መዳን በሌላ በማንም የለም

“መዳን በሌላ በማንም የለም” /ሐዋ. 4፥12/

በመጀመሪያ ቃሉን ማን ተናገረው የት ቦታ ተናገረው መቼ ተናገረው በምን ምክንያት ተናገረው ብለን በደንብ ማየት ተገቢ ነው ቃሉን የተናገረው ሐዋሪያው ቅዱስ ጴጥሮስ ነው በመቅደስ ደጃፍ ከእናቱ ማህጸን ጀምሮ አንካሳ ሆኖ የተወለውን ምስኪን ቅዱስ ጴጥሮስ በናዝሪቱ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ተነሳና ተመላላስ ባለው ጊዜ እግሮቹ ቀንተውለት ቆሙ የካህናት አለቆችና ሽማግሌዎች ጻፎች ሊቃነ ካህናቱም ሐና እና ቀያፋ ጴጥሮስ ዮሐንስንይዘው በምነ ሐይል ወይም በማን ስም ይህን አደረጋችሁ ቢሏቸው እናንተስ ሰቅላችሁ በገደላችሁት ነገር ግን ሞትን ድል ነስቶ በተነሳው በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ይህንን አድርገናል ብሎ ጴጥሮስ መልስ ከሰጠው በኃላ መዳን በማንም የለም ብሎ እነርሱ የጠሉት እና የሰቀሉት ኢየሱስ ክርስቶስ ስሙ ራሱ አዳኝ መሆኑን ገለጸላቸው፡፡ቅዱስ ጴጥሮስ ና ሌሎችም ሐዋሪያት አላማቸው የኢሱስ ክርስቶስን ጌትነትና አዳኝነት መመስከርና ለዓለም ማሳወቅ ስለነበረ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና ብሏል ይህ ታዲያ ኢየሱስ ክርስቶስ አማላጅ ነው የሚያሰኝ ሳይሆን የስሙን መድኃኒትነት ክብር የሚገልጽ ነው፡፡ ‹‹መጽሐፍ ቅዱሳዊ መልስ መስጠት ጨዋነት ነው››.
ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር በሰራቸው ስራዎች ምን ተማርን የእርሱ ተከታዮች የሆንን ሁሉ የእርሱን አርአያ ልንከተል ይገባል ‹‹ከእኔ ተማሩ›› ብሎናል እና ልንማር ይገባል ማቴ 11፡29 ከእርሱ ብዙ እንማራለን ብዙ መማር የምንችለው አምላክ ፈጣሪ መሆኑን ስንረዳ ብቻ ነው፡፡ሐዋሪያት የጌታን ፈለግ ተከተሉ በድልም ተወጡ ዮሐ 15፡18-19 ,ዮሐ 16፡33 አርአያውን መከተል ሉቃ 2፡27 ,ሁሉን ነገር ጠይቀን መረዳት ሉቃ 2፡46 ,ስደትን አስተማረን ዮሐ 15፡2 እውነት እውነት እላችኃለው በእኔ የሚያምን እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል፡፡እኔ ወደ አብ እሄዳለው አብም ስለ ወልድ እንዲከበር በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ አደርገዋለው፡፡ማናቸውንም ነገር በስሜ ብለምኑ እኔ አደርገዋለው ዮሐ 14፡12-14 ቅዱሳን አባቶቻችን እና እናቶቻችን ከኔ ተማሩ ባለው መሰረት ከእርሱ የተማሩትን ነው የፈጸሙት፡፡

አዎ መዳን በሌላ በማንም የለም አዳኙ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ያለ እርሱ አዳኝ የለም፡፡ ቅዱሳን መላዕክት, ሐዋሪያት ቢያድኑ እንኳን ዋናው ምንጩ( በእነሱ አድሮ የሚሰራው) እሱ ኢየሱስ ነው ለማለት ነው እንጅ ሐዋሪያት እኮ የማዳን ስልጣን ተሰጥቷቸዋል/ማቴ 10፥1/ ሲያድኑም አይተናል “ጴጥሮስና ጳውሎስ በጥላቸውና በቀሚሳቸው ወይም በልብሳቸው ቁራጭ አዳኑ(ሐዋ 5፥15, ሐዋ19፥11) ፣ መላእክት እንደሚያድኑም ከላይ አይተናል፡፡ ነገር ግን የነሱ የመናፍቃን ችግራቸው የቅዱሳንን ማዳንና የኢየሱስን ማዳን ይቀላቅላሉ እኛ ግን ለይተናል፡፡ የዛሬዎቹ ከአይሁድ የማይሻሉ መናፍቃን ቅዱሳን ሐዋሪያት አያድኑም ይላሉ እንጅ አይሁድ እኮ እነ ጴጥሮስ አንካሳውን ሰው/ሐዋ 3፥2/ እንዳዳኑት (የሐዋሪያትን ማዳን) አውቀዋል፣ ነገር ግን # በማን ሀይል በማን # ስም እንዳዳኑት/ሐዋ 3፥6/ ምንጩን # ሲጠይቋቸው እንድህ ብለው መለሱ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” /ሐዋ 4፥12/ ብለው መለሱ ትክክል ናቸው፡፡ መናፍቃን ቅዱሳንን አያድኑም ይበሉ እንጅ የእነሱን የራሳቸውን ማዳን አይቃወሙም በየቻናሎቻቸው በየፖስተሮቻቸው የፈውስ ቀን ፣ ኮቴን የነካ እንኳን ይድናል፣ ማንም ማን ሊጨብጠኝ አይችልም ፣ እንፈውሳለን፣ እናድናለን ይላሉ፡፡ የራሳቸው ማዳን ይሰብካሉ ቅዱሳንን ግን አያድኑም ይላሉ፡፡ እኛም አንሰማችሁም እንላቸዋለን!

ወስብሓት እግዚአብሔር!

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top