ዓሳን በጾም

ዓሳን በጾም ለምን አንበላም?

ይህን ርዕስ አንስተን መነጋገር እራሱ ተገቢ አልነበረም ስለ መንፈሳዊ እንጂ ስለ ስጋ ማውራት አይጠቅመንምና!

ዓሳን በተመለከተ ብዙ ግዜ ጥያቄ ይነሳል፤ በፆም አሳ ለምን አንበላም? ጌታ ለሐዋርያቱ አሳን አበርክቶ ሰቷቸዋል፤ ሐዋርያቱም አሳ በልተዋል፤ ደግሞም እኮ በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበር ይህ አሁን የመጣ ታሪክ ነው ይሉና ለምን አሳን በጾም አንበላም ብለው ብዙ ግዜ ይጠይቁናል; እናንተም ተጠይቃቹ ወይም ሲባል ሰምታቹ ይሆናል።

ጌታ ለሀዋርያቱ አሳን መግቦቸዋል ስለዚህ ዓሳ በጾም ወቅት ቢበላ ምን ችግር አለው?

ጾም በሃዲስ ኪዳን የተጀመረው ከጌታችን ዕርገት በኋላ ነው ። ጌታምሀዋርያትን ዓሳ በሚያበላበት ወቅት ጾም አልንበረም! ነገር ግን እኛ አሁን በምንጾምበት ሰዓት ምሴተ ሀሙስ(የጌታ እራት) በአቢይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት በሆነው በህማማት ወቅት አብረን ስለምናስበው ጌታ ለሐዋርያት ዓሳ ያበላችው በጾም ወቅት ይምስለናል ይህ ግን ስህተት ነው። ምክኒያቱም በዚያ ወቅት ሀዋርያቱ ጾም እንደማይጾሙ ናግሯል።

በማቴ 9፥14፡18 ላይ የዪሀንስ ደቀመዛሙርት ወደ ጌታ መጥተው ለምንድን ነው እኛና ፈሪሳውያን እንጾማለን ያንተ ደቀመዛሙርት የማይጾሙት ብለው ጠየቁት ጌታም ሲመልስ እንዲህ አላቸው “ሚዜዎች ሙሽራው ከነሱ ጋር እያለ ሊያዝኑ ይችላሉን ? ነገር ግን ሙሽራው ከነሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል በዚያን ጊዜ ይጾማሉ አላቸው።” ይህንን ቃል እንደተመለከትነው ሙሽራው ተባለው ጌታ ከነሱ ጋር እያለ ሀዋርያት አለመጾማቸውን ነው። ነገር ግን ሙሽራው የተባለው ጌታ ከእነርሱ ከተለየ ቡሀላ ሀዋርያት ጾመዋል ። ለዚህም የመጸሀፍ ቅዱስ ጥቅስ ስንመለከት “በዚያን ጊዜም ከጦሙ ከጸለዩም በኋላ…….”ሐዋ13፥2 ላይ ።”በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው…..” ሐዋ14፥23 ይላል። 
ስለዚህም ሐዋርያቱ ጾምን የጾሙት ከጌታ ዕርገት በኋላ ነው!

በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበር …

“ኢትብልሁ ሥጋ ዘእንበለ አሳ” ይለናል በቀኖና ቤ/ተ/ክ

ይህም “ሥጋ አትብሉ አሳን ጭምር” ማለት ነው።
ሌሎች ግን “ሥጋ አትብሉ ከአሳ በቀር” ብለው ተርጉመውታል ይህ ግን ልክ አይደለም። ዘእንበለ የሚለው ግዕዝ ጭምር ወይም በቀር ተብሎ ይተረጎማል።

ምሳሌ እናቅርብ፦ “እግዚአብሔር ፈጠረ ኩሉ አለም ዘእንበለ ትል” ሲል እግዚአብሔር አለምን ሁሉ ፈጠረ ትልን ጭምር ይባላል እንጂ ከትል በቀር አይባልም። ስለዚህም አሳን ጭምር አትብሉ ማለት ይሆናል ማለት ነው።

ዓሳ ከበግና ከበሬ ስጋ የተሻለ ጥቅም አንዳለውም ይታወቃል። ስለዚህ ከበግና ከበሬ ተከልክሎ አሳን መብላት እራስን ማታለል ነውና ቤተ ክርስቲያን በጾም ሰአት ዓሳን መብላት ለክላለች።( ሥጋም ሆነ የወይን ጠጅ ወደ አፌ አልገባም ዳን 10:3)

መደምደሚያ!

አበው አባቶቻችን በጾም ክርክር ቢነሳ ለጾም አድሉ ከመብል አለመብላት እጅግ ይሻላልና ብለው አልፈዋል!

” ሁሉ ተፈቅዶልኛል ነገር ግን ሁሉም ነገር አይጠቅምም”(1ኛ ቆሮ 10:23)

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top