ኢየሱስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ

የመናፍቃን የሮሜ 8፡34 የማታለያ ጥቅስ ሲጋለጥ

ከመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ (የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የሐዲስ ኪዳን ትርጓሜ መምህር)

የኢየሱስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ መኾኑን ለማመን የተቸገሩና ፈራጅነቱን የካዱ ተጠራጣሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አንደኛው በሮሜ 8፡34 ላይ ያለው ኀይለ ቃል ነው፡፡ ይኽ “እስመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ሞተ ወተንሥአ እሙታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀስ በእንቲኣነ” (ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል) የሚለው የጠራው የግእዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ኀይለ ቃል በተለየ መልኩ በዘመናት ኹሉ ለዚኽች ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢኾን መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁኑ ፈራርሳ ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ የክርስቶስን ፈራጅነት በካዱ በባሕር ማዶ ቀሳጮች ብዙ ጊዜ ተሰርዞ (ይማልዳል) በሚል ተቀይሮ እናነብባለን፡፡

ለምስክርነት እስቲ እንይ፡- 

በ1938 ዓ.ም ታትሞ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል

በ1975 ዓ.ም ታትሞ ከግእዙ ወደ ዐማርኛው የተመለሰው “ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል፡፡

በ1980 ዓ.ም ግእዙን የሚያውቁ ዐይናማ ሊቃውንት ሳያዩት በጥቂቶች አስተባባሪነት የክርስቶስን ፈራጅነት በማያምኑ በምዕራባውያን የዶላር ድጋፍ የታተመው ደግሞ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል፡፡

ይኽ ዕትም ችግሩ ይኼ ብቻ ሳይኾን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈበትን የግሪክን ቋንቋ እና ቀደምት የተተረጎመትን የግእዝ፣ የሶርያ፣ የአርመን፣ የቅብጥ ቅጅ በተለይ በግሪክ የተጻፈውን የ1900 ዓመት እድሜ ያለውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ከማየት ይልቅ እንግሊዞች እንዲመቻቸው አድርገው ቃላቱን በድፍረት እየጨመሩና እየቀነሱ በ1611 ዓ.ም ያሳተሙትን የ400 ዓመት ዕድሜ ያለውን የኪንግ ጀምስ ቅጂን ወደ ዐማርኛ ተርጒመው ለማቅረብ ሞክረዋል፤

በዚኹ በሮሜ 8፡27 ላይ “ወባሕቱ መንፈስ ለሊሁ ይትዋቀስ ለነ በእንተ ሕማምነ ወምንዳቤነ ወውእቱ የሐትቶ ለልብነ ወየአምር ዘይኄሊ መንፈስ ወይትዋቀስ በኀበ እግዚአብሔር በእንተ ቅዱሳን” (ርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ይመልስልናል፤ ርሱ ልቡናችንን ይመረምረዋል፤ ልብ ያሰበውን ርሱ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ለቅዱሳን ጸሎት መልስ ይሰጣል) የሚለውን ገጸ ንባብ ለውጦ በድፍረት “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” በሚል በድፍረት ቃሉን በመለወጥ መንፈስ ቀዱስንም አማላጅ አድርገው መንፈስ ቅዱስን በመናቅ አሳትመውት እናነብባለን፡፡

ይኽ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈውን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንደገዛ ፈቃዳቸው አጣምመው ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኾንም እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8፡33-34 ላይ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ …… ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” የሚለውን ኀይለ ቃል በዝርዝር ዐይተን ሰዎች በተለያየ ጊዜ የጨመሩበት በባዶ ቦታው ላይ ያለው በእውነት ስለምን እንደሚያስገነዝብ መረዳት እንችላለን እስቲ ከዚኽ በታች እንየው፡-

“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?”

ቅዱስ ጳውሎስ በዚኽ ምዕራፉ ላይ በትክክል እንዳስቀመጠው እግዚአብሔር መራጭ እንደኾነ ነው፤ ከላይ በትክክል እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ በእውነት እግዚአብሔር እንደኾነ የታወቀ የታመነ የተረጋገጠ ነውና ስለዚኽ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አረጋግጦ ጻፈ፤ የመረጣቸውስ ማንን ነው ቢሉ “ንዑ ትልዉኒ” (ኑ ተከተሉኝ) ብሎ የጠራቸው ብሎ ሐዋርያትን፤ ዳግመኛም 72ቱ አርድዕትን፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስትን ነው፤ ይኽነንም ወንጌላዊዉ ማቴዎስ “ዐሥራ ኹለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ርሱ ጠርቶ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ኹሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው” በማለት ፲፪ቱ ሐዋያትን እንደጠራና ሥልጣንን እንደሰጣቸው በትክክል አስቀመጠ፡፡

ራሱ ቅዱስ ጳውሎስም በዚኹ ምዕራፍ ቊ፴ ላይ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” በማለት ሐዋርያት ሰብአ አርድዕት እያለ የሾማቸው ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ልብድዮስ የተባለው ታዴዎስ፤ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እየለ የጠራ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን መሰከረ፡፡

“የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው” በማለት የጠራቸውን የሐዋርያት ነገራቸው ወንጌልን በተአምራት እያስረዳ እያጸደቀ እውነት መኾኑን ሰዎች እንዲያውቁት ያደረገው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን አስረዳ፡፡ ከዚያም “ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” የጠራቸው ሐዋርያቱን በዚኽም ዓለም በተአምራት በወዲያኛውም ዓለም “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” (ማቴ 19፡28) በማለት ያከበረው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በትክክል እንዳስተማረ በቊ 32 ላይ ላይም “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት ማንም ሊወቅሳቸው የማይችለውን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመረጠው ፍጹም እግዚአብሔር የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ገለጸ፡፡

የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል በዚኽ ላይም ማጽደቅ እና መኰነን የሚችል ርሱ ልዑል እግዚአብሔር እንደኾነ በትክክል አስቀምጧል፤ እውነት ነው ዓለምን በታላቅ ግርማ አሳልፎ መላእክቱን አስከትሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ለኹሉም እንደ የሥራው የሚከፍለው፤ ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሎ የሚያጸድቅ፤ በግራው የቆሙትን ኃጥኣንን ደግሞ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” በማለት የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ገለጸ፡፡ ራሱ ጌታ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል” በማለት እንዳስተማረን (ማቴ 25፡31-46)፡፡ ታዲያ ማጽደቅና እና መኰነን የፍርድ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ ነውን በፍጹም አይደለም፡፡

“የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው”

ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያትን የጠራው፣ የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብ

ሔር መኾኑን በትክክል ካስረዳ በኋላ በመቀጠልም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ባባቱ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በትክክል አስተማረ፤ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሣቱም ፊተኛው እና ኋለኛው ርሱ ስለመኾኑ ራሱ ጌታ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ” በማለት ይኽነን እውነት እንዲጽፍ ለዮሐንስ እንዳዘዘው ቅዱስ ጳውሎስም እውነቱን መሰከረ፡፡

ወንጌላዊ ማርቆስም ስለዚኽ ነገር “ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር 16፡19) በማለት ባባቱ ዕሪና መቀመጡን እንደነገረን ቅዱስ ጳውሎስም በድጋሚ ይኽነን አስተማረ፡፡

ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ፡- “እግዚአብሔር ጌታዬን፡- ጠላቶችኽን በእግርኽ መረገጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ብሎ እንደተነበየ /መዝ.፻፱ (፻፲)፡፩/ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይኽ ትንቢት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ አስተምሯል /ዕብ.፲፡፲፪/፡፡

ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የሉቃስ ወንጌልን በተረጐመበት ፳፬ኛው ምዕራፍ ላይ ይኽን በተመለከተ ሲናገር እንዲኽ ይላል፡- “ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝ (ዕሪናም) ተቀመጠ፡፡ የተቀመጠውም በባሕርየ መለኮቱ ብቻ አይደለም፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ጭምር እንጂ፡፡ አካላዊ ቃል ባሕርያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና፡፡ … እግዚአብሔር ሲኾን ስለ እኛ ሰው ኾነ፡፡ በፍቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል”

አኹን ለመለኮት የተገደበ የተወሰነ ቀኝ ግራ ፊት ኋላ አለው ማለትም አይደለም ቀኝ ማለት ኀይል ምልአትን በዕሪና መተካከልን የሚያመለክት ብቻ ነው ሊቁ “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ ወዕሪናሆሙ በክብር” (ቀኝ ማለት በክብር መተካከላቸውን ተዋሕዶቸውን ያመለክታል) እንዳለ፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ)፤ ይሉታል እንጂ እንደ ባለቤት “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ለዐይን ጥቅሻ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ አልተለየምና “ነበረ” ይለዋል፤ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 1፡3 ላይ “በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” በማለት የጻፈው፡፡

እስኪ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቀኝ የሚለውን ኅሊናን በመሰብሰብ እንየው፡፡

“እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ” (መዝ 109፡1)

“እኔ ነኝ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ (መዝ 48፡12-13)

እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ማቴ 22፡43-44

“አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ” (ዘፀ 15፡6)

“አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው” (ዘፀ 15፡11-12)

“የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” መዝ 117፡15-16)

“ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ” ማር 14፡62 ይላል፡፡

በመኾኑም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን የጠራው የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለመኾኑና ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአብ ቀኝ (ዕሪና) እንዳለ ከገለጸ በኋላ በዕለተ ዐርብ ባደረገው የድኅነት ምስጢር ዓለምን አድኖ ዋጋችንን የሰጠን ዳግመኛም በታላቅ ጌትነት ለፍርድ ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና “ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” በማለት በትክክል ተናገረ እንጂ፤ ምክንያቱም ከላይ ዠምሮ የጥቅሱን ሐሳብ እንዳየነው ሙሉ ነገሩ የክርስቶስን እግዚአብሔርነት፣ መራጭነት፣ አጽዳቂነት፣ ኰናኝነት፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት፣ በአብ ዕሪና መቀመጥ ብቻ ነው፤ ታዲያ ራሱ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር ከኾነና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ አንሶ ወደ ማን ሊማልድ ነው ይባላል? ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንዳንል በአምላክነት፣ በፈጣሪነት፣ በቅድምና፣ በእግዚአብሔርነት፣ በዕበይ፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን፣ በመመለክ፣ በመመስገን፣ በገናንነት፣ በክብር፣ በኀይል፣ በክሂል፣ በፈቃድ፣ በትእዛዝ አንድ ናቸው፡፡

ስለዚኽ ከጊዜ በኋላ እነዚኽ ቀሳጮች ምስጢረ ሥላሴን አፋልሰው የማይለየውን አንድነት ለመበታተን እንዲመቻቸው በማድረግ አስገብተውበታል እንጂ ክብር ይግባውና ጌታስ በዘመነ ሥጋዌዉ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ዓለምን ከራሱ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ ዳግመኛም ታረቀ ከዚያም የማስታረቅን ቃል ለሐዋርያት ሰጥቶ በክብሩ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል እንጂ አኹንም እንደገና ያደነውን ዓለም እንደገና እንዳልዳነ አኹንም መልሶ ይማልዳል ማለት ሎቱ ስብሐት ጠላት ዲያብሎስ የዘራው መርዝ ኑፋቄ ክሕደት ነው፡፡

ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ቆሮ 5፡18-20 “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” በማለት የማስታረቅ አገልግሎት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን አበው የተሰጠ መኾኑን ትክክለኛውን ትምህርት ያስተማረው፡፡

እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሌሎችም በተጠራጣሪዎች የሚነሱ ጥቅሶችንም ወደፊት ተንትነን እናያለን፡፡

መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

ነገረ ክርስቶስ ከሚለው መጽሐፌ የተወሰደ

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የቀናውን እውነት የኾነውን የሐዋርያትን ትምህርት ሳትበርዝ ሳትከልስ ሳትቈራርጥ ያስተማረችውን በደምህ የመሠረትካትን ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችንን ጠብቅልን፡፡

የሚኰንንስ ማን ነው? … ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው

ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ ፰:፴፫

፴፫    እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

፴፬    የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።

የሚማልደው የሚለው ቃል ከ1940 በፊት ያለው መፅሀፍ ቅዱስ ላይ “የሚፈርደው” ነው የሚለው። ሮሜ 8:34፤ በግሪክ:- “τίς ὁ κατακρινῶν; Χριστὸς [Ἰησοῦς] ὁ ἀποθανών, µᾶλλον δὲἐγερθείς, ὃς καί ἐστιν ἐν δεξιᾷ τοῦ θεοῦ, ὃς καὶ ἐντυγχάνει ὑπὲρ ἡµῶν.” ሲተረጎም፡- “THE who condemns? Liniments [Jesus] who died, he arose, number and Estin In dexiᾷ of GOD, number and entynchanei for us.”

Entynchanei :- ይህ ቃል ሲተረጎም “pleads our cause” ማለት ነው፡፡ “pleads our cause” የሚለው ቃል ደግሞ ሲተረጎም ልክ እንደግእዙ በተለያየ ቦታ የተለያየ ትርጉም ይዞ እናገኘዋለን፡፡ ለምሳሌ ይህንኑ ቃል በመዝሙር 119(120) ፥154 ላይ እንዲህ ተጽፎ እናገኘዋለን፡፡ “plead my cause and redeem me; revive me according to your word.” በአማርኛው “ፍርዴን ፍረድ አድነኝም ስለ ቃልህ ሕያው አድርገኝ፡፡” ይላል፡፡ ታዲያ የግእዙ ትርጓሜ የሚስማማው ከየትኛው ጋር ነው? አማልደኝ ነው ወይስ ፍረድልኝ?

በአሁን ሰዓት በእንግሊዘኛ እና በአማርኛ ተጽፎ የምናገኘው አብዛኛው መጽሐፍ ቅዱስ የሉተር ተከታዮች የጻፉት ነው፡፡ ይህንን ቃል እነሱ ለራሳቸው እንደሚስማማ አድርገው ተርጉመውታል፡፡ ውሉደ ሉተር ፕሮቴስታቶች እነርሱ በያዙት መጽሐፍ ቅዱስ እንኳ በሮሜ 8:34 ላይ “የሚማልደው” ተብሏልና ክርስቶስን አማላጅ ነው ይላሉ በነሱ አካሄድ ብንሄድማ መንፈስ ቅዱስንም አማላጅ ሊሉ ነዋ ምክንያቱም “መንፈስ ራሱ በማይናገር መቃተት ይማልዳል” ሮሜ 8:26 ይላልና:: እንዲህ ተብለው ሲጠየቁ በሮሜ 8:26 ያለው ቃል መንፈስ ቅዱስን አማላጅ ለማለት አይደለም፡፡ ትርጉሙ…” በማለት ለመተርጎም ይነሳሉ፡፡ ሮሜ 8:34 ላይ የሰፈረውን ቃል ግን ሊያስተውሉ አይወዱም፡፡ ከፍ ብለው ቢያነቡ ክብር ይግባውና መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ሳይሆን ፈራጅ ጌታ መሆኑን ይረዱ ነበር፡፡

ከሮሜ 8፦33 ጀምሮ ስናነብብ እንዲህ ይላል። ” የሚያፀድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኮንንስ ማነው ?” እንዲህ ማለቱ የማፅደቅ (መንግስቱን የማወረስ) እናንተ ያባቴ ብሩካን አለም ከተፈጠረ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግስት ውረሱ ማቴ 25፦34 በማለት መንግስቱን (መንግስተ ሰማያትን) የሚያወርስ እርሱ ኢየሱስ ነው በማለት ተናገረ። ቀጥሎም “የሚኮንንስ ማነው?” አለ። መኮነን የሚለው ቃል ‘ኮነነ’ ከሚለው የግዕዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ፈረደ፣ ገዛ ማለት ነው። በእግሊዘኛውም “who is he that condemneth?” ይላል፡፡ “Condemn” ማለት መፍረድ ነውና፡፡ እንግዲህ ልብ እንበል ማፅደቅና መኮነን የፈራጅ ስራዎች እንጂ የአማላጅ እንዳልሆኑ እናስተውል።

ቀጥሎም “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በማለት አሁን ያለበትን ቦታ ገለፀ። ለመለኮት ቀኝ ግራ ብለን ስፋትና ወሰን አበጅተን የማንናገርለት በሁሉ ምሉዕ ነው። ቀኝ ብሎ መናገሩ የክርስቶስን ፍፁም ሃይልና ስልጣን ሲናገር ነው። ታድያ አፅዳቂ፣ ኮናኝ ከሆነ በፍፁም ሃይል የሚገኝውን መድኃኔአለም ክርስቶስን አማላጅ ማለት እንዴት ያለ አለማስተዋል ነው፡፡ የክርሰቶስን ፈራጅነት የሚገለጥ ነውና፡፡

እንግዲህ የኢየሱስን የባሕርይ አምላክነትና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ መኾኑን ለማመን የተቸገሩና ፈራጅነቱን የካዱ ተጠራጣሪዎች ከሚያቀርቧቸው ጥያቄዎች አንደኛው በሮሜ 8፡34 ላይ ያለው ኀይለ ቃል ነው፡፡ ይኽ “እስመ ለሊሁ ያጸድቅ መኑ ዘይኴንን ክርስቶስ ሞተ ወተንሥአ እሙታን ወሀሎ ይነብር በየማነ እግዚአብሔር ወይትዋቀስ በእንቲኣነ” (ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል) የሚለው የጠራው የግእዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ኀይለ ቃል በተለየ መልኩ በዘመናት ኹሉ ለዚኽች ቤተ ክርስቲያን መቼም ቢኾን መልካም ዐስበው በማያውቁ ይልቁኑ ፈራርሳ ቢያይዋት ደስ በሚሰኙ የክርስቶስን ፈራጅነት በካዱ በባሕር ማዶ ቀሳጮች ብዙ ጊዜ ተሰርዞ (ይማልዳል) በሚል ተቀይሮ እናነብባለን፡፡

ለምስክርነት እስቲ እንይ፡-

በ1938 ዓ.ም ታትሞ የነበረው መጽሐፍ ቅዱስ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሣ፤ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፤ ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል።

በ1975 ዓ.ም ታትሞ ከግእዙ ወደ ዐማርኛው የተመለሰው “ርሱ ሲያጸድቅ የሚፈርድ ማነው ክርስቶስ ሙቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል” ይላል፡፡

በ1980 ዓ.ም ግእዙን የሚያውቁ ዐይናማ ሊቃውንት ሳያዩት በጥቂቶች አስተባባሪነት የክርስቶስን ፈራጅነት በማያምኑ በምዕራባውያን የዶላር ድጋፍ የታተመው ደግሞ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” ይላል፡፡

ይኽ ዕትም ችግሩ ይኼ ብቻ ሳይኾን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ የተጻፈበትን የግሪክን ቋንቋ እና ቀደምት የተተረጎመትን የግእዝ፣ የሶርያ፣ የአርመን፣ የቅብጥ ቅጅ በተለይ በግሪክ የተጻፈውን የ1900 ዓመት እድሜ ያለውን የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ ከማየት ይልቅ እንግሊዞች እንዲመቻቸው አድርገው ቃላቱን በድፍረት እየጨመሩና እየቀነሱ በ1611 ዓ.ም ያሳተሙትን የ400 ዓመት ዕድሜ ያለውን የኪንግ ጀምስ ቅጂን ወደ ዐማርኛ ተርጒመው ለማቅረብ ሞክረዋል፤

በዚኹ በሮሜ 8፡27 ላይ “ወባሕቱ መንፈስ ለሊሁ ይትዋቀስ ለነ በእንተ ሕማምነ ወምንዳቤነ ወውእቱ የሐትቶ ለልብነ ወየአምር ዘይኄሊ መንፈስ ወይትዋቀስ በኀበ እግዚአብሔር በእንተ ቅዱሳን” (ርሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ይመልስልናል፤ ርሱ ልቡናችንን ይመረምረዋል፤ ልብ ያሰበውን ርሱ መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፤ በእግዚአብሔር ዘንድም ለቅዱሳን ጸሎት መልስ ይሰጣል) የሚለውን ገጸ ንባብ ለውጦ በድፍረት “ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል ልብንም የሚመረምረው የመንፈስ ዐሳብ ምን እንደ ሆነ ያውቃል፥ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” በሚል በድፍረት ቃሉን በመለወጥ መንፈስ ቀዱስንም አማላጅ አድርገው መንፈስ ቅዱስን በመናቅ አሳትመውት እናነብባለን፡፡

ይኽ እንደ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ የተጻፈውን ቅዱስ ቃል ሰዎች እንደገዛ ፈቃዳቸው አጣምመው ለማቅረብ የሚሞክሩ ቢኾንም እስቲ ቅዱስ ጳውሎስ በሮሜ 8፡33-34 ላይ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው የሚኰንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለ እኛ …… ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” የሚለውን ኀይለ ቃል በዝርዝር ዐይተን ሰዎች በተለያየ ጊዜ የጨመሩበት በባዶ ቦታው ላይ ያለው በእውነት ስለምን እንደሚያስገነዝብ መረዳት እንችላለን እስቲ ከዚኽ በታች እንየው፡-

“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?”

ቅዱስ ጳውሎስ በዚኽ ምዕራፉ ላይ በትክክል እንዳስቀመጠው እግዚአብሔር መራጭ እንደኾነ ነው፤ ከላይ በትክክል እንዳየነው በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንደሰፈረው ኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የተካከለ በእውነት እግዚአብሔር እንደኾነ የታወቀ የታመነ የተረጋገጠ ነውና ስለዚኽ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት የኢየሱስ ክርስቶስን እግዚአብሔርነት አረጋግጦ ጻፈ፤ የመረጣቸውስ ማንን ነው ቢሉ “ንዑ ትልዉኒ” (ኑ ተከተሉኝ) ብሎ የጠራቸው ብሎ ሐዋርያትን፤ ዳግመኛም 72ቱ አርድዕትን፣ 36ቱ ቅዱሳት አንስትን ነው፤ ይኽነንም ወንጌላዊዉ ማቴዎስ “ዐሥራ ኹለቱን ደቀ መዛሙርቱን ወደ ርሱ ጠርቶ እንዲያወጡአቸው በርኩሳን መናፍስት ላይ ደዌንና ሕማምንም ኹሉ እንዲፈውሱ ሥልጣን ሰጣቸው” በማለት ፲፪ቱ ሐዋያትን እንደጠራና ሥልጣንን እንደሰጣቸው በትክክል አስቀመጠ፡፡

ራሱ ቅዱስ ጳውሎስም በዚኹ ምዕራፍ ቊ፴ ላይ “አስቀድሞም የወሰናቸውን እነዚህን ደግሞ ጠራቸው፤ የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው፤ ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” በማለት ሐዋርያት ሰብአ አርድዕት እያለ የሾማቸው ስምዖን የተባለውን ጴጥሮስ ልብድዮስ የተባለው ታዴዎስ፤ ዲዲሞስ የተባለውን ቶማስ እየለ የጠራ ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን መሰከረ፡፡

“የጠራቸውንም እነዚህን ደግሞ አጸደቃቸው” በማለት የጠራቸውን የሐዋርያት ነገራቸው ወንጌልን በተአምራት እያስረዳ እያጸደቀ እውነት መኾኑን ሰዎች እንዲያውቁት ያደረገው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ መኾኑን አስረዳ፡፡ ከዚያም “ያጸደቃቸውንም እነዚህን ደግሞ አከበራቸው” የጠራቸው ሐዋርያቱን በዚኽም ዓለም በተአምራት በወዲያኛውም ዓለም “እውነት እላችኋለሁ፥ እናንተስ የተከተላችሁኝ፥ በዳግመኛ ልደት የሰው ልጅ በክብሩ ዙፋን በሚቀመጥበት ጊዜ፥ እናንተ ደግሞ በአሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገድ ስትፈርዱ በአሥራ ሁለት ዙፋን ትቀመጣላችሁ” (ማቴ 19፡28) በማለት ያከበረው ራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን በትክክል እንዳስተማረ በቊ 32 ላይ ላይም “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” በማለት ማንም ሊወቅሳቸው የማይችለውን ቅዱሳን ሐዋርያትን የመረጠው ፍጹም እግዚአብሔር የኾነው ኢየሱስ ክርስቶስ መኾኑን ገለጸ፡፡

የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው፥ የሚኰንንስ ማን ነው?

ቅዱስ ጳውሎስ በትክክል በዚኽ ላይም ማጽደቅ እና መኰነን የሚችል ርሱ ልዑል እግዚአብሔር እንደኾነ በትክክል አስቀምጧል፤ እውነት ነው ዓለምን በታላቅ ግርማ አሳልፎ መላእክቱን አስከትሎ በዙፋኑ ተቀምጦ ለኹሉም እንደ የሥራው የሚከፍለው፤ ጻድቃንን በቀኙ አቁሞ “እናንተ የአባቴ ቡሩካን፥ ኑ፤ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ” ብሎ የሚያጸድቅ፤ በግራው የቆሙትን ኃጥኣንን ደግሞ “እናንተ ርጉማን፥ ለሰይጣንና ለመላእክቱ ወደ ተዘጋጀ ወደ ዘላለም እሳት ከእኔ ሂዱ” በማለት የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር መኾኑን በትክክል ገለጸ፡፡ ራሱ ጌታ “የሰው ልጅ በክብሩ በሚመጣበት ጊዜ ከእርሱም ጋር ቅዱሳን መላእክቱ ሁሉ፥ በዚያን ጊዜ በክብሩ ዙፋን ይቀመጣል አሕዛብም ሁሉ በፊቱ ይሰበሰባሉ፤ እረኛም በጎቹን ከፍየሎች እንደሚለይ እርስ በርሳቸው ይለያቸዋል በጎችን በቀኙ ፍየሎችንም በግራው ያቆማቸዋል” በማለት እንዳስተማረን (ማቴ 25፡31-46)፡፡ ታዲያ ማጽደቅና እና መኰነን የፍርድ ሥራ እንጂ የማማለድ ሥራ ነውን በፍጹም አይደለም፡፡

“የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው”

ቅዱስ ጳውሎስ ሐዋርያትን የጠራው፣ የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብ

ሔር መኾኑን በትክክል ካስረዳ በኋላ በመቀጠልም ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ ባባቱ በእግዚአብሔር አብ ቀኝ መቀመጡን “የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሣው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በትክክል አስተማረ፤ ሞትን ድል አድርጎ ስለመነሣቱም ፊተኛው እና ኋለኛው ርሱ ስለመኾኑ ራሱ ጌታ “ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ” በማለት ይኽነን እውነት እንዲጽፍ ለዮሐንስ እንዳዘዘው ቅዱስ ጳውሎስም እውነቱን መሰከረ፡፡

ወንጌላዊ ማርቆስም ስለዚኽ ነገር “ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ” (ማር 16፡19) በማለት ባባቱ ዕሪና መቀመጡን እንደነገረን ቅዱስ ጳውሎስም በድጋሚ ይኽነን አስተማረ፡፡ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት አስቀድሞ፡- “እግዚአብሔር ጌታዬን፡- ጠላቶችኽን በእግርኽ መረገጫ እስካደርግልኽ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው” ብሎ እንደተነበየ /መዝ.፻፱ (፻፲)፡፩/ በአብ ቀኝ ተቀምጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም ይኽ ትንቢት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ እንደተፈጸመ አስተምሯል /ዕብ.፲፡፲፪/፡፡

ዓምደ ሃይማኖት የተባለው ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ የሉቃስ ወንጌልን በተረጐመበት ፳፬ኛው ምዕራፍ ላይ ይኽን በተመለከተ ሲናገር እንዲኽ ይላል፡- “ደቀ መዛሙርቱን ከባረካቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በአባቱ ቀኝ (ዕሪናም) ተቀመጠ፡፡ የተቀመጠውም በባሕርየ መለኮቱ ብቻ አይደለም፤ በተዋሐደው ሰውነቱም ጭምር እንጂ፡፡ አካላዊ ቃል ባሕርያችንን ሲዋሐድ እኛን ወደዚኽ ክብር ለመመለስ ነበርና፡፡ … እግዚአብሔር ሲኾን ስለ እኛ ሰው ኾነ፡፡ በፍቃዱ መከራ መስቀልን በተዋሐደው ሰውነቱ ተቀበለ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱ ሙስና መቃብርን አጥፍቶ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ፡፡ በተዋሐደው ሰውነቱም ዐረገ፡፡ በሕያዋንና በሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድም ዳግመኛ በክበበ ትስብእት ይመጣል” /Commentary on Luke, Chap.24/፡፡

አኹን ለመለኮት የተገደበ የተወሰነ ቀኝ ግራ ፊት ኋላ አለው ማለትም አይደለም ቀኝ ማለት ኀይል ምልአትን በዕሪና መተካከልን የሚያመለክት ብቻ ነው ሊቁ “እስመ ብሂለ የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ ወዕሪናሆሙ በክብር” (ቀኝ ማለት በክብር መተካከላቸውን ተዋሕዶቸውን ያመለክታል) እንዳለ፤ እንግዳን “ንበር” (ተቀመጥ)፤ ይሉታል እንጂ እንደ ባለቤት “ነበረ” (ተቀመጠ) እንዳይሉት ለዐይን ጥቅሻ እንኳን ኢየሱስ ክርስቶስ ከክብሩ አልተለየምና “ነበረ” ይለዋል፤ ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በዕብ 1፡3 ላይ “በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ” በማለት የጻፈው፡፡

እስኪ እንደ መጽሐፍ ቅዱሱ ቀኝ የሚለውን ኅሊናን በመሰብሰብ እንየው፡፡

“እግዚአብሔር ጌታዬን፦ ጠላቶችህን ለእግርህ መቀመጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው እግዚአብሔር የኃይልን በትር ከጽዮን ይልክልሃል በጠላቶችህም መካከል ግዛ” (መዝ 109፡1)

“እኔ ነኝ እኔ ፊተኛው ነኝ እኔም ኋለኛው ነኝ እጄም ምድርን መሥርታለች ቀኜም ሰማያትን ዘርግታለች በጠራኋቸው ጊዜ በአንድነት ይቆማሉ (መዝ 48፡12-13)

እንኪያስ ዳዊት፦ ጌታ ጌታዬን። ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ አለው ሲል እንዴት በመንፈስ ጌታ ብሎ ይጠራዋል? ማቴ 22፡43-44

“አቤቱ፥ ቀኝህ በኃይል ከበረ” (ዘፀ 15፡6)

“አቤቱ፥ በአማልክት መካከል እንደ አንተ ያለ ማን ነው? ቀኝህን ዘረጋህ፥ ምድርም ዋጠቻቸው” (ዘፀ 15፡11-12)

“የእልልታና የመድኃኒት ድምፅ በጻድቃን ድንኳን ነው የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች የእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ከፍ አደረገችኝ የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” መዝ 117፡15-16)

“ኢየሱስም፦ እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም በኃይል ቀኝ ሲቀመጥ በሰማይም ደመና ሲመጣ ታያላችሁ አለ” ማር 14፡62 ይላል፡፡

በመኾኑም ቅዱስ ጳውሎስ ቅዱሳን ሐዋርያቱን የጠራው የሚያጸድቀው የሚኰንነው ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ስለመኾኑና ሞትን ድል አድርጎ ተነሥቶ በአብ ቀኝ (ዕሪና) እንዳለ ከገለጸ በኋላ በዕለተ ዐርብ ባደረገው የድኅነት ምስጢር ዓለምን አድኖ ዋጋችንን የሰጠን ዳግመኛም በታላቅ ጌትነት ለፍርድ ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነውና “ደግሞ ስለ እኛ የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው” በማለት በትክክል ተናገረ እንጂ፤ ምክንያቱም ከላይ ዠምሮ የጥቅሱን ሐሳብ እንዳየነው ሙሉ ነገሩ የክርስቶስን እግዚአብሔርነት፣ መራጭነት፣ አጽዳቂነት፣ ኰናኝነት፣ ሞትን ድል አድርጎ መነሣት፣ በአብ ዕሪና መቀመጥ ብቻ ነው፤ ታዲያ ራሱ ክርስቶስ ፍጹም እግዚአብሔር ከኾነና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ አንሶ ወደ ማን ሊማልድ ነው ይባላል? ወደ አብ ወደ መንፈስ ቅዱስ እንዳንል በአምላክነት፣ በፈጣሪነት፣ በቅድምና፣ በእግዚአብሔርነት፣ በዕበይ፣ በመንግሥት፣ በሥልጣን፣ በመመለክ፣ በመመስገን፣ በገናንነት፣ በክብር፣ በኀይል፣ በክሂል፣ በፈቃድ፣ በትእዛዝ አንድ ናቸው፡፡

ስለዚኽ ከጊዜ በኋላ እነዚኽ ቀሳጮች ምስጢረ ሥላሴን አፋልሰው የማይለየውን አንድነት ለመበታተን እንዲመቻቸው በማድረግ አስገብተውበታል እንጂ ክብር ይግባውና ጌታስ በዘመነ ሥጋዌዉ በዕለተ ዐርብ ባደረገው ተልእኮ ዓለምን ከራሱ፣ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር አስታረቀ ዳግመኛም ታረቀ ከዚያም የማስታረቅን ቃል ለሐዋርያት ሰጥቶ በክብሩ ተቀመጠ ዳግመኛም በሕያዋንና በሙታን ላይ ለመፍረድ በጌትነት ይመጣል እንጂ አኹንም እንደገና ያደነውን ዓለም እንደገና እንዳልዳነ አኹንም መልሶ ይማልዳል ማለት ሎቱ ስብሐት ጠላት ዲያብሎስ የዘራው መርዝ ኑፋቄ ክሕደት ነው፡፡

ለዚኽ ነው ቅዱስ ጳውሎስ በ2ቆሮ 5፡18-20 “ነገር ግን የሆነው ሁሉ፥ በክርስቶስ ከራሱ ጋር ካስታረቀን የማስታረቅም አገልግሎት ከሰጠን፥ ከእግዚአብሔር ነው እግዚአብሔር በክርስቶስ ሆኖ ዓለሙን ከራሱ ጋር ያስታርቅ ነበርና፥ በደላቸውን አይቆጥርባቸውም ነበር፤ በእኛም የማስታረቅ ቃል አኖረ እንግዲህ እግዚአብሔር በእኛ እንደሚማለድ ስለ ክርስቶስ መልክተኞች ነን፤ ከእግዚአብሔር ጋር ታረቁ ብለን ስለ ክርስቶስ እንለምናለን” በማለት የማስታረቅ አገልግሎት ለቅዱሳን ሐዋርያት ለቤተ ክርስቲያን አበው የተሰጠ መኾኑን ትክክለኛውን ትምህርት ያስተማረው፡፡ እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሌሎችም በተጠራጣሪዎች የሚነሱ ጥቅሶችንም ወደፊት ተንትነን እናያለን፡፡

ኢየሱስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ?

በ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፦ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለ እኛ ይፈርዳል”። በ1975 ዓ.ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመውም እንዲህ ይላል፦ “የሚፈርድ ማን ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል።”
በአሁኑ ሰዐት ከኦርቶዶክሳውያን በቀር በአብዝሃኛው ሕዝብ ተሰራጭቶ የሚገኘው እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው:: የሚኮንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በሮሜ 8:-34 ላይ በተለያዩ ዘመናት የተጻፉ መጽሐፍ ቅዱሶችን ተመልክተናል። ቀድሞ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ይፈርዳል ብሎ ፈራጅ ሲያደርገው በብዙወቻችን እጅ አሁን የሚገኘው አዲሱ ትርጉም አማ ላጅ አድርጎታል። ታዲያ ትክክለኛው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል የትኛው ነው? ብለን ስንጠይቅ መረዳት የምንችለው አንድም ቀዳሚውን በመመልከት ካልሆነ ደግሞ ከምንባቡ ሃሳብ በመነሳት ነው። ስለዚህ ቀጥለን በዝርዝር እንመልከተው። ቁጥር 33 ላይ እንዲህ ሲል ይጀምራል:-“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” ይህ ማለት እግዚአብሔር ተከተሉኝ ብሎ በመጥራት የመረጣቸውን አይ እነርሱ አያስፈልጉንም ፣ አንተን ሊከተሉ አይገባቸውም ብሎ የሚከሳቸው ማን ነው? በማለት ይጠይቃል በመቀጠልም “የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።” በማለት የመረጣቸውን ሰዎች መንግሥቱን ለማውረስ እናንተ የአባቴ ብሩካን የሚያጸድቃቸው እግዚአብሔር ነው አለ፤ እንዲሁም የሚኮንን (የሚፈርድ) ማን ነው? በማለት ይጠይቃል። “መኮነን” ከግዕዙ ሳይተረጎም ቀጥታ የተወሰደ ቃል ሲሆን “ መኮነን“ ማለት መፍረድ ማለት ነው። ምክንያቱም “ኮነነ” ከሚለው የግዕዝ ሥርዎ ቃል የወጣ ነው። “ኮነነ” ማለት ደግሞ ፈረደ ፣ ገዛ ማለት ነው።እንግዲህ ማጽደቅና መኮነን የተለያዩ ትርጉም እንዳላቸው ማስተዋል ያስፈልጋል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ካልሆነ እውነታው ይህ ነው። ማጽደቅና መኮነን የአማላጅነት ሥራ ሳይሆን የፈራጅነት ሥራ እንደሆነ ልብ እንበል። በመቀጠልም የሚኮንንስ ማን ነው? ብሎ ለጠየቀው ጥያቄ መልስ ሲሰጥ ቁጥር 34 የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” በማለት አሁን ያለበትን ስፍራ ይገልጻል። የሞተውና ሞትን ድል አድርጎ በሥልጣኑ የተነሳው ኢየሱስ ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ አለ ማለት ነው። መቼም እግዚአብሔር ቀኝና ግራ ፊትና ኋላ እንደ ፍጡር የለውም እርሱ ስፍራ የማይወስነው ረቂቅ ነው። የነፋስን ቀኝና ግራ የሚያውቅ ማን ነው ከነፋስ ይልቅ ነፍስ ትረቃለች ከነፍስ ደግሞ መላእክት ይረቃሉ። ከመላእክት ደግሞ የበለጠ እግዚአብሔር ይረቃል ስለዚህ በሁሉም ቦታ ምሉዕ ነው። ታዲያ በእግዚአብሔር ቀኝ ሲል ምን ማለት ነው? ብለን ስንጠይቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ዉስጥ ቀኝ የተለያየ ትርጉም ቢኖረውም በዚህ ምዕራፍ ላይ ግን ክብርን ፣ ስልጣንን ያመለክታል።በመዝሙር 117:-16 “የእግዚአብሔር ቀኝ ኃይልን አደረገች” ይላል። ይህ ማለት እግዚአብሔር በስልጣኑ ኃይልን እንዳደረገ የሚገልጽ ነው።ምክንያቱም እግዚአብሔር ኃይልን የሚያደርገው ሰዎችንም ከፍ ከፍ የሚያደርገው በሥልጣኑ በመለኮታዊ ኃይሉ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም የእግዚአብሔር ቀኝ ሲል ሥልጣኑን \መለኮታዊ ክብሩን\ ያመለክታል።በዘፀ 15:-12 ላይ “ቀኝህን ዘረጋህ ምድርም ዋጠቻቸው” ይላል ከዚህ የምንረዳው ግብጻውያንን እግዚአብሔር በስልጣኑ ምድር እንድትውጣቸው ማድረጉን ነው። ስለዚህ “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው” ማለቱ በስልጣንና በክብር በሰማያት ያለው ማለቱ ነው። ይህም ማለት ክርስቶስ ቀድሞ ሥጋ ከምልበሱ በፊት ክብር የሌለው ሆኖ በኋላ ክብር አገኘ ማለት አይደለም ክብርና ሥልጣኑ ቅድመ ተዋሕዶ ጊዜ ተዋሕዶ ድህረ ተዋሕዶ ከባህርይ አባቱ ከአብ ከባህርይ ህይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል ነው።በመቀጠል እንዲህ ይላል “በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ  ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በክፍት ቦታው ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን ሙሉ ብንባል ያለጥርጥር የሚፈርደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው የሚለውን ነው። ምክንያቱም ከላይ በዝርዝር እንዳየነው ጥቅሱ የሚያመለክተው ፈራጂነቱን እንጂ አማላጅነቱን በፍጹም አይደለም። ማጽደቅና መኮነን ከቻለ እንዲሁም በእግዚአብሔር ቀኝ \ክብር\ ካለ እርሱ የክብር ባለቤት ፈራጅ እንጂ አማልጅ አይሆንም። ደግሞ “የሚኮንን ማንነው?” የሚለውና “ስለኛ የሚማልደው” የሚሉት ሁለት ቃላት \ሐሳቦች\ \ርስ በርሳቸው እንዳይጋጩ አስማምቶ መተርጎም ያስፈልጋል። ንባቡን ይዞ መሮጥ ግን ወደ ባሰ ጥፋት የሚያመራ መሆኑንም ሐዋርያው አስረጝቶ አስረድቷል ትርጉም ያድናል ንባብ ይገድላል በማለት። ስለዚህ ማስተዋል ግድ ይለናል!!!

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top