ፆም 

✥ ፆም እና ጥቅሙ ለማንበብ እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ ዓሳ መብላት በጾም አይፈቀድም  እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ 7ቱ አጽዋማት ዝርዝር እዚህ በመጫን ያንብቡ

ከሩካቤ ሥጋ የምንታቀብበት ጊዜያት/ቀናት/ እና ምክንያት እዚህ በመጫን ያንብቡ

ፀሎት | daily prayer

✥ ምን ዓይነት ጸሎት በየትኛው ሰዓት እንጸልይ? እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ የዘወትር ጸሎት እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ አባታችን ሆይ እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ ውዳሴ አምላክ  እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ ውዳሴ ማርያም እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ መዝሙረ ዳዊት እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ ጸሎተ ነብያት እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ እንደቸርነትህ እዚህ በመጫን ያንብቡ

✥ አባታችን ሆይ አንድምታ እዚህ በመጫን ያንብቡ

 ስግደት  

ስግደት ቃል ለቃል ትርጉሙ መዋረድ ማጎንበስ፣ መንበርከክ፣ በግንባር በመውደቅ፣ ግንባርን ምድርን አስነክቶ መሬት ስሞ መመለስ ነው፡፡የገዥና የተገዥ የመታዘዝና የትህትና ምልክት /መገለጫ/ ነው፡፡ ‹‹በሠርክም መሥዋዕት ጊዜ ልብሴና መጎናፀፊያዬ እንደተቀደደ ሆኖ ከመዋረዴ ተነሳሁ በጉልበቴም ተንበርክኬ ወደ አምላኬ ወደ እግዚአብሔር እጄን ዘረጋሁ›› ( ዕዝ 9፡5)

ስንት አይነት ስግደት አለ

1~አድንኖ፦አድርጎ ይህ ማለት እራስን ዝቅ ከወገብ ጎንበስ ማለት ነው።

2~አስተብርኮይህ ማለት በጉልበት ወድቆ ግንባር መሬት ሳይነካ የምንነሳው ስግደት ነው።

3~ሰጊድይህ ማለት ሙሉ በሙሉ በጉልበት ወድቆ በግንባር መሬት ነክቶ ምንነሳው ስግደት ነው።

የማይሰገድባቸው ጊዜያት

የሚሰገድባቸው ጊዜያት እንዳሉት ሁሉ የማይሰገድባቸው ጊዜያትም አሉ፡፡ የግዝት በዓላት 5 ሲሆኑ የወልድ በዓል፣ የእመቤታችን በዓል፣ የቅዱስ ሚካኤል በዓል፣ ቀዳሚት ሰንበትና እሑድ ሰንበት ናቸው። ከነዚህ በተጨማሪ ከቁርባን በኋላና የበዓለ ሐምሳ ወራትም የማይሰገድባቸው ጊዜያት ናቸው። እነዚህ ስግደት የተገዘተባቸው ጊዜያት የሚከተሉት ናቸው፡፡

1ኛ. በዕለተ ቅዳሜና እሑድ

በዕለተ እሑድ

ከአልቦ ነገር ወይም ከምንም (ex- nihilo – from nothingness) የተፈጠረ ፍጥረት ሁሉ ክርስቶስ ዳግም ሲመጣ ጠፍቶ ወደ ምንምነት ሲቀየር ከማይጠፉ ከአምስቱ ፍጥረታት አንዷ ሰንበት ናት፡፡ ጌታ የተነሣባት ፣ ዳግምም የሚመጣባት ዕለት ናት፡፡ በዚህና በሌሎች ምክንያቶችም ሰንበተ ክርስቲያን እሑድ በዓል ነች፡፡ ስለዚህ በዕለተ እሑድ መስገድ የተከለከለ ነው፡፡ ይህንን ፍትሐ ነገሥቱ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል፡- “ከአድንኖና ከአስተብርኮ በቀር እስከ ምድር መስገድን የሚተዉባቸው የታወቁ ጊዜያቶች እነዚህ ናቸው፡፡ ኒቅያ 20፣ በዕለተ እሑድና በበዓለ ሃምሳ ወራት፣…” ፍት.መን. አን. 14 ቁ. 537 ይህንን ይበልጥ ሲያጸናው በሰንበታትና በበዓላት አንቀጹ እንዲህ ሲል ደግሞታል፡- “በእሑድና በተከበሩት በዓላት ቀን ስግደት አይገባም፤ እነዚህ የደስታ ቀኖች ናቸውና” ፍት. መን. አን. 19 ቁ. 715

በዕለተ ቅዳሜ

ሌላው ከዕለታት መካከል ቅዳሜ የግዝት በዓል ተብሎ የተመረጠበት ምክንያት የሁሉ ባለቤት የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ዓለማትን ሁሉ….ተጨማሪ ያንብቡ ︾

 ምፅዋት

5ቱ ስጦታዎች እና ሥርዓታቸው

ከመጋቤ አእላፍ ፋሲል ታደሰ (ቀሲስ)

ሥርዓተ አምልኮ  ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ ስጦታ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከራሱ  የሆነ አንዳች የለውም  በጎ የሆነውን ሁሉ ከፈጣሪ ዓለማት  ከእግዚአብሔር ያገኘው  ነው፡፡ በመሆኑም ፈጣሪያችን መስጠትን  እንዳስተማረን ሁሉ እኛም ተገዥነታችንን ከምንገልጥበት  አንዱ ከእርሱ የተቀበልነውን በፈቃደኝነት በደስታ በመስጠት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ይህን ሲያሰረዳ “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህ  የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ልናቀርብልህ የቻልን ማነን?… በፈቃዴ ይህን አቅርቤአለሁ” በማለት ከእግዚአብሔር  ያገኘውን ሀብት በደስታ  በፈቃዱ ለቤተ መቅደስ ሥራ እንዲውል መስጠቱን በመግለጽ ስለ ስጦታ ጽፏል/1ኛ. ዜና!9. 9-06/:: ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ  “ ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን” በማለት እንዳስተማረን ለእግዚአብሔር የምንሰጠው የአምልኮት መግለጫ በሥርዓት ልናደርገው እና ከልብ  ሊሆን ይገባል፡፡ ለዚህ  ደግሞ መሠረቱ የስጦታ ዓይነቶችንና የአቀራረብ ሥርዓቱን ማወቅ ነው፡፡ በዚህች አጭር ጽሑፍም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት መንፈሳዊ ምግባራት የሆኑትን አምስቱ የስጦታ ዓይነቶች ምጽዋት፣መባዕ፣ሰእለት፣ በኩራት እና አሥራትን እንመለከታለን፡፡
1. ምጽዋት፡-
ምጽዋት መስጠት ከገንዘብ፣ ከዕውቀት፣ከንብረት…ከመሳሰሉት ላይ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለችግሮኞች መለገስ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በአንቀጸ ብፁዓን ትምህርቱ “ ብፁዓን መሐርያን፣ የሚምሩ ብፁዓን” ናቸው ያለውስ ለምጽዋት ሲሆን ሊቃውንት ሲተረጉሙት በሦስት መንገድ ያስቀምጡታል፡፡ እነዚህም፡-
ሀ/ምሕረት ሥጋዊ፡- ይህ የሚያስረዳው ለሥጋ የሚሆን ነገርን መለገስን ሲሆን በይበልጥ ለችግረኞች በማሰብ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ነግሮች መለገስን ያመለክታል፡፡
ለ/ምሕረት መንፈሳዊ፡- በምክር ፣ በትምህርት… በሥነ ልቡናን የሚያንጽ /የሚያበረታ/ መንፈሳዊ

ምክር እና የሐሳብ ቀና የሆነ እገዛን ያስረዳል፡፡
ሐ/ምሕረት ነፍሳዊ፡- ደግሞ ራስን እስከ መስጠት “መጥወተ ርእስ” መድረስን ነው /ማቴ.5.7 /፡፡ትርጓሜ ወንጌል፡፡
ምጽዋት ካለን ነገር ላይ ማካፈልን ያመለክታል፡፡ ለፍጹምነትም የሚያበቃ ምግባር  መሆኑ የተመሰከረለት ነው፡፡ “ ፍጹም እንድትሆን ለድሃ ስጥ” እንዲል /ማቴ.09.!1 /፡፡
“የሚሰጥ ብፁዕ ነው” የሚለውም ኃይለ ቃል ይህን ያስረዳል፡፡ሐዋ./፡፡ በነገረ ምጽአትም ከሕይወት ቃል አንዱ በምጽዋት የሚገኝ መሆኑ እሙን ነው /ማቴ./፡፡
ምጽዋትን በልብስ፣ በገንዘብ፣ እንጀራ  በመቁረስ የመሳሰሉት ለደሃ በመስጠት ፣ በማካፈል መግለጽ ይቻላል፡፡ በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ምእመናን ሀብታቸውን ለደሃ ያካፍሉ እንደነበር በግብረሐዋሪያት ተጽፏል፡፡ ሐዋ/ እንደዚሁም ዕውቀትን  ማካፈል ፣ ምክር መለገስ ከምጽዋት የሚቆጠር ሲሆን ለእግዚአብሔር ቤትም  በገንዘብ፣ በጉልበት፣ በስጦታችን ማገልገል የምጽዋትን ዋጋ ያስገኛል/ኢሳ.$8.7 ፣ ሮሜ.02.8 ፣ ሮሜ.05.01-05 ፣ ምሳ.3.7/፡፡ በረከተ  ሥጋ ወነፍ  የሚያስገኘውንና በደልን የሚያስወግደውን  የልግስና ስጦታ /ምጽዋትን / ልማዳችን ማድረግ ይገባናል /ዳን.4.!7/፡፡
2.መባዕ፡-
ለአምላካችን ለልዑል እግዚአብሔር ከሚቀረበው የስጦታ ዓይነቶች አንዱ መባዕ ነው/ዘሌ. ፣ ዘኅ/፡፡ ነቢዩ ዳዊት መባዕ ለእግዚአብሔር ቤት እንደሚገባ ሲገልጽ “ እበውእ ቤተከ ምስለ መባእየ መባዬን በመያዝ ወደቤትህ  እገባለሁ” ብሏል /መዝ.85.03/፡፡ መባዕ ለቤተ መቅደስ መገልገያ የሚሆን እና ንዋያተ ቅዱሳትን በመስጠት የሚፈጸም ሲሆን ለምሳሌ ጧፍ፣ ዘቢብ፣…. የመሳሰሉት በአጥቢያችን እና በተለያዩ ገዳማት ስንሔድ ይዘን መግባት ይጠበቅብናል፡፡ #በፊቱ ባዶ እጃችሁን አትታዩ$ እንዲል /ዘዳ.33.”5፣”4.!/፡፡
መባዕ ማቅረብ የተገዥነት መገለጫ በመሆኑ በረከት የሚያስገኝ ምግባር ነው፡፡ በቤተልሔም የተገኙት የሰብአሰገል እጅመንሻየ ለዚሁ አብነት ይሆናል፡፡ ማቴ፡2 በቤተክርስቲን በጸሎት መባዕ በካህኑ በሚደርሰው ሥርዓተ ጸሎት #መብአቸውን ተቀበል$ የሚለው ብራኬ የመንፈሳዊ ጸጋ ተሳታፊ ያደርጋል /ማቴ.5.!4 ፣ማር.7.02/፡፡
3.ስእለት፡–
ስእለት  ሰው በፈቃዱ አንድ ነገር ለእግዚአብሔር ለማድረግ  /ደስታውን ለመግለጥ/ ቃል የሚገባበት ሥርዓት ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት በቅዱሳን አማላጅነት በማመንና በመማጸን “ ይህ ቢደረግልኝ ይህን አደርጋለሁ” በሚል አገላለጽ ቃል የሚገቡት የስጦታ ዓይነት ነው፡፡
ሰእለት እምነታችንን ይምንገልጽበትም በመሆኑ በሥርዐት እና ከልብ ሆነው ስእለት ሊሳሉ ይገባል፡፡ ጠቢቡ ሰሎሞን ይህን” ለእግዚአብሔር በተሳልህ ጊዜ ትፈጽመው ዘንድ አትዘግይ፣ የተደሳልከውን ፈጽም፣ የማትፈጽም  ከሆነ አትሳል” በማለት አስረድቷል/መክ 5.4/፡፡ እመሳሙኤል  ሐና እንደተሳለችና ስእለቷን እንደፈጸመች ይህም ምግባር ቀድማም የነበረ እና መጽሐፍ  ቅዱሳዊ እንደሆነ የሚስተምረን ነው/1ኛ ሳሙ. 1.1/፡፡ በረከት ለመቀበል እና ፍላጎታቸው እንዲሟላ  የሚሉም ነበሩ፡፡ /ዘፍ.!8.! ፣ዘሌ.!7፣ ዘኅ.!1.1-3 ፣ምሳ.01.” /፡፡
ሰእለትን በአግባቡ መሳል እና በቃላችን መሠረት መፈጸም የሚገባ ሲሆን ነገር ግን ቃልን አለመጠበቅ ደግሞ ኃጢአት ስለ መሆኑ እንዲህ ተጽፏል” ለአምላካችን ለእግዚአብሔር ስእለት በተሳልህ ጊዜ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና ኃጢአትም ይሆንብሃል መክፈሉን አታዘግይ፡፡ ባትሳል ግን ኃጢአት የለብህም በአፍህ የተናገርኸውን ለአምላክ ለእግዚአብሔር በፈቃድህ ተስለሃልና ከከንፈርህ የወጣውን ታደረግ ዘንድ ጠብቅ /ዘዳ.!3.!1-!3፣ ምሳ.!.!5/፡፡
4.በኩራት
በኩር ማለት መጀመሪያ ማለት ሲሆን የበኩራት ስጦታ ከልጅ ፣ ከከብት ከንብረት … ከመሳሰለው የመጀመሪያውን መስጠት ነው፡ የአዳምል አቤል መሥዋዕት  ሲያቀርብ “ የመጀመሪያውን ለየ” የሚለው  የኩራቱን ስማቅረቡ ሲስረዳ ሲሆን ይህም ተወደደ መሥዋዕት ሆኖለታል /ዘፍ.4.4/፡፡ ከዘመነ ኦሪት  ጀምሮ  ሕዝበ እግዚአብሔር አምልኮታቸውን ከሚገልጡበት አንዱ በበኩታት ነበር፡፡ ከልጆቻቸው፣ ከምርታቸው… በኩር  የሆነውን ለእግዚአብሔር ቤት ይሰጣል፡፡ /ዘኅ.3.#2፣1ሳሙ.2፣ዘኅ.08.05-07/፡፡
በኩራትን ማቅረብ እጅግተወደደ እና ከሁሉ የሚበልጥ የስጦታ ዓይነት ነው /ዘዳ.!3.09፣ዘዳ 86/፡፡
በኩራትን  ማቅረብ እጅግ ተወደደ እና ከሁሉ የሚበልጥ የስጦታ ዓይነት  ነው /ዘዳ .!3.09፣ ዘዳ.!6/፡፡ ክርስቲያኖችም ሁላችንም ሥርዐተ አምልኮ የምንገልጥበት አንዱ     የሆነው በኩራቱን በማቅረብ ሕገ-አምላክን ልንጠብቅ ይገባል፡፡ ይህንንም ከመጀመሪያው ምርታችን ከመጀመሪያ ደመወዛችን የመጀመሪያ (ቦነስ) ጭማሪዎችን ለእግዚአብሔር ቤት በመስጠት የተናገረውን ከማያስቀረው አምላካችን በረከት አንደምናገኝ በማመን ልንፈጽም ይገባናል/ዘዳ.!8.1-05//፡፡
5.ዐሥራት
ዐሥራት አንድ ዐሥረኛ ማለት ነው፡፡ ከሚያገኙት ገቢ አንድ ዐሥረኛውን ለእግዚአብሔር ቤት  መስጠትን ያመለክታል፡፡ ከሙሴ በፊት በዘመነ አበው የተጀመረ የእግዚአብሔር ሕግ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዐሥራት በስፋት ይገልፃል፡፡ ከእነዚህም ለአብነት ያህል  በጥቂቱ እንመልከት፡፡
አበብዙኃን አብርሃም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ መልከ ጼዴቅ በሔደ ጊዜ ዐሥራት ማውጣቱን “ አብርሃምም ከሁሉ ዐሥራት  ሰጠው” በማለት ዐሥራት አበው እንደጀመሩት  ያስረዳና. /ዘፍ.04.!/፡፡ ያዕቆብ ከአባቶቹ የወረሰውን ሕገ አምላክ የሆነውን ዐሥራት  ማውጣትን ሲገልፅ “ ከሰጠኸኝ ሁሉ ለአንተ ከዐሥር አንዱን እሰጣለሁ” ብሏል ዘፍ!8.1- !2.፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ዐሥራት ሲስረዳ ከእግዚአብሔር የታዘዘ  መሆኑ አጽንኦት በመስጠት ነው፡፡” ከመታገኘው ሁሉ ዐሥራትን ታወጣለህ “ የሚለው “ዐሥራት አስገቡ” ማለቱ  እንደዚሁም  የምድር ዐሥራት እግዚአብሔር  መሆኑን የሚገልጹ ማሽረጃች ሁሉ ሕገ አምላክ  መሆኑን ያረጋግጣል፡፡ /ዘዳ04.!2 ፣ ዘሌ.!7.”፣ዘዳ.04.!3፣ ሚል.3. 0/፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመዋዕለ ስብከቱ “ትእዛዝ መሆኑን አስገንዝቦናል /ማቴ.!2.07/፡፡ እንደዚሁም አንድ ቀራጭ ወደ ጌታችን ቀረቦ “ከማገኘው ዐሥራት አመጣለሁ” ማለቱ ቀድሞ የነበረ ሕግ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን ጌታችንም ለቀራጩ   በዐሥራት ጉዳይ ላይ የተለየ መልስ አለመስጠቱ ዐሥራት ተገቢ የሆነ ሥርዓት መሆኑን የሚያመለክት ነው/ ሉቃ.08.02//፡፡
ዐሥራት በመስጠታችን  የምናገኘው ጥቅም ምንድን ነው?
ሀ. በረከት ይበዛልናል
ዐሥራት ማውጣት ትእዛዝን መፈጸም ነውና በአምላካዊ ቃሉ መሠረት በረከቱን የበዛልናል፡፡ “ ቃሌን ብትሰማ በረከቶች ሁሉ ላንተ ይሆናሉ” በማለት ቃል እንደገባልን  ዐሥራት በማውጣት ለቃሉ ብንገዛ ሀገር ፣ ቤት ትዳር፣ ልጆች ወዘተ… ሁሉም እንደሚባረኩ የታመነ ነው/ ዘዳ.!8.1-!/፡፡ በነቢዩ  ሚልክያስ  የተጻፈው  ቃለ እግዚአብሔር እንደሚያረጋግጥልን የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ዐሥራት በማውጣት ብንታዘዝ “የሰማይ መስኮትን  እከፍታለሁ  በረከትን  እሰጣለሁ”  በማለት አስገንዝቦናል /ሚል3.0./፡፡
ለ. ለጽድቅ ያበቃል
“ሕግን የሚሠሩ ይጸድቃሉ” እንዳለ ዐሥራት ሕግን መፈጸም ነውና ለጽድቅ የሚበቃ መሆኑን ልናምን ይገባል /ሮሜ.02.02/፡፡ ሕገ እግዚአብሔርን በመፈጸም ምህረተ ሥጋ ወነፍስ የምናገኝ መሆኑን በማይሻር ቃሉ እንዲህ ብሏል “ትእዛዜን ለሚጠብቁ ምሕረትን የማደርግ እኔ ነኝ” /ዘዳ.!.6/፡፡ ቅዱሳን ሐዋርያትም ከልብ በሆነ ፈቃደኝነት  ዐሥራት በመስጠት ክርስትናችንን እንድንገልጽና ለጽድቅ እንድንበቃ መክረውናል፡፡ በመሆኑም  ከምናገኘው ላይ ከዐሥር አንድ አስበን ለእግዚአብሔር ቤት በመስጠት ለመንፈሳዊ ዋጋ ልንተጋ ይገባል፡፡ “በበረከት የሚዘራ በበረከት ያጭዳል” ተብሏልና /1ቆሮ.06.04 ፣ቆሮ.9.6 -02/፡፡
 ነገር ግን በተቃራኒው ዐሥራት በስስትና በተለያዩ ምክንያቶች አለመክፈል ከእግዚአብሔር ጸጋ ያርቃል፣ መርገምንም ያመጣል፡፡ “ሰርቃችሁኛል … ይኸም ዐሥራትና በኩራቴን ነው” የሚለው ኃይለ ቃል የሚያስረዳውም ዐሥራት አለመክፈል ከእግዚአብሔር ገንዘብ ላይ መስረቅ መሆኑን ነው፡፡ በነቢዩ በኢሳይያስ የተነገረውም ያለመታዘዝን ጉዳት ያስረዳል “እምቢ ብትሉ ሰይፍ ይበላችኋል”/ ኢሳ.1.09/፡፡ እንዲል፡፡
ዐሥራት አከፋፈል
ዐሥራት መክፈል አምልኮተ እግዚአብሔርን ከምገልጽበት ተግባር አንዱ መሆኑን ከተገነዘብን አከፋፈሉንም በማስተዋል ልንፈጽም  ያስፈልጋል፡፡ዐሥራት ከገቢ/ከደመወዝ/ ከዐሥር አንዱን በየወሩ ለቤተክርስቲያን  በመምህረ ንስሐ በኩል ወይም በቀጥታ በመሔድ በየወሩ ልንከፍ ይገባል፡፡ የምንከፍለውን ዐሥራት ለገጠርም ሆነ ለአጥቢያችን ስናበረክት ማረጋገጫ መቀበል ሳንዘነጋ ነው፡፡ ይህም ማለት ሕጋዊ ሰነድ (ሞዴል) የመሰለ ማስረጃ መቀበል ያስፈልጋል፡፡አገልግሎቱም፡፡
ሀ/ ሥርዐተ አምልኮ ለማስፈጸም
 የምንከፍለው ዐሥራት ለሥርዓተ አምልኮ ማስፈጸሚያ ይሆናል፡፡ ከዘመነ ኦሪት ጀምሮ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረዳው የቤተ መቅደስ መገልገያ እና አገልግሎቱ በዐሥራት ስጦታ ይሟላል/ዘዳ.!7.1/፡፡ ስለሆነም ለሥርዓተ ቅዳሴ የሚያስፈልጉ እና ለመንፈሳዊ አገልገሎት የሚውሉ ነገሮችን ሁሉ በካህናት አስፈጻሚነት ይሟላበታል፡፡
ለ. አገልጋዮችን ለመርዳት
 በዘመነ ኦሪት ሌዋውያን በዐሥራት እንዲጠቀሙ እና በአግባቡ እንዲያገለግሉ ፈቃደ እግዚአብሔር በመሆኑ ለአገልጋዮች ይውላል/ዘኀ.08.!1/፡፡ በዚህም መሠረት በዘመነ አዲስም በፍትሐ ነገሥት እና በቃለ ዐቃዲ በተመዘገበው መሠረት የቤተክርስቲያን መደበኛ አገልጋዮች የሆኑ ካህናት ከሚገባው ዐሥራት ላይ ወርኃዊ ደመወዝ እያገኙ አገልግሎታቸውን እንዲፈጽሙበት ይውላል፡፡ ዐሥራትን ሳናስቀር በአግባቡ ብንከፍል እና አገልጋዮችም አግባብ ባለው ቦታ ላይ ቢያውሉት በይበልጥም በገጠር ዛሬ የምናየውን የአገልጋዮች መጉላላት ፣ የአብነት ትምህርት ቤቶች መፈታት፣ በገጠር የካህናት እጥረት … የመሳሰሉት ችግሮችን የሚቀርፍ ዋና አማራጭ መፍትሔ መሆኑ ሊስተዋል ይገባል፡፡
ሐ. ነዳያንና ጧሪ ቀባሪ የሌላለቸው ይረዱበታል፡፡
ነዳያን ከሙዳየ ምፅዋት ብቻ እንደሚረዱ የሚያስተምሩ መምህራን ያሉ ቢሆንም በተጨማሪም ግን ከቃለ ዐዋዲ ላይ እንደተጻፈው በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚገኙ ደካሞች እና በተለያዩ ምክንያቶች መሥራት የማይችሉ ነዳያን ከምእመናን ከሚመጣው ዐሥራት ላይ ተቀንሶ በበጎ አድራጎት ክፍል (በደብሩ ወይም በገዳሙ አስተዳዳር አባላት) አስተባባሪነት  እንዲረዱበትም ያዝዛል፡፡ በሙሴ እና ሌዋውያንም በስፋት በቤተመቅደስ በሚያገልግሉበት ዘመን ከዐሥራት ላይ ለነዳያን እንዲሰጡ እግዚአብሔር ስለማዘዙ ተጽፏል፡፡ ስለዚህም ዐሥራት ለነዳያን የሚውል መሆኑንም ያረጋግጣል፡፡ /ዘዳ. 04.!8፣86.12/፡፡

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

 

Copyright © 2010 – 2023 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top