አልተሳሳትንም === በመምህር ምህረተ አብ
በምስክሩ ታቦት ላይ ሆኜ አነጋግርሃለው === ቀሲስ ተስፋዬ መቆያ

ታቦት እና ጽላት

ትምህርት ሃይማኖት (የሃይማኖት ትምህርት) በሁለት ይከፈላል፡፡
ይኸውም፦
1 ኛ፡- ዶግማ 2 ኛ፡- ቀኖና በሚል ነው፡፡
ዶግማ፡- ቃሉ የግሪክ ሲሆን ፍችውም እምነት ማለት ነው፡፡
ቀኖና፡- ደግሞ ቃሉ የግሪክ ሲሆን ሥርዓት ማለት ነው፡፡ ከእነዚህ ከሁለቱ ዶግማ ወይም እምነት አይጨመርበትም፤ አይቀነስበትም፤ አይሻሻልም፤ ችግርና ፈተናም ቢመጣ እስከ ሞት ድረስ አጥብቀን የምንይዘው ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ይህን ዓለም ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ የፈጠረ፤ ቢመረምር እንጂ የማይመረመር ሁሉን ቻይ አምላክ፤ የሚሳነው ነገር የሌለ ፈጣሪ፤ የሰማይና የምድር ባለቤት የሠራዊት ጌታ ሕያው እግዚአብሔር ነው፡፡ እግዚአብሔር (ፈጣሪ) የአካል ሦስትነት አለው፡፡ በመለኮት፣ በመፍጠር፣ በሥልጣን፣ በአገዛዝ፣ በፈቃድ ግን አንድ ነው፡፡ በሦስትነቱ አብ፤ ወልድ፤ መንፈስ ቅዱስ ሲባል በአንድነቱ አንድ መለኮት አንድ እግዚአብሔር ይባላል፡፡ በአዳም ምክንያት ከመጣው የዘለዓለም ሞትና ከዲያብሎስ
ባርነት ነጻ የወጣነው ከሦስቱ አካላት በአንደኛው አካል ማለትም በወልድ በኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ይህ ዶግማ ወይም እምነት ይባላል፡፡
ቀኖና ግን በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ አምነው ያደጉ ክርስቲያኖች የሚመሩበት ሥርዓት ስለሆነ፤ በሃይማኖት አባቶች ወይም በቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት እንደጊዜው ሁኔታ የሚሻሻል በመሆኑ የሚጨመርበት፤ የሚቀነስለት ነው፡፡ ለምሳሌ ያህል እኛ ኦርቶዶክሳውያን የምንጠመቀው ሴት በሰማንያ ወንድ በአርባ ቀናችን ነው፡፡ የተወለዱ ሕጻናት ሴቷ ሰማንያ ወንዱም አርባ ቀን ሳይሞላቸው ቢታመሙና በሽታው አስጊ ከሆነ በ 10፣ በ 20፣ በ 30…ቀናቸው መጠመቅ ይችላሉ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን የቀዳስያን ብዛት መነሻው አምስት ነው፡፡ ምናልባት ከአምስቱ አንዱ፤ ሁለቱ፤ ሦስቱ ቢታጡና ሌላም ተፈልጎ እስከ መጨረሻ የማይገኝ ከሆነ ከአቅም በላይም የሆነ ችግር ከገጠመ ሁለቱ ወይም አንዱ ብቻ ቀድሰው ማቁረብ ይችላሉ፡፡ ቀኖና ነውና፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ታቦት ሲከብር ቤተ ክርስቲያኑን የሚዞረው ሦስት ጊዜ ነው ችግር ካለ አንድ ጊዜ ብቻ ዑደት ተፈጽሞ ሊገባ ይችላል። ቀኖና ነውና፤ ስለቀኖና (ስለሥርዐት) ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ እንዲህ ሲል ጽፏል።
1. ‹‹ነገር ግን ሁሉን በአግባብና በሥርዐት አድርጉ፡፡›› 1 ኛ ቆሮ. 14፥40፡፡
2. ‹‹ወንድሞች ሆይ በሠራንላቸው ሥርዐት ሳይሆን በተንኮል ከሚሄዱት ወንድሞች ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፡፡ እኛን ልትመስሉ እንደሚገባችሁ እኛም በእናንተ መካከል ያለ ሥራ እንዳልኖርን ራሳችሁ ታውቃላችሁ›› 2 ኛተሰ. 3፥6-7››
ቀኖና (ሥርዐት) የሚወሰነው በሃይማኖት አባቶች እንደሆነና ወንጌልን የሚስተምር ሰው ለሚያስተምራቸው ክርስቲያኖች በሃይማኖት አባቶች የተወሰነ ቀኖና ማስተማርና መሰጠት እንዳለበት መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ሲል ያስረዳል፡፡
በየከተማውም ሲሄዱ፥ ሐዋርያትና ቀሳውስት በኢየሩሳሌም ያዘዙትን /የወሰኑትን/ ሥርዐት አስተማሯቸው፡፡ አብያተ….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ስለ ታቦት

ታቦት ማለት ቤተ፣ አደረ ከሚለው የግዕዝ ቃል የወጣ ነው፡፡ ታቦት ማደሪያነቱ ለጽላተ ኪዳኑ ማደሪያና የእግዚአብሔርም መገለጫ ነው፡፡ ስለዚህ ያሉትን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች እንይ፡፡
1. ኦሪት ዘጸአት 24÷8
እግዚአብሔርም ሙሴን፦ ወደ እኔ ወደ ተራራው ውጣ፥ በዚያም ሁን እነርሱን ታስተምር ዘንድ እኔ የጻፍሁትን ሕግና ትእዛዝ የድንጋይም ጽላት እሰጥሃለሁ አለው።
ሙሴና ሎሌው ኢያሱ ተነሡ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ።
2. ኦሪት ዘጸአት 25÷8-30
8፤እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ርዝመቱ፡ሠላሳ፡ክንድ፥እያንዳንዱም፡መጋረጃ፡ወርዱ፡አራት፡ክንድ፡ይኹን፤የዐሥራ፡አንዱም፡መጋረጃዎች፡መጠናቸው፡ትክክል፡ይኹን።
9፤ዐምስቱ፡መጋረጃዎች፡አንድ፡ኾነው፡ይጋጠሙ፥ስድስቱም፡መጋረጃዎች፡ርስ፡በርሳቸው፡አንድ፡ኾነው፡ይጋጠሙ፤ስድስተኛውም፡መጋረጃ፡በድንኳኑ፡ፊት፡ይደረብ።
10፤ከተጋጠሙት፡መጋረጃዎች፡በአንደኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አድርግ፤ደግሞ፡ከተጋጠሙት፡ከሌላዎቹ፡በአንድኛው፡መጋረጃ፡ዘርፍ፡ላይ፡እንዲሁ፡ዐምሳ፡ቀለበቶች፡አድር።
11፤ዐምሳም፡የናስ፡መያዣዎችን፡ሥራ፥መያዣዎችንም፡ወደ፡ቀለበቶች፡አግባቸው፥ድንኳኑም፡አንድ፡እንዲኾን፡አጋጥመው።
12፤ከድንኳኑ፡መጋረጃዎች፡የቀረ፡ትርፍ፡ግማሽ፡መጋረጃ፡በማደሪያው፡ዠርባ፡ይንጠልጠል።
13፤ማደሪያውን፡እንዲሸፍን፡ከርዝመቱ፡ባንድ፡ወገን፡አንድ፡ክንድ፥ባንድ፡ወገንም፡አንድ፡ክንድ፡
ከድንኳኑ፡መጋረጃዎች፡የቀረው፡ትርፍ፡በማደሪያው፡ውጭ፡በወዲህና፡በወዲያ፡ይንጠልጠል።
14፤ለድንኳኑም፡መደረቢያ፡ከቀይ፡አውራ፡በግ፡ቍርበት፥ከዚያም፡በላይ፡ሌላ፡መደረቢያ፡ከአቍስጣ፡ቍርበት፡አድርግ።
15፤ለማደሪያውም፡የሚቆሙትን፡ሳንቃዎች፡ከግራር፡ዕንጨት፡አድርግ።
16፤የሳንቃው፡ዅሉ፡ርዝመቱ፡ዐሥር፡ክንድ፥ወርዱም፡አንድ፡ክንድ፡ተኩል፡ይኹን።
17፤ለያንዳንዱም፡ሳንቃ፡አንዱን፡በአንዱ፡ላይ፡የሚያያይዙ፡ኹለት፡ማጋጠሚያዎች፡ይኹኑለት፤ለማደሪያው፡ሳንቃዎች፡ዅሉ፡እንዲሁ፡አድርግ።
18፤ለማደሪያውም፡በደቡብ፡ወገን፡ኻያ፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
19፤ከኻያውም፡ሳንቃዎች፡በታች፡አርባ፡የብር፡እግሮችን፡አድርግ፤ከያንዳንዱ፡ሳንቃ፡በታች፡ለኹለት፡ማጋጠሚያዎች፡ኹለት፡እግሮች፡ይኹኑ።
20፤ለማደሪያው፡ለኹለተኛው፡ወገን፡በሰሜን፡በኩል፡ኻያ፡ሳንቃዎች፥
21፤ለእነርሱም፡አርባ፡የብር፡እግሮች፡ይኹኑ፤ከያንዳንዱም፡ሳንቃ፡በታች፡ኹለት፡እግሮች፡ይኹኑ።22፤ለማደሪያውም፡በምዕራቡ፡ወገን፡በስተዃላ፡ስድስት፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
23፤ለማደሪያውም፡ለኹለቱ፡ማእዘን፡በስተዃላ፡ኹለት፡ሳንቃዎችን፡አድርግ።
24፤ከታችም፡እስከ፡ላይ፡እስከ፡አንደኛው፡ቀለበት፡ድረስ፡አንዱ፡ሳንቃ፡ድርብ፡ይኹን፤……ተጨማሪ ያንብቡ ︾

ስለ ታቦት(ጽላት) የሚነሱ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች እና መልሶቻቸው!

1.ታቦት ምንድነው ጽላትስ?
መልስ፡- ጽላት ማለት ቅዱስ ቃሉ
የተጻፈበት ሰሌዳ ማለት ነው(አስርቱ ትዕዛዛት የተጻፈበት)፡፡ ዘጸአት 34፥27-28፡፡
ታቦት ደግሞ የጽላት ማደሪያ ነው፡፡(ጽላቱ የሚቀመጥበት) ዘጸ 40፥20፡፡
2, እንደ ሙሴ ህግ አሰራራቸው ምን ይመስል ነበር?
መልስ፦ ታቦት እንደሙሴ ሕግ የሚዘጋጀው ከግራር እንጨት ሆኖ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፤ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል ቁመቱም አንድ ተኩል ይሁን ይልና በውስጥና በውጭም በጥሩ ወርቅ ለብጠው፤ በዙሪያውም የወርቅ አክሊል አድርግለት ይላል፡፡ ደግሞም ታቦቱን የሚሸከሙት ከወርቅ በተሠሩ መሎጊያዎች አራት ሰዎች እንደሆኑ እንረዳለን፡፡
ጽላትም እንደሙሴ ሕግ ከሆነ መዘጋጀትና መጠረብ ያለበት ከከበረ ድንጋይ ነው፡፡ በአንድ ታቦት ውስጥም መቀመጥ ያለባቸው ሁለት ጽላቶች ናቸው፡፡ ዘጸአት 34፥1፡፡ 
3,የአዲስ ኪዳን ጽላት(ታቦት) አሰራሩ እንዴት ነው?
የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽም ሆነ አጠቃቀሙ የተወሰነውና የሚወሰነው በቀኖና ነው፡፡ ቀኖና ደግሞ እንደ ሁኔታው የሚሻሻል ነው፡፡ (ዶግማ ከሆነ መቀነስም ሆነ መቀነስ አይቻልም ለምሳሌ የ ሥላሴ በአካል ሶስትነት በስልጣን አንድ መሆን ዶግማ ነው።ከጊዜ ጋር የምናሻሽለው አይደለም። ታቦት በአዲስ ኪዳን ግን ቀኖና ስለሆነ አሰራሩን እንደምንችለው መጠን ማድረግ እንችላለን)
እንግዲህ በቤተክርስቲያናችን ቀኖና ካበረከታቸው ነገሮች አንዱ የሐዲስ ኪዳን የታቦትና የጽላት አቀራረጽንና አጠቃቀምን ነው፡፡
ስለዚህ በሐዲስ ኪዳን ታቦትን ለመቅረጽ የግራር እንጨት ባይገኝ በዘፍ 1፥31 ላይ ‹‹ እግዚአብሔርም የፈጠረውን (ያደረገውን) ሁሉ እጅግ መልካም እንደሆነ አየ›› ስለሚልና እግዚአብሔር የፈጠረውን ስለማይንቅ ከግራር ሌላ ከማይነቅዝ እንጨት መቅረጽ እንችላለን፡፡ ቁመቱ ወርዱና ዙሪያውም እንደችሎታችን ይሆናል፡፡ በውስጥና….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

በምስክሩ ታቦት ላይ ሆኜ አነጋግርሃለው

_ዘፀ 25፥22 _ሮሜ 16፥18 _2ኛ ጴጥ 3፥16 _ዘፍ 19፥1 _ኢያ 7፥6 _ዘዳ 32፥7 _ማር 9፥26 _መዝ 95፥9 _ዮሐ 1፥18
_ዮሐ 4፥24
ታቦት ማለት ምን ማለት ነው?
_ዘፀ 25፥22 _1ኛ ሳሙ 3፥18
የታቦት ጥቅም ምንድን ነው?
_ዮሐ 6፥54
ታቦት ጣዖት ነውን?
_ዘፀ 31፥18 _ዘፀ 32፥16 _2ኛ ቆሮ 6፥16 _ማቴ 22፥29 _2ኛ ጢሞ 3፥17
ከሙሴ በኋላ ታቦት የለምን?
_ዘፀ 34፥1-5 _ዘፀ 31፥1-6 _ዘፀ 37፥1
ታቦት ለምን በዛ?
_ዘፀ 34፥1 _ሚል 1፥11 _ሐዋ 8፥27 _ኤር 23፥23
ለምን ታቦት በቅዱሳን ስም ይሰየማል?
_ኢሳ 56፥4 _ሉቃ 10፥20
ታቦት በአዲስ ኪዳን ተሽሯልን?
_ማቴ 5፥19 _ራዕ 11፥19 _ማቴ 5፥17
ታቦት ኃይል የለውምን?
_ማቴ 13፥28 _1ኛ ሳሙ 5፥1 _1ኛ ሳሙ 4፥11 _2ኛ ጴጥ 2፥9 _ማቴ 26፥14
ለታቦት ስግደት አይገባምን?
_ኢያ 24፥15 _ኢያ 7፥6 _ዕብ 13፥7 _ፊሊ 2፥10
ታቦትን መሸከም ጣዖትን መሸከም ነውን?
_ኢሳ 43፥3 _ ኢሳ 66፥1 _መዝ 79፥1 _ዘፍ 1፥26 _ዘፍ 2፥7 _ራዕ 13፥6 _ይሁ 1፥8 _2ኛ ጴጥ 3፥17 _ራዕ 7፥15

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top