን አማላጃችን ነው የሌሎችን ፍጡራን ረዳትነት አንሻም የሚለው ትምህርት ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ጆሮ የሚዘገንንና የሚቀፍ ከመሆኑ ባሻገር ምንፍቅናና ክህደትም ጭምር ነው፡፡

በሃይማኖት የምንመስላቸው ጥንታውያን የሆኑት የእስክንድርያ ፣ የሦርያ፣ የሕንድና የአርመንያ አቢያተ ክርስቲያናት የቅዱሳንን አማላጅነት በሚገባ ይቀበላሉ፡፡ እንዲሁም በሃይማኖት ቀኖና ዶግማ ከእኛ የሚለዩት ጥንታውያን የሆኑት የሮም ካቶሊክና የግሪክ ፣ የራሽያ፣ የሮማንያ ኦርቶዶክስ አቢያተ….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ቅዱሳን፣ጻድቃን፣ሰማዕታት በመፅሓፍ ቅዱስ

በብሉይ ኪዳን

• ኢያሱ ጸሐይን አቆመ።(ኢያ.10፣13) ሕዝቡም ጠላቶቻቸውን እስኪበቀሉ ድረስ ፀሐይ ቆመ፥ ጨረቃም ዘገየ።
• ሶምሶን የመኳንንቱን ቤት አፍርሷል።(መሳ.16፣30) ምሰሶቹን በሙሉ ኅይሉ ገፋ፥ ቤቱም በውስጡ በነበሩት በመኳንንቱም በሕዝቡም ሁሉ ላይ ወደቀ።
• ኤልያስ ሰማይን ለጉሟል ደግሞም መልሶ ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል።(1ኛ ነገ18፣41-45) ከጥቂትም ጊዜ በኋላ ሰማዩ ከደመናውና ከነፋሱ የተነሣ ጨለመ፥ ብዙም ዝናብ ሆነ፤
• አልያስም ኤልሳዕም የዮርዳኖስን ባሕር ከፍለዋል(2ኛ ነገ.2፡8 2፣19)
• አልያስ በሰራፕታ የባልቴቷን ቤት በበረከት ሞልቷል።(1ኛ 17፣14) በምድር ላይ እግዚአብሔር ዝናብ እስከሚሰጥበት ቀን ድረስ፥ ዱቄቱ ከማድጋ አይጨረስም፥ ዘይቱም ከማሰሮው አይጎድልም።
• አልያስ የሞተ ልጇን አስነስቷል።(1ኛነገ 17፣22) እግዚአብሔርም የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች፥ እርሱም ዳነ።
• ኤልሳዕም ለሱነማዊት ሴት በረከት ሰጥቷል የሞተ ልጇንም አስነስቷል(2ኛ ነገ 4 1-35 ) መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ።ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ።
• ኤልሳዕ ንዕማንን ከለምጹ አንጽቶታል።2ኛ ነገ 4፣42-44 በባህር የሰጠመውን መጥረቢያ በውሃ ላይ እንዲሳፈፍ አድርጓል። 2ኛ ነገ 6፣6
• ኤልሳዕ የደቀመዝሙሩን ዓይነልቡና ተከፍቶ መላዕክትን ለማየት እንዲበቃ አድርጓል።(2ኛ ነገ 6፡17) የሶርያውን ሰራዊት አይናቸው እንዲታወር አድርጓል።
• ኤልሳዕ በተቀበረበት ቦታ የወደቀ የሞተ ሰው ከሞት ተነስቷል።ከሞተ በኋላ እንኳ ሙት አስነስቷል።(1ኛ ነገ 13፣21) ሰዎችም አንድ ሰው….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ነገረ ቅዱሳን

•‹‹ነገር›› ማለት፡- በቤተክርስቲያን የአንድነት ትምህርት ሙሉ መግለጫ በመሆን ያገለግላል፡፡
•በዚህ ነገር ስንል ስለአንድ ነገር የሚናገር፣ የሚያስረዳ፣ የሚተርክ ለዛ ለሚነገርለት ነገር እንደመግለጫ አስረጂ ሆኖ የሚቀርብ ቃል ነው፡፡
ቅዱስ ማለት
•‹‹ቅዱስ›› ማለት ‹‹ቀደሰ›› ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ለየ፣ አከበረ፣ አመሰገነ፣ አገነነ፣መረጠ፣ አጠራ፣ አነጻ፣ ባረከ ወዘተ … ማለት ነው፡፡
•በመሆኑም ቀደሰ ሲል ከርኩሰት፣ ከኃጢአት መንጻት፣ በማየ ቅድስና መንጻት (መታጠብ)፣ መአዛ ኃይማኖት ሆኖ መገኘትና፣ ለመልካም አገልግሎት በቅብዐ መንፈስ ቅዱስ ተቀብቶ ብቁ መሆን ማለት ነው፡፡
ቅድስና ራሱ በሁለት ይከፈላል
1. የባህሪ ቅድስና
•የባህሪይ ቅድስና ገንዘብነቱ ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ቅዱስ የሚለው ቃል ከሁሉ በፊት የሚያገለግለው ለእግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡
•ይህ ስም የእግዚአብሔር የባህሪዩ መገለጫ ሆኖ የሚጠራበት ስያሜ ሲሆን ቅድስናው ከእርሱ የማይለይ
ከማንም ያልተቀበለው፣ ያልተዋሰው ማንም ሊወስድበት የማይችል የራሱ ገንዘብ ማለት ነው፡፡ ዘሌ. 19÷2 ‹‹እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ›› እንዲል፡፡
መዝ. 137÷2 ‹‹ወደቅዱስ መቅደስህ እሰግዳለሁ፤ ስለምህረትህና ስለ እውነትህ ስምህን አመሰግናለሁ፤ በሁሉ ላይ ቅዱስ ስምህን ከፍ ከፍ አድርገሀልና›› እንዲል፡፡
2. የጸጋ ቅድስና
•‹‹ጸጋ›› ማለት፡- ቸርነት፣ በጎነት፣ ምህረት፣ ያለብድራት፣ ያለዋጋ የሚደረግ ስጦታ ማለት ነው፡ በመሆኑም የጸጋ
ቅድስና ስንል ከእግዚብሔር በጸጋ (በስጦታ) የተሰጠ ወይም የተገኘ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛው
ከእግዚአብሔር የሚገኝ ሃብት ሁሉ የጸጋ ቅድስና፣ የጸጋ ሀብት ይባላል፡፡
መዝ. 32÷5 ‹‹ጽድቅና ፍርድን ይወድዳል የእግዚአብሔር ቸርነት ምድርን ሞላች››
ሮሜ 8÷28 ‹‹እግዚአብሔር ለሚወድዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን›› እንዲል፡፡ ከላይ….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top