zetewahedo Posts

ዳግም ምጽአት

ዳግም ምጽአት    ( በዲ/ን ያሬድ መለሰ) ምጽአት መምጣት ማለት ሲሆን ዳግም የሚለው ቃል ሁለተኛ ምጽአት (መምጣት) የሚለውን ያመለክተናል ይህም የድርጊቱን መደገም የሚያመለክት ነው፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን የመጀመርያ መምጣት(ቀዳማዊ ምጽአት) ስንለው ዳግመኛ የጌታን ለፍርድ መምጣት ደግሞ ዳግም ምጽአት እንለዋለን፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የጌታችንን ዳግም መምጣት በዓመት ሦስት ጊዜያት ታስባለች […]

ዳግም ምጽአት Read More »

የዘወትር ጸሎት

በአማርኛ በስመ ሥላሴ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።  * በጌታዬ በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕምርተ መስቀል ፊቴንና መላ ሰውነቴን ሦስት ጊዜ አማትባለሁ ፩. አንድ አምላክ በሆኑ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ንጹሕ ልዩ ክቡር ጽሩይ በሆኑ በሦስትነት ወይም በሥላሴ እያመንኩና እየተማጸንኩ ጠላቴ ሰይጣንን እክድሃለሁ፤ በዚህች በእናቴ በቤተ ክርስቲያን ፊት ቁሜ እክድሃለሁ ለዚህም ምስክሬ ማርያም ናት። በዚህም ዓለም በወዲያኛውም ዓለም እሷን

የዘወትር ጸሎት Read More »

የበዓል ጊዜያት

ወርሃዊ በዓላት 1.     ልደታ፣ዮሐንስ ፣ራጉኤል ፣እዮብ ፣ኤልያስ ፣ ሶስና 2.  በርቶሎሚዎስ ፣ጴጥሮስ ፣አባ ጉባ ፣መሪና 3.  በአታ ማርያም ፣ፋኑኤል ፣ዜና ማርቆስ 4.  ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ ፣አባ መቃርዎስ፣ አባ አብርሐ 5.  ጴጥሮስና ጳውሎስ ፣ገብረ መንፈስ ቅዱስ 6.  ቁስቋም ፣ኢየሱስ ፣አርሴማ ቅድስት ፣እያሱ 7. አጋዕዝተ አለም ሥላሤ ፣ዲዎስቆሮስ 8.  ኪሮስ ፣ማቲዮስ፣ ኪሩቤል አርባእቱ እንስሳ፡ ዘካርያስ 9. 

የበዓል ጊዜያት Read More »

የስርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች

ሥርዓተ ቤተ-ክርስቲያን ሥርዓት ማለት ምን ማለት ነው ሥርዓት ማለት ‹‹ሠርዐ›› ሰራ ካለው የግእዝ ግስ ወጣ፡፡ ትርጉሙም ደምብ፣ አሠራር መርሐ ግብር ማለት ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን ማለትስ ምን ማለት ነው ቤተ ክርስቲያን፡- በዘርፍና በባለቤትነት የተቀመጠ ስም ነው ሦስት አይነትም ትርጉም አለው፡፡ 1ኛ የክርስቲያን ቤት፣የክርስቲያን መሰብሰቢያ፣ የክርስቲያን መገናኛ ማለት ነው፡፡ (ኢሳ56፡7) ፣ (ኤር7፡10-11)፣ (ማቴ 26፡13)፣ (ማር 11፡17)፣ (ሉቃ 19፡46) ሕጻን ሽማግሌ፣ድሀ ሀብታም፣ወንድ

የስርዓተ ቤተክርስቲያን ምንጮች Read More »

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

✥ ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እዚህ በመጫን ያንብቡ ✥ ፹፩ (81) መፅሐፍ ቅዱስ እዚህ በመጫን ያንብቡ ✥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት_የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክና ትርጉም እዚህ በመጫን ያንብቡ ✝የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መግቢያ ✝ ክፍል አንድ መጽሐፍ ቅዱስ ምንድነው? 🗝 መጽሐፍ ቅዱስ ቃሉ እንደሚያመለክተው መጽሐፍ እና ቅዱስ የሚሉ የሁለት ቃላት ጥምረት ነው ፡፡ ★“መጽሐፍ” ለሚለው ምንጭ በግሪክ ቋንቋ ቢብሎስ (byblos) ከደንገል በተሠራ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት Read More »

ዓሳን በጾም

ዓሳን በጾም ለምን አንበላም? ይህን ርዕስ አንስተን መነጋገር እራሱ ተገቢ አልነበረም ስለ መንፈሳዊ እንጂ ስለ ስጋ ማውራት አይጠቅመንምና! ዓሳን በተመለከተ ብዙ ግዜ ጥያቄ ይነሳል፤ በፆም አሳ ለምን አንበላም? ጌታ ለሐዋርያቱ አሳን አበርክቶ ሰቷቸዋል፤ ሐዋርያቱም አሳ በልተዋል፤ ደግሞም እኮ በድሮ ግዜ አሳ ይበላ ነበር ይህ አሁን የመጣ ታሪክ ነው ይሉና ለምን አሳን በጾም አንበላም ብለው ብዙ

ዓሳን በጾም Read More »

ውዳሴ አምላክ

ውዳሴ አምላክ ዘዘወትር ከቁጣ የራቅህ ይቅርታህ የበዛ ጻድቅ ልበ ሰፊ መሐሪ ሆይ አከብርሃለሁ። ዕለት ዕለት ስበድል ታግሠህ ጠብቀኸኛልና፤ ንስሐ እንገባ ዘንድም ለሁላችን ሥልጣን ሰጠኸን፤ስለዚህ እናከብርህ ዘንድ ክቡር ስምህን እናመሰግን ዘንድ ታገስኸን ስለምትሠራው ሁሉ የፍጥረት ሹም ሆይ ኀዘንና ፍርሃትን ድካምንም የምታመጣበት ጊዜ አለና። በነቢያት የዘለፍክበት ጊዜም ነበርና ኋላ ግን በአንድ ልጅህ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መታየት ጐበኘኸን። ካለመኖር ወደ መኖር

ውዳሴ አምላክ Read More »

ውዳሴ ማርያም

ሶርያዊው ቅዱስ ኤፍሬም የደረሰው ሰኞ የሚጸለይ አምላክን የወለደች የድንግል ማርያም ምስጋና መጀመሪያ ክፍል ፩. ጌታ ልቡ ያዘነና የተከዘ አዳምን ነፃ ያወጣውና ወደ ቀድሞ ቦታው ይመልሰው ዘንድ ወደደ። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፪. ከድንግል ያለወንድ ዘር በሥጋ ተወለደና አዳነን ከይሲ (ዲያብሎስ) ያሳታት ሔዋንን እግዚአብሔር ምጥሽንና ጻዕርሽን አበዛዋለሁ ብሎ ፈረደባት ሰውን ወደደና ነፃ አደረጋት። ቅድስት ሆይ ለምኝልን። ፫. ሰው የሆነና በእኛ ያደረ ቃል ኢየሱስ ክርስቶስ

ውዳሴ ማርያም Read More »

ዳውንሎድ ሞባይል አፕ

ሶሻል ሚድያ ላይ ያግኙን

Copyright © 2010 – 2025 zetewahedo.com | All rights reserved.
error: Content is protected !!
Scroll to Top