ኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክ ነው እዚህ በመጫን ያንብቡ
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው እዚህ በመጫን ያንብቡ
ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በብሉይ ኪዳን የተነገሩ ምሳሌዎች እዚህ በመጫን ያንብቡ
ኢየሱስ ፈራጅ ወይስ አማላጅ?
በ1938 ዓ.ም የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል ፦ “ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በአብ ቀኝ ተቀምጧል ስለ እኛ ይፈርዳል”። በ1975 ዓ.ም ከግዕዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመውም እንዲህ ይላል፦ “የሚፈርድ ማን ነው? ክርስቶስ ኢየሱስ ሞተ ከሙታንም ተለይቶ ተነሳ በእግዚአብሔር ቀኝ ተቀምጧል ስለእኛም ይፈርዳል።”
በአሁኑ ሰዐት ከኦርቶዶክሳውያን በቀር በአብዝሃኛው ሕዝብ ተሰራጭቶ የሚገኘው እንዲህ ይላል፦ “እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል? የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው:: የሚኮንንስ ማን ነው? የሞተው ይልቁንም ከሙታን የተነሳው በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው ደግሞ ስለኛ የሚማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።” በሮሜ 8:-34 ላይ በተለያዩ ዘመናት የተጻፉ መጽሐፍ ቅዱሶችን ተመልክተናል። ቀድሞ የታተመው መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለኛ ይፈርዳል ብሎ ፈራጅ ሲያደርገው በብዙወቻችን እጅ አሁን የሚገኘው አዲሱ ትርጉም አማ ላጅ አድርጎታል። ታዲያ ትክክለኛው የቅዱስ ጳውሎስ ቃል የትኛው ነው? ብለን ስንጠይቅ መረዳት የምንችለው አንድም ቀዳሚውን በመመልከት ካልሆነ ደግሞ ከምንባቡ ሃሳብ በመነሳት ነው። ስለዚህ ቀጥለን በዝርዝር እንመልከተው። ቁጥር 33 ላይ እንዲህ ሲል ይጀምራል:-“እግዚአብሔር የመረጣቸውን ማን ይከሳቸዋል?” ይህ ማለት እግዚአብሔር ተከተሉኝ ብሎ በመጥራት የመረጣቸውን አይ እነርሱ አያስፈልጉንም ፣ አንተን ሊከተሉ አይገባቸውም ብሎ የሚከሳቸው ማን ነው? በማለት ይጠይቃል በመቀጠልም “የሚያጸድቅ እግዚአብሔር ነው።” በማለት የመረጣቸውን ሰዎች መንግሥቱን ለማውረስ እናንተ የአባቴ ብሩካን የሚያጸድቃቸው እግዚአብሔር ነው አለ፤ እንዲሁም የሚኮንን (የሚፈርድ) ማን ነው? በማለት ይጠይቃል። “መኮነን” ከግዕዙ ሳይተረጎም ቀጥታ የተወሰደ ቃል ሲሆን “ መኮነን“ ማለት መፍረድ ማለት ነው። ምክንያቱም “ኮነነ” ከሚለው የግዕዝ ሥርዎ ቃል የወጣ ነው። “ኮነነ” ማለት ደግሞ ፈረደ ፣ ገዛ ማለት ነው።እንግዲህ ማጽደቅና መኮነን የተለያዩ ትርጉም እንዳላቸው ማስተዋል ያስፈልጋል። ካፈርኩ አይመልሰኝ ካልሆነ እውነታው ይህ ነው። ማጽደቅና መኮነን የአማላጅነት ሥራ ሳይሆን … ተጨማሪ ያንብቡ ︾
የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ፦
የጌታችን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ የምናጠናው በአራቱ ወንጌላት አቀራረብ መሠረት ነው። ስናጠናም የታሪኩን ቅደም ተከተል በመጠበቅ ይሆናል።
የኢየሱስ ክርስቶስ ቀዳማዊነት፦
ከአራቱ ወንጌላት ውስጥ የኢየሱስ ክርስቶስን ቀዳማዊነት በመተረክ የሚጀምረው የዮሐንስ ወንጌል ነው። ቀዳማዊነት ስንል ኢየሱስ ክርስቶስ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት የነበረ፤ አልፋና ዖሜጋ፤ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው፤ ሁሉ በእርሱ የሆነ፤ ማንም የማይቀድመው፤ ለዘመኑ ጥንት ወይም ፍጻሜ የሌለው ማለታችን ነው። በዚሁ በዮሐንስ ወንጌል ውስጥ ተጽፎ የምናገኘው ታሪክ ገና ከመግቢያው ሲል እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ በመጀመሪያው ቃል ነበረ፥ ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ፥ ቃልም እግዚአብሔር ነበረ። ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ። ሁሉ በእርሱ ሆነ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። በእርሱ ሕይወት ነበረች፥ ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች። ብርሃንም በጨለማ ይበራል፥ ጨለማም አላሸነፈውም። ዮሐ. ፩፡ ፩ በዚህ ክፍል ዮሐንስ ጌታን <ቃል> ብሎ ይጠራዋል። ይህም በግሪክኛ <ሎጎስ> ይባላል። የኢየሱስ ክርስቶስ ህልውና የሚጀምረው በቤተልሔም ከተወለደ ጀምሮ አይደለም። ነገር ግን ዓለም ከመፈጠሩ በፊት በአምላክነቱ (በእግዚአብሔርነቱ)….ተጨማሪ ያንብቡ ︾
ነገረ ክርስቶስ በ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
በነገረ ክርስቶስ ዙሪያ የሚነሱ ጥያቄዎች በ መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
አልተሳሳትንም ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔር ነው
መጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ
ብዙዎች በዘመናችን የመጽሐፍ ቅዱስን ትምህርት ባለመረዳትና “እኔና አብ አንድ ነን” ያለውን የአምላካቸውን የኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክነትን፣ ፈጣሪነት፣ ፍጹም ተዋሕዶውን ፈራጅነቱን በመካድ ሎቱ ስብሐት ከአብ አሳንሰው ርሱን ለማኝ አብን ተለማኝ ያደርጋሉ፤ ቅድስት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን ከበፊት ጀምሮ እስካሁን ከመናፍቃን የሚደርስባት ፈተና ለምን ኢየሱስ ክርስቶስን የባሕርይ አምላክ ነው? ለምን ከአባቱ ጋር የተካከለ ፈራጅ ነው? ብለሽ ታስተምሪያለሽ የሚል ነው፤
ይህም ዐዲስ አይደለም የባሕርይ አምላክነቱን፣ ተዋሕዶውን፣ ፈራጅነቱን ከካዱት ውስጥ ከቀድሞዎቹ እነ ጳውሎስ ሳምሳጢ፣ አርዮስ፣ ንስጥሮስ …. በ16ኛው መቶ ክ.ዘመን ወዲህ በየዘመናቱ የሚነሱ የእምነት ድርጅቶች ወ.ዘ.ተ ይገኛሉ፤ የእነዚኽን አስተምህሮ በማስተምርበት የነገረ መለኮት ኮሌጅ ውስጥ ከደቀ መዛሙርት ጋር በክፍል ውይይት ጊዜ በጥልቀት የምዳስሰው ቢኾንም፤ ለ ፌስ ቡክ (face book) ጓደኞቼ ግን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ የምታስተምረውን በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተጻፈውን አስተምህሮ ጥቂቱን ከዚኽ በታች አስፍሬዋለኊ፡- ይኸውም በብሉይ ኪዳን የተጠቀሰው እግዚአብሔር ከሦስቱ አካል አንዱ እግዚአብሔር ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለመኾኑ የተጻፈውን የብሉይ ኪዳንና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍትን እውነት በማንበብ አረጋግጡ፡-
ሀ) ኢየሱስ ክርስቶስ በእውነት እግዚአብሔር ነው እንላለን፡፡
►“በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) ╬ “ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው” (ዕብ 1፡10)
►“እግዚአብሔርም ሙሴን፦ «ያለና የሚኖር» እኔ ነኝ አለው እንዲህ ለእስራኤል ልጆች። «ያለና የሚኖር» ወደ እናንተ ….ተጨማሪ ያንብቡ